ኤድስ የመጣብን ከወያኔና ከሻእቢያ ጋር ተቀናጅቶ ነው!
ኤድስ
የመጣብን ከወያኔና ከሻእቢያ ጋር ተቀናጅቶ ነው!
በቅርቡ የወያኔ-ትግሬ አገዛዝ መራዊን በኤድስ እንዳጠቃው የተሰራጨውን መረጃ ያነበቡ ሁለት
ነርሶች የሚሉት አላቸው። እንደ ነርሶቹ ከሆነ በኤድስ ሕዝብን ማጥፋትና መበከል የተጀመረው ደርግ ወድቆ ወያኔና ሻእቢያ ስልጣን
ከያዙ ቀን ጀምሮ ነው። ነርሶቹ ዛሬ በአውሮፓ ነዋሪዎች ናቸው። ቀደም ሲል በጎንደር ሆስፒታልና በበለሳ የጤና ጣቢያዎች የሰሩ
ናቸው። እንደነርሱ ከሆነ በተለይ የኤድስን ቫይረስ ያስረጩ የነበሩት በበሽታው የተበኩሉት ኤርትራውያን የሻእቢያ ወታደሮች
ነበሩ። ብዙዎቹም የሻእቢያ ወታደሮች በበሽታው መሞታቸውን ይናገራሉ። ጉዳዪም በቶሎ ስለተደረሰበት በጎንደር በሽታውን እንዴት
መከላከል እንደሚቻል በቂ ትምህርት በወቅቱ ይሰጥ እንደነበር ነርሶቹ ተናግረዋል። ተመሳሳይ ትምህርት ግን በጎጃም ስለመሰጠቱ መረጃ
የላቸውም። በሌላ በኩል ጋይንት ውስጥ ወያኔ-ትግሬ ህዝቡን መርፌ በመውጋት በኤድስ ማጥቃቱን ያልተረጋገጡ ምንጮች ይጠቁማሉ።
ኸረ ለነገሩ ኤድስን ለመከላከል በጎንደር ይሁን በሌላው ኤትዮጵያ የተሰጠው ትምህርት ምን ያህል
ተከታታይነት አለው? ወያኔና ሻእቢያ ስልጣን ከያዙ 23 አመታቸው ነው። በዚያኔ ለአቅመ አዳም የደረሱት ሊጠነቀቁ ይችላሉ።
ተከታታይ ትምህርትና ምክር ግን ለታዳጊው ከወላጆቾች፣ ከሃይማኖት አባቶችና ተቁዋሞች ካልተሰጠው አደጋው ሊረሳ ይችላል። ለኤድስ
መዳህኒት ተገኘ ከተባለ በሁዋላ እንኩዋን በአውሮፓ ሰው ዘና ማለት በመጀመሩ ብከላው አልጠፋም። ዛሬም ሰዎች ይጠቃሉ።
በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዘመን ረሃብ በወሎና በትግራይ ገብቶ ሰዎች እያለቁ ነው በመባሉ፤ የአዲስ
አበባ ዩኒቨርስቲ አስተማሪዎች፤ እንደ ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌና ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያ በቦታው ሄደው ችጋሩን በአይናቸው
አይተው ለዓለም ይሁን ለኢትዮጵያ ሕዝቡ በደሉ እንዲታወቅ አድርገዋል። በደርግ ጊዜም በተከሰተው ትልቅ ረሃብ፤ ነፍሱን ይማረውና
ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን ሄዶ በአይኑ እንዳየና ያቀፈው ልጅ እጁ ላይ እንደሞተ ነግሮኛል። የድሮዎቹ የዩኒቨርሲቲ አስተማሪዎች
ይሁኑ የጥበብ ሰዎች የጠለቀ እውቀት ብቻ ሳይሆን ህሊናም ነበራቸው።
የዛሬዎቹ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ምሁራን፤ በእውቀት የከረከሱ፣ አድርባዮች፣ ፋራንክ ብቻ
የሚያሳድዱ ሆዳሞችና የወያኔ-ትግሬ አሽከሮች ናቸው። ይኽ ሁሉ ህዝብ በወያኔ-ትግሬ በበሽታ እያለቀ፣ ከቄየው እየተፈናቀለ ለሞት
ሲዳረግ፤ ምንም ነገር አይናገሩም። አይሰሩም። ጭጭ። ምጭጭ። ግፉና ወንጀሉ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችም መነጋገሪያ ጉዳይ እንዲሆን እንኩዋን
አያበረታቱም።
እነርሱ ብቻ አይደሉም። ሌላው ይቅር በቤነሻንጉል አማሮች እንደዛ በግፍ ሲባረሩ፤ የሰብአዊ
መብት ድርጅቶች አድርባዮችና አፍቅሮተ ነዋይ ዳሬክተሮችም በቦታው ሄደው አንዲት ብጣቂ ሪፖርት እንኩዋን አላቀረቡም። የሰማያዊ
ፓርቲ በቦታው እንደነበር ትዝ ይለኛል። ሌሎች የፖለቲካ ድርጅት ተወካዮች ምን እንዳደረጉ መረጃ የለኝም። ምን አይነት አገር
ነው? ምሁር ተብዬው ይሁን ሕዝቡ አፉ ተሽብቦና አይኑ ተደፍኖ ዝምብሎ የሚያልቅ!
Comments
Post a Comment