ወያኔ-ትግሬ፤ መራዊን በኤድስ ቀጣው!



            
                      ወያኔ-ትግሬ፤ መራዊን በኤድስ ቀጣው!

                     ከአሻግሬ ይግለጡ(የብእር)፤ መራዊ፤ መስከረም 2007

ፋሺስቱ የወያኔ-ትግሬ ሰርዓት፤ የመራዊን ወረዳ ህዝብ በኤድስ በሽታ እንዲጠቃ፤ ሁኔታዎችን በማመቻቸት የቂም በቀል እርምጃ መውሰዱን ሁነኛ ምንጮች አጋለጡ።
መራዊ በምእራብ ጎጃም የምትገኝ ወረዳ ናት። በ1997 በተደረገው አገራዊ ምርጫም እንደ ድፍን ጎጃም ሁሉ ነዋሪዋ ቅንጅትን መምረጡ ይታወሳል።
“…በዚህ ቂም የያዘው የወያኔ-ትግሬ ፍሽት አገዛዝ፤ ከራሱ ጦር ውስጥ በኤድስ ቫይረስ የተጠቁትን ወታደሮች መርጦ ምንም የፀጥታ ስጋት በሌለባት መራዊ ወረዳ ካምፕ ሰርቶ ያሰፍራቸዋል። ከዚያም ወታደሮቹ ሴተኛ አዳሪዎችንም ሆነ በገንዘባቸው ሊያዞምቱ የሚችሉትን ሌሎችን መገናኘትና ብሎም መበከል ይጀምራሉ። በዚህም የተነሳ በአጭር ጊዜ ውስጥ ቁጥሩ ያልታወቀ ሰው በበሽታው ሊጠቃ ችሎአል።  ዛሬ በመርሃዊ ብዙ ሰው የኤዴስ በሽተኛ መሆኑን በአይን አይቶ መመስከር እንደሚቻል እነዚሁ በቅርቡ ወደ ቦታው ሄደው ያዩ የአይን ምስክሮች አረጋግጠዋል።”
ከዚህ ቀደም እ.ኢ.አ በ2000 ዓ.ም በጎጃም ማቻክል ወረዳም፤ አማራውን በክትባትና በኪኒን ስም በማምከን ፋሽቱ ወያኔ-ትግሬ እያደረገ የነበረውን የዘር ማጥፋት ወንጀል ከእነዚሁ ምንጮች አግኝተን ኢፋ ማድረጋችን ይታወሳል። አገርቤት ለአማራው እንታገላለን የሚሉ ድርጅቶችም መረጃው ደርሶአቸው፤ በፍርሃት ይሁን በወያኔ ወኪሎች እቀባ ምንም እርምጃ ሳይወስዱ ቀርተዋል።
ይሁን እንጂ በአሳዛኝ ሁኔታ፤ ወንጀሉ እጅግ ዘግይቶ እንደወንጀል መታየትና እሪ! መባል የተጀመረው የአማራው ሕዝብ ቁጥር ያውም በወያኔ-ትግሬ ፓርላማ 2.4 ሚሊዮን ቀነስ ከተባለ በሁዋላ ነው። በመቀጠልም የአይን እማኞች በማቻክል ተገኝተው የመረጃችንን ሃቅኝነት ከአምስት አመታት በሁዋላ በቪዲዮ ቀርጸው ማረጋገጣቸው ይታወቃል።
የማቻከሉም ሆነ የመራዊው ወንጀሎች ዋና ተጠያቂዎች የፋሽቱ የወያኔ-ትግሬ ስርዓትና አሽከሮቹ ናቸው። ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ግን በማቻከሉ የመጀመሪያው ተጠያቂ የአማራ ቀንደኛ ጠላት ነው።
አንድ እ.አ.አ በ2010 የተዘጋጀ መረጃ እንደሚያመለክተው፤ የክሊንተን ፋውንዴሺን በመራዊ የኤድስ ፋይረስ ከእርጉዝ እናቶች ወደ ጽንሱ እንዳይተላለፍ ህክምና እየሰጠ ይገኛል። የጤና ጣቢያዎቹ ባለሙያዎችም ሆነ በበጎ ፍቃደኝነት ስለበሽታው አገረኛውን የሚያስተምሩና የሚመክሩ ሰዎች እንደተናገሩት፤ “የበሽታው ስርጭት ዋነኛ ምንጭ የሆኑትን ሴተኛ አዳሪዎች መለየታቸውን አስታውቀዋል።”
አማራውም ሆነ ሌላው ኢትዮጵያዊ ማወቅ ያለበት፤ የትግሬ-ወያኔ አገዛዝ አማራን ለማጥፍት የሚፈልግባቸው የራሱ ብዙ ምክንያቶች እንዳሉት ነው።  
1ኛ፤ ትግራይ በተፈጥሮ የተራቆተና አፈሩ የታጠበ ስለሆነ፤ በዘር ፖለቲካ  የሰከረው ወያኔ-ትግሬ ለመስፋፋት ሰፊና ለም መሬት ያስፈልገዋል። በዚህ ምክንያት ከወሎና ከጎንደር ከ50 ሼህ ስኬዎር ኬሎ ሚትር መሬት በላይ ቆርሶ ወደ ትግራይ አጥፎአል።
ይኸም ብቻ ሳይሆን በመሬቱ ላይ አምስት መቶ ሺህ ትግሬ አስፍሮ ሴቶችን በግዳጅ በመሃይም ትግሬ  በማሥደፈር ጭምር፤ አማራውን አጥፍቶ አገሩን በትግሬ አስወርሮታል። እነ እስየ አብርሃምም ይኼንኑ ወንጀል ደግፈው ወደፊት አገሩ የጎንደር ወይስ የትግሬ የሚል ሙግት ቢነሳ፤ በሪፈረንደም ሊወስን እንደሚገባው አሽፈውብናል። የዚህ ቀንደኛው ወንጀለኛ መሃንዲስ ስብሃት ነጋ ነው።
2ኛ፤ አማራው በአብዛኛው የሰፈረበት አገር ውሃ ያለበት ነው። ይኸም ብቻ አይደለም፤ የጣና ባሕር የሚገኘው እዛው ጎጃም ነው። ይኸንንም ትልቅ ሃብት ወያኔ-ትግሬ በደርግ ግዜ በሳሊኒ በመሰራት ላይ የነበረውና ለአገረኛው ጠቃሚ ሊሆን የሚችሉ ግብአቶችን ሰርዞና ነቃቅሎ፤ ዛሬ እነሆ ለራሱ የገቢ ምንጭ ሊያስገኝ በሚችል የሕዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ቀርጾ የኤሌክትሪክ ኃይል ለማመንጨት አገረኛውን በቦንድ ግዤ ፈጥርቆ በመያዝ እያሰቃየ፤ በዴያስጶራው ደግሞ ለልመና ሲመጣ ውርደትን እየተቀለበ ይገኛል። ይኼን የውሃ ሃብት የራሴ የኔ ነው! የሚል የጎጃሜ ተቃዋውሞ ወያኔ እንኩዋን በውኑ በህልሙ ማለም አይፈልግም። ስለዚህ አማራ በዚህ ምክንያትም መጥፋት አለበት በወያኔ-ትግሬ አመለካከት።
3ኛ፤ አማራ ከትግሬም ሆነ ከማንኛውም ኢትዮጵያዊ ጋር በሰላምና በፍቅር እንጂ በባርነት አልገዛም ብሎ የተነሳ እለት፤ ዛሬ በቅድሚያ አማራ ብሎ ራሱ ወያኔ የከለለውን አገር ከትግሬ ነጻ ለማድረግ እንደሚገደድ ወያኔ- ትግሬ ጠንቅቆ ያውቃል። በሌላ አነጋገር እንዲህ ማለት ይጀመራል፤
- የአማራ ነጋዴ ትግራይ አለ እንዴ? የለም። ታዲያ የትግሬ ነጋዴ አማራ አገር ምን ያደርጋል? - የአማራ ግንበኛ ትግራይ አለ እንዴ? የለም። ታዲያ የትግሬው አማራ አገር ምን ይደርጋል? - - የአማራ አራሽ ትግሬ አለ እንዴ? የለም። ታዲያ የትግሬ አራሽ በአማራ ምን ያደርጋል?
- አማሮች በትግሬ ምን አላቸው? ሆቴል? ፋብሪካ? መሬት? ቪላ? ምንም። ታዲያ ትግሬዎች በዓማራ አገር ለምን የእነዚህ ሁሉ ባለቤት ይሆናሉ? የዚህ መልሱ፤ አማራ ተደራጅቶ ራሱን ማስከበር ባለመቻሉ ብቻ ነው።
ነገርግን፤ እነዚህንና የመሳሰሉ ጥያቄዎችን አማራ እንደኔ የሆዴን በማውጣት ሳይሆን፤ በነፍጥ አስደግፎ መናገርና ማናገር ሲጀምር፤ የወያኔ ትግሬ እግር ከተከዜ እንደማያልፍ ሳይታለም የተፈታ ነው። ስለዚህ በዚህ ሊከሰት በሚችል ከፍተኛ አደጋ አሁንም ወያኔ-ትግሬ አማራውን ማጥፋት ዘለቄታ ጥቅሙን ለማስጠበቅ ሁነኛ ተግባር አድርጎ መስራቱ በፍጹም ሊያስደንቀን አይገባም።
በእንደዚህ አይነት ዘመን ስንኖር እውነት ለመናገር መድፈር የግድ ነው። አንዴ ነው የሚኖረው። ዓማራው ወገናችንም እራሱን እንደሚታደግ ጥርጥር የለንም። ከዚህም ከዚያም አደግዳጌ ሁሉ! ጥላቻ እያልክ አንቡዋትር። አልነጋ መስሎአት በቁዋት አራ. ይባል ነበር።
ዓማራ ሆይ! እቅጩን ልንገርህ! ወያኔ-ትግሬን ከአገርህ ካላስወጣህ ማለቅህን እወቀው!!
አንተ ህሊና-ቢስ አንት ወያኔ-ትግሬ!
ሳይመሽብህ ውጣ፤
ከጎጃም አገሬ !
ከጎንደር አገሬ !
ከወሎም አገሬ!
ሳይመሽብህ ውጣ ከሸዋም አገሬ!







   








Comments

Popular posts from this blog

የፋኖ አንድነት እንዴት?

እስከ ስባት ትውልድ!

አሞላቃቂ ጥቅመኛ!