እስከ ስባት ትውልድ!
ልደቱ አያሌው... እስከ ሰባት ትውልድ!
ቦጋለ ካሣዬ
የፖለቲካ ውይይቶች በፖሊሲ ላይ የተመሰረቱ መሆን ቢኖርባቸውም እንደየአገሩ ልሂቃን የፖለቲካ
ባህል ይዘታቸውና ቃናቸው ይለያያሉ፡፡
ኢታሊያዊው ፋውስቶ በርቲኖቲ እንደ ልደቱ አያሌው የመናገር ችሎታ ካላቸው ፖለቲከኞች አንዱ
ነው፡፡ማህበራዊ ፍትህ ለኢታሊያ ህዝብ ብቻ ሳይሆን ለአለም ህዝብ ሁሉ የሚመኝ ሃቀኛ ሰው ነው፡፡ መሃንዲስ ነው።በሰራተኛ ማህበራት
ውስጥም መሪ ሆኖ ሰርቶአል፡፡በስሎ ነው ወደ ፖለቲካ አለም የገባው፡፡ተልእኮው የካቲታሊዝምን ያልተገራ የሃብት ቅንቅን ማጋለጥ እንጂ
የካቢኔ ሹመት አይደለም፡፡ የሚናገረው ሁሉ እውነት ስለሆነ ማንም አጭበርባሪ ኢታሊያዊ ፖለቲከኛ ይሁን አድርባይ ምሁር ከእርሱ ጋር
በአደባባይ ለመወያየት አይደፍርም፡፡ራእይና እውነት ያለው ሰው ነው፡፡ “la Citta’ degli uomini”/2007 (የወንዶች ከተማ) የሚል መጽሃፉ ተደጋግሞ ቢነበብ አይሰለችም። የአብይ አህመድ የመደመር
ዝባዝንኬን ግን ገልጦ 30 ገጽ መድረስ ትልቅ አቀበት ነው።
ሌላ የማውቀው የልደቱ ተመሳሳይ የንግግር ችሎታ ያለው ሰው የዳቹ ያን ማርያኒሰን ነው፡፡ እርሱም
የማህበራዊ ፍትህ ጠበቃ ነው፡፡ የሰሜን አትላንቲክ ትብብርን አጥብቆ የሚያወግዝና እንዲሁ እንደ በርቲኖቲ የካፒታሊዝም ቅንቅን የሚራገፍበት
አለም ማየት ነው ምኞቱ፡፡ ያን ራሱን በንባብና በልምድ ያዳበረ ሰው ነው፡፡ ውሸት አይወድም፡፡
ልደቱ አያሌው
ልደቱ አያሌው በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ የተከሰተው በጉርምስና እድሜው ከመኪና ንግድ ውጭ ምንም
የስራም ሆነ የትምህርት ዝግጅት ሳያደርግ የመላው ዐማራ ሕዝብ ድርጅት(መዐሕድ) በ1984
ሲመሰረት ነው።የወጣቱ ክንፍ ውስጥ ነበር የሚሰራው፡፡ልደቱ እንደ በርቲኖቲና ያን ከእውነት ጋር የተጋባ ሳይሆን የተፋታ ነው፡፡
ጥቂቶቹን...
1.በቀደም ከዶ/ር መሳይ ከበደ ጋር ሲወያይ፤ በ1984 የተመሰረተው የመላው ዐማራ ሕዝብ ድርጅት(መዐሕድ)፤ የፖለቲካ ድርጅት አይደለም ብሎ ውሽት ሲናገር ትንሽም ስቅጥት አላለው፡፡ ይሁን እንጂ የመዐሕድ መስራች ቀዳማዊ ስብሰባዎች ሁሉ የሚያሳዩት በኢትዮጵያ ስም የሚንቀሳቀስ የፖለቲካ ድርጅት ለመመስረት ስም መረጣ ላይ እንደነበር ነው፡፡ የፖለቲካ ፕሮግራሙም፤ አላማና የአስራር ስልጣን፣ስለ መንግስት አመሰራረት፣ስለ ፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ስለ ጎሳ ንቅናቄዎችና ስለ ዜጎች ስብአዊ መብቶች፣ ስለ ኢኮኖሚ፣ ማህበራዊ ኑሮና ባህል እንዲሁም ስለ የአገሪቱ የመከላከያና የውጭ ፖሊስን ያካተቱ ነበሩ፡፡ ይሁን እንጂ የድርጅቱ ስያሜ ሳይወጣ በፊት በወያኔና በኦነግ በአማራው ላይ የሚደረገው የዘር ጭፍጨፋ ስለተጠናከረ፤ የተሰናዳውን የፖለቲካ ፕሮግራም ይዞ መዐሕድ ተመሰረተ፡፡ መዐሕድ አመሰራረቱ ሁሉም ዜጎች የተሳተፉበት ሲሆን ቅርጹ በወቅታዊ ሁኔታ አማራ ይሁን እንጂ ይዘቱ ነገድን የተሻገረ ነበር። የአማራነት ቅርጽንም ይዞ በኢትዮጵያ አንድነትና በልጆቹዋ እኩልነት የሚያምኑ የሁሉም ነገዳት አባላት ድጋፍ የነበረው የፖለቲካ ድርጅት ነበር::
2.ልደቱ ከዚሁ ከዶ/ር መሳይ ከበደ ጋር ሲወያይ፤ እርሱ የሚቃወመው የጎሳ ብሄረተኝነት ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያን አክራሪ ብሄረተኝነት ነው ሲል ደግሞ ተደምጦአል።ይሁን እንጂ በድርጅት ይሁን በግለሰብ አክራሪ የኢትዮጵያ ብሄረተኝነት የተንፀባረቀበትን ምሳሌ አይጠቅስም። ጉዳዪን ለሚያውቅ ሰው ግን አክራሪ የኢትዮጵያ ብሄረተኝነት የሚለው ከልደቱ የኢዴፓ ምስረታ ጋር የተያያዘ ነው። እንደሚታወቀው የልደቱ ኢዴፓ የተመሰረተው መዐሕድን በመናድ ወይም አማራውን በማዳከም መሆኑ መረሳት የለበትም። ለዚህም ነው መዐሕድን አዳከምክ እንዳይባልም መዐሕድ የፖለቲካ ድርጅት አይደለም ሲል እንደ ልማዱ የሚክደው። ልደቱ የመዐሕድን ወጣት ክንፍ ገንጥሎ የፖለቲካ ድርጅት ለማቁዋቁዋም መጀመሪያ ምክር የጠየቀው በጎሳ ፖለቲካ የሚያምነውን ዶ/ር በየነ ጵጥሮስን ነበር። የልደቱ ኢዴፓ የጎሳና አክራሪ ያልሆኑ ኢትዮጵያዊ ብሄረተኞች ስብስብ ነበር ማለት ነው።ይኼም ብዙም ከወያኔና ከኦነግ ፈቀቅ ያላለ የብሄር ጭቆናን ትርክት በአማራው ላይ አሳባቢና አጭበርበሪ ተልእኮ ያለው አካሄድ ነው። ልደቱ አማራ ጨቁዋኝ ነበር ብሎ ከሚያምኑት ጎራ የሚመደብ ነው።
3.ልደቱ ኢዴፓን ከመሰረተ በሁዋላ ከመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት(መኢአድ) ጋር ህብረት
ወይም ውህደት ለመፍጠር በሚደረግበት ወቅት አምስተርዳም መጥቶ እርሱ እንግዳ የሆነበት ህዝባዊ ስብሰባ ተካሄዶ ነበር። ኢዴፓ በአዲስ
አበባና በአንዳንድ ከተሞች ከመንቀሳቀስ ውጭ እንደ መኢአድ ሰፊ ህዝባዊ መሰረት አልበረውም።ስለዚህ ውህደቱ እንዲጠናቀቅ የተሰራው
ስሌት አንድ ለአስራ ስምንት(1:18) ነበር። ልደቱ ግን አሻፈረኝ! ተደፈርኩ ብሎ ኢንጂነር ኃይሉ ሻውል ላይ የስም ማጥፋት ዘመቻ
ጀመረ። በቁጥር እንዴት ይታፈራል? ልክ እንደ ዛሬው ዘመነ ካሴ መሆኑ ነው። ዋናው ጉዳይ ግን የልደቱ አካኪ ዘራፍነት ውህደቱ እንዳይፈፀም
የማድረግ ተልእኮውን ለመሸፈን ነበር።ያሳዘነኝ ነገር ግን ኢትዮጵያም ሆነ አፍሪካ እንደ ኢንጂነር ኃይሉ ሻውል ያሉ ብዙ ሰዎች የሉዋቸውም፡፡በጣም የስራ ልምድና ትምህርት ያካባቱ ናቸው። መከበርና መደመጥ ሲገባቸው የአማራ ጠላቶች እንደ ልደቱ ያሉ ተጋላቢ ጥቅመኞችን በማሰማራት
ሎሬት ፀጋዮ ገብረመድህን እንዳለው፤ “ጥሩ ፋሬ ገዳዮች”ን ልከው የዝርጠጣና የዘለፋ ፕሮፓጋንዳ ያካሂዱባቸዋል። አሊ ማዝሩዊ እንደ ልደቱ ያሉትን
ስልጣን ለመያዝ ምንም የማያቆማቸውን ሰዎች፤ የቦዘኔ ታጋዮች(Lumpen
Militante) ብሎ ይጠራቸዋል።
4.ልደቱ በቅንጅት የምርጫ ሂደት ማገባደጃ ላይ ጠፍቶ ነበር። ይሁን እንጂ እርሱ ባላዘጋጀው
ሰላማዊ ሰልፉ ላይ ድንገት ተከስቶ በመኪና መንጋውን ሲንጠው ታየ። ቀጥሎም በጠመንጃ የተነጠቀውን የምርጫ ውጤት ተቀብሎ የወያኔን
ፓርላማ ሊያዳምቅና ደመወዙን ሊበላ ገባ። እስከ ዛሬ ድረስ ልደቱ አያሌው በምርጫው ቅንጅት ማሸነፉን አይቀበልም። የአውሮፓ ታዛቢዋን
አና ጎመዝን ሁለቴ ለማግኘት እድል ነበረኝ። የምርጫው ውጤት ምንም ጥርጥር አልነበረውም። ቅንጀት አሸንፎአል።
5.ልደቱ አያሌው ወያኔ መጥፋት ያለበት የፖለቲካ ድርጅት ነው ሲባል፤ መልሱ ይኼማ የዘር
ፍጅት ነው የሚል ጥምዘዛ ነው። ስለ ድርጅት መጥፋት አስተያየት ስጥ ሲባል ድርጅቱን ከሕዝብ ነጥሎ ለማየት አይፈልግም። ለወያኔ
ሥስ ልብ አለው የሚባለው ካለነገር አይደለም። ልደቱ አያሌው አማራው በተለይ በወልቃይት የተደረገበትን ስልታዊ የዘር ማጥፋት ድርጊት እያወቀ፤
እስከዛሬ ድረስ በወልቃይት ባለቤትነት ወያኔ የሚያንሳውን ጥያቄ አድበስብሶ ነው የሚያልፈው፡፡
በመጨረሻም
ሰሞኑን ደግሞ ልደቱ አያሌው መነጋገሪያ በመሆን የቱክረታችንን አቅጣጫ እያሳተው ነው፡፡ በመሰረቱ
“እስከ ስባት ትውልድ!” የሚለው ፍረጃ ከቁጭት የመነጨ ቢሆንም ሰቅጣጭ ነው።ግን ልብ ብለን ካየነው፤ እስከ ሰባት ትውልድ በሰለጠኑት
አገሮችም በስራ ላይ ይውላል። በአገርና በህዝብ ክህደቶች እንዲሁም በሌሎች ከፍተኛ ወንጀሎች የተነከሩ ሰዎችና ዘመዶቻቸው ለሁነኛ
የመንግስት ሃላፊነት አይታጩም። ይጣራል ስር መሰረታቸው። ስለዚህ ይኼን የፕሮፌሰር ሃብታሙን የቁጭት ንግግር ከአውዱ በጣም አውጥቶ
መለጠጥና በዚህ ጊዜ ማጥፋት ይሁን ፕሮፌሰሩን የማሪያም ጠላት ማድረግ መቆም አለበት።ልደቱ ፕሮፌሰሩን በግሉ ሊከስ ይችላል። አማራ
እንዳይደራጅ አሽከር ሆኖ ከ30 አመት በላይ ለአማራ ጠላቶች ያገለገለ ጌኛ ተነካ ተብሎ በፕሮፌሰሩ ላይ መረባረብ የጠላት መሳሪያ
መሆን ነው። አማራው እንዲህ ያሉ ነገሮች ላይ ሳይሆን ዛሬ አትኩሮቱን ማድረግ ያለበት በሃቀኛው እስክንድር ነጋ የሚመራውን የአማራ
ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅትና ሌሎቹ ሃቀኛ ፋኖዎች አብረው እየታገሉ የአማራው ሰቆቃ የሚወገድበትን ወቅት የማሳጠር ነው።ልደቱ ራሱ እንዳለው
የከሸፈ ፖለቲከኛ ነው። የግል ጉዳዩን ራሱ ይወጣ።
ወንድማችን ቦጋለ ካሳዬ ስለ ልደቱ አያሌው የፓለቲካ ነጋዴነት እካሄድና ከዚሁ ጋር አስታከህ ያጋራኽን የአማራውን ብሎም የኢትዮጵያ ጠላቶች ጥቃትና ቅን ብራቸው ወቅታዌና ትልቅ ትምህርት ነው እላለሁ። እውነቱን በግልፅና በሚጣፍጥ ቅዋንቅዋ እስቀምጠኽዋል። እግዜር ይስጥህ። ስለ እስክንድርም ያቀርከብከው ጉዳይ እንደዚሁ እሱነቱንና ቤተሰቡን ለአማራ ህልውና ማስጠበቅ በማሰብ ሲል እራሱን ለአደጋ አጋልጦ፣ ቤተሰቡን ትቶ ሜዳ መውረዱን በሚገርም ሁኔታ እንዳንዶች ማላገጫ እድርገውታል። ከናካቴው ፋኖ እይደለም፣ ስርጎገብ ነው እስከ ማለትም ተደርሷል።እግዜር ትርዳን።
ReplyDeleteወንድሜ ስለሺ፤ ዝም ማለት የለብንም። ቆማጣን ቆማጣ ካላሉት ገብቶ መፈትፈቱን አይተውም። የእውነት አምላክ ይረዳናል።
Deleteልደቱን በጥሩ መንገድ ቢገልፁትም የኢንጅነር ሀይሉ ሸዋልን አማራን የጎዳ መሰሪ አካሄድን በሚገባ መገለፅ አለበት ምክንያቱም ፕሮፌሰር አስራት መዐሕድን የመሰረቱት የአማራን የዘር ጭፍጨፋን ለመመከት በመሆኑ በወቅቱ እነእስክንድ ነጋ መዐህድ መፍረስ የለበትም ብለው ቢታገሉም ኢንጅነሩ አማራን በአማራነቱ እንዳይደራጅ እንዲሁም የአማራ ጭፍጨፋ የኢትዮጵያውያን ግጭት በሚል እስከ ቅርብ ጊዜ አማራ ተጨፈጨፈ አትበሉ ይበልጥ ታጋጩታላችሁ በሚል ሰበብ ለወያኔ አገዛዝ የሚችን መንገድ ሲከተሉ የነበሩ መሆናቸው መነገር አለበት።
ReplyDelete