‘ጄኔራል’ ወያኔ፤ በአማራ ጥላ መደንበር እስከመቼ?

“ስምና ቁንጫ ባዶ ቤት ይወዳል” ይሉ ነበር አበው። ካለነገር አይደለም።
የወያኔ-ትግሬ ሰራዊት በቁጩ(fake) ጄኔራሎች የሚመራ ነው። አብዛኞቹ መደበኛ የሚሊትሪ ሳይንስ የተከታተሉና ልምድ ያላቸው አይደሉም። ስብሃት ነጋና መለስ ዜናዊ የሾሙዋቸው ተጋዳላይዎች ናቸው። ልምዳቸውና ጀብዱዋቸው ያው አማራ ገዳይ! እያሉ መፎከርና ደርግን አሸነፍን! እያሉ ለ23 ዓመታት የቀጠለው አደንቁሮታቸው ነው። እንደ እውነቱ ከሆነ ደርግ ራሱን በራሱና በቀዝቃዛው ጦርነት ማክትም ምክንያት፤ ርዳታ ለማግኘት ባለመቻሉ፣ እንዲሁም አሜሪካኖችም መንግስቱ ከስልጣን እንዲወርድ ስለፈለጉና ስለሰሩ ነው የወደቀው። ደርግ እንኩዋንም ወደቀ።

እሺ… ወያኔ-ትግሬ ደርግን አሸንፈሃል ብለን እስኪ ሃራይ! ሃራይ! ሐቂ እዩ!! እንበልለት፤ ከበሮ እየደለቅን… ደስ እንዲለው። ታዲያ የወያኔ-ትግሬ ጄኔራሎቹ ቁጩ ካልሆኑ፤ ለምን በሰራዊቱ ውስጥ ከ62 ጄኔራሎች ውስጥ 57ቱ ትግሬዎች ሆኑ? ቁጩ ካልሆኑ እኮ በሰራዊቱ ውስጥ ለምሳሌ ከ62ቱ  30 ተጋሩዎችንም ቁልፍ የሰራዊቱን ስልጣን አስይዞ የዘር መድሎውን ስርዓት ለማስቀጠል ይቻል ነበር። ይኼ ግን ሲሆን ለምን አናይም? በተለይ ወያኔ ትግሬ ለምን በሰራዊቱ ውስጥ ለወሬ ነጋሪ አንድ አማራ ጄኔራል ቢኖር ከስልጣን ያባርረዋል? ያውም ይኼም ጄኔራል ከወያኔ-ትግሬዎች የተለየ ትምህርትና ልምድ እንዳለው የሚታወቅ ነገር የለም። ነገሩ ግልጽ ነው። ወያኔ-ትግሬ ከዐማራ ሕዝብ ሆነ ከተቀረው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር የማይታረቅ ቅራኔ ውስጥ ስለገባ በፍርሃት እየጠንቀጠቀጠ ነው። ይኽ ሁሉ የፍርሃቱ ነጸብራቅ ነው።
ዓማራን በተለይ እርቦት በአጎረሰው እጁን ነክሶታል። መሬቱን መሬቴ ነው ብሎ ነዋሪውን እያተገረው ይገኛል። ያፈናቅለዋል። ያመክንዋል። በበሽታ ይመርዘዋል። አማራን መግደል የተለመደ እንዲሆን አድርጉዋል። ዛሬ አማራ ሲገደል ማንም አይጮኸም። በቅርቡ መኢአድ ባወጣው መግለጫ እንኩዋን ወያኔ-ትግሬ አርባ አማራ ገድሎአል። ኩላሊታቸውን እንደ ሻእቢያዎች ይሸጠዋል የሚል ስጋት አለኝ። ምክንያቱም ወያኔ-ትግሬ በምንም መንገድ የተገኘን ገንዘብ መልቀም ነውና የሚፈልገው።

አማራውንም ሆነ የተቀረውን የኢትዮጵያ ሕዝብ በክትባት፣ በእንክብል፣ በኤድስ፣በርሃብ፣በማፈናቀል፣በማሰደድና በመጨፍጨፍ ወያኔ-ትግሬ የማይታረቅ ቅራኔ ውስጥ ስለገባ ከራሱ ጎሳ ሌላ የሚያምነው የቁጩም ቢሆን ጄኔራል የለም።
የወያኔ-ትግሬ ኢታ ማጆር ሹሙ 10ኛን ክፍል እንኩዋን ያልጨረስ አድማሰ ጠባብ ነው። ይህቺ አገር እኮ በተለይ የውጭ ጠላቶቹዋ እንደ እሳት እየጋዩ ባይሆን ኖሮ፤ ስላም ኖሮአቸው ሊወሩዋት ቢከጅሉ ያሁኖቹ ጄኔራሎች የአህያ ባል ከጅብ አይስጥልም አይነቶች ናቸው። ብቁ ዝግጅት የላቸውም አንድ ሰራዊትን ለማወጋት። አካላዊ ብቃታቸው ሳይቀር አሳፋሪ ነው። በክትፎና በቢራ ያረገዘው ሆዳቸው ቱር ከጠገቡ የወጥ ቤት ሰራተኞች አይለያቸውም።

የሚገርመኝ፤ አንድ ያውም ወያኔን ያገለገለ አማራ እንዲህ ወያኔን የሚያስፈራና የሚንቦቀቡቅ ከሆነ፤ እውነተኛው አማራ የተነሳ እለት ቡኬው ወያኔ ምን ይውጠው ይሆን? አዎ ወያኔ ቡኬ(ፈሪ) ነው። ለነገሩ አማራን ወይኔ ሊያምነውም አይገባም። ታዲያ አንድን አማራ ጄኔራል እንኩዋን መቆጣጠር አቅቶት፤ ባገለው ይሻለኛል ብሎ የተብረከረከው በሌላ ምክንያት አይደለም። ቡኬ በመሆኑና ጄኔራሎቹም የቁጩ ስለሆኑ ነው።
ለዚህ ነው ቁጩ ጄኔራሎች ሌላው ቀርቶ ድንጋይ ያልወረወረን የአዲስ አበባና የአምቦ ተማሪዎችንና ሌሎችንም በጥይት ያስቆሉት።
ለነገሩ መንግስቱ ሃይለማሪያምም እንደ ወያኔም ባይሆን ቡኬ ነበር። ለዛም ነው፤ በራሳቸው የሚተማመኑትንና ይበልጡኛል ይላቸው የነበሩትን ጄኔራሎች፤ ጎሳ ሳይለይ ያጠፋቸው። መለስ ዜናዊማ ሜዳም እያለ ጥይት ሳይመታው፤ በጩኸቱ ብቻ የተመታ መስሎት መውደቁን እናውቃለን። በጣም ፈሪ ስለነበር፤ ለስልጣንም ያቀረበው አደገኛ ያልሆኑትን እንደ ዩኑስ ያለ አሽከርና አድማሰ ጠባብ ነው።
ጦቢያ በአርበኞች መንፈሰ፣ በሕዝባዊ ይሁንታና በሕግ የሚተዳደር አስተዳደር ትፈልጋለች። መሃፀኑዋ ባንዳ እንደወለደ ሁሉ ጀግናም ወልዶአል። የቁጩ ጄኔራሎች ስብስብ እንደ እንሳሳት ክለብ ነው። እርሱ በእርሱ ይተሻሽ። ከነተረቱስ? አህያ ቢራገጥ ጥርስ አይሳበርም ይባል የል? የአማራ ነገር ይገርመኛል። ገና ሳይነሳ ጥላው እንዲህ ያሸብራል? ሲነሳ ምን ሊኮን ይሆን? ጦቢያ ሆይ! መላ በል!!

Comments

Popular posts from this blog

የፋኖ አንድነት እንዴት?

እስከ ስባት ትውልድ!

አሞላቃቂ ጥቅመኛ!