ትዝብት፤ዮንግ ፖለቲከኞች! (ቦጋለ ካሣዬ/ አምስተርዳም)
ለፖለቲካ ስልጣን ጉጉ የሆኑ ግለሰቦች ስልጣን የሚጨብጡበት ሂደት እንደየአገሩ አደረጃጀት ይለያያል። የኔዘርላንድስ ፖለቲከኞች ስልጣን የሚጨብጡት፤ ከከፍተኛ የትምህርት ተቁዋማት ተመርቀው በልዩ ልዩ የስራ ዘርፎች ልምድና እውቀት ካካበቱ በሁዋላ ነው። ብዙዎቹ የፖለቲካ ፓርቲዎች የራሳቸው የጥናትና የምርምር ተቁዋማት ስለአሉዋቸው፤ አባላቶቻቸው ጥናቶች፣ውይይቶች፣ሌሎች ስራዎችን እንዲሰሩ ሁኔታዎች ተደላድለውላቸዋል።
እነዚህ የፓርቲ ተቁዋማትም ከዩኒቨርሲቲዎች፣ከንግድ፣ከጦር ሃይል፣ከደህነት፣ከጤና፣ከሰራተኛና ስራ ቀጣሪዎች ድርጅቶች ወዘተርፈ ጋር አብረው ይሰራሉ። ይህ ሁሉ ነገር ስለተመቻቸላቸው፣ ጉጉ የወደፊት ፖለቲከኞች ዝንባሌያቸው ወደ አደላው ዘርፍ ፤ሕግ፣ የውጭ ጉዳይ፣ ፋይናስ፣ስራአጥነትን ቅነሳና፣ ስራ ፈጠራን፣ንግድ፣ ፀጥታ፣ ጤና፣ እርሻና እትህ፣ ሃይል፣ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ወዘተ በተመለከተ የጠለቀ እውቀትና የስራ ልምድ ያካብታሉ። ከዚህም በሁዋላ ነው የፖለቲካ ስልጣን ለመያዝ በፓርቲያቸው አማካይነት ወይም በግላቸው ወደ ሕዝብ ፊት ቀርበው ሃሳባቸውን አስረድተው የሕዝብ ይሁንታ የሚጠይቁት።
የከፍተኛ ትምህርት ለመከታተል የሚታክታቸው ለፖለቲካ ጉጉ የሆኑ ግለሰቦችም አሉ። ለምሳሌ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የሶሺያሊስት ፓርቲ ሊቀመንበር የነበረው ሰውዬ በመደበኛ ትምህርት ብዙ የገፋ አልነበረም። ይሁን እንጂ ብዙ በማንበብ፣በመከራከርና በስራ ልምድ እውቀቱን አዳብሮ የፓርቲው ሊቀመንበር በመሆን ፓርቲውን የተከበረ ለማድረግ በቅቶአል።
እንግዲህ ስልጣን የመያዝ ጉጉት የሚያድርባቸው የሰከነ አገር የሚኖሩ ፖለቲከኞች መጀመሪያ ከፍተኛ መስናዶ ያደርጋሉ፤ ከዚያም ስልጣን ይዘው እንዴት አገሬን ልጥቀም? እንዴት የተሻለች ላድርጋት? በሚል ተጨንቀው ተጠበው ለአገራቸው አመርቂ ስራ ለመስራት ይጥራሉ። በማንኛውም አገራዊ ጉዳይ ላይ በረጋ መንፈሥ፤ጉዳቱና ጥቅሙ ተመዛዝኖ፣ተተንትኖ ነው ስምምነትና ውሳኔ ላይ የሚደረሰው። የተረጋጋ አገር ውስጥ በደመነፍስና በእልህ የሚካሄድ የፖለቲካ ውሳኔ የለም። የጠላቴ ጠላት ወዳጅ ነው የሚለው አባዜ እዚህ አገር አይታወቅም።
ታዲያ በዝርክሩኩዋ ኢትዮጵያ ጉጉ ፖለቲከኞች እንዴት ነው ስልጣን ላይ ጉብ የሚሉት? የሚለውን ለመዳሰስ አንድ ገጽ ይቅርና አንድ መስመርም አይፈጅ። “በሕገ አራዊት”፤ በነፍጥ ነው። አለቀ። ደቀቀ።
***
ዛሬ በሬዲዮና ቴሌቪዚን፣ጋዜጦች፣ በዘመናዊ የማሕበራዊ መድረኮች ተቃዋሚዎች በግለሰብም ሆነ በድርጅታቸው፤ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የሚሰጡዋቸው ብዙ አስተያየቶች አሉ። እነዚህን አስተያየቶች፤እያጠናና እየፈተሸ ለሕዝብ ውይይት መልሶ የሚያቀርብ በሙያ የዳበረ ይቅር ገና ለመጀመር የሚያስብ የድርጅቶችም ሆነ ነጻ የሆነ የሙያተኞች ተቁዋም የለም። ለምሳሌ በኢትዮጵያ እንደ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ያሉ የትምህርት ተቁዋማት ነጻነት ቢኖራቸው ኑሮ፤ በልዩ ልዩ የአገሪቱ ጉዳዮች ላይ የሃሳብ መዳበር፣ጥራትና መንሸራሸር እንዲኖር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ሊያደርጉ ይገባ ነበር። ስርአቱ ይሄን ስለማይፈቅድ ፖለቲካ ሙያ-ቀመስ ሆኖ የሃሳብ ፍትጊያ እንዳይደረግበት ትልቅ ደንቃር ፈጥሮአል። በሌላ ጎኑ ይህ ሁኔታ ድርጅት አቁዋቁሞ የፖለቲካ ስልጣን መያዝ አለብኝ ለሚል ስብሰብ ሁሉ አመቺ የመጋለቢያ ሜዳ ፈጥሮአል። የፖለቲካ መሪዎች የሚያራምዱት አቁዋም በጀሌዎቻቸው ተቀባይነት ሲያገኝ በሙያተኞች ሳይፈተሽ የመታገያ ሃሳብ ይሆናል። “ተፈጥሮን በቁጥጥራችን ስር እናንደርጋለን፣ አረንጉዋዴው አብዮት ይፋፋም” የሚሉት የኮሎኔል መንግስቱ ሃይለማሪያም መፈክሮች ክፍትን ባያስተላልፉም እንዴት በተግባር ይተርጎሙ? ሲባል፤ ከበቀቀን ካድሬዎቻቸው ጋር ትልቅ ፍጥጫ ውስጥ ይገባ ነበር።
የደብረዘይት እርሻ ኮሌጅ ምርምር ተነቅሎ ፎገራ ካልሄደ ተብሎ ሲወሰን፤ በስንት ክርክር ነው ፎገራ መሄዱ የምርምሩን ስራ ያስታጉለዋል እንጂ አያሻሽለውም የሚለውን አስረድቶ ደብረዘይት እንዲቀር ለማድረግ የተቻለው። ይኸን ለማስረዳት ሙያዊ ብቃት ብቻ ሳይሆን በሕይወትም ላይ ሊያስከትል የሚችለውን አደጋ አውጥቶና አውርዶ፤ ደፋር ውሳኔ ላይ መድረስን ይጠይቅ ነበር። የሕጻናት አምባ በአፈሩና በውሃው ጨዋማነት የተነሳ ለህል ስብል ማብቀያ ተስማሚ አይደለም ተብሎ ሃቁ ሲነገር፤ እነ ሻለቃ...«እባክህ ዝም በል! እህል እንኩዋንስ በትራክተር ታርሶ ድንጋይ ላይ ቢዘራም ይበቅላል» ሲሉ እንግዲህ እንደ በሬ ሽንት ወደሁዋላ እንጂ ወደፊት እየሄድን አለመሆኑን መገመት አያስቸግርም። መለስ ዜናዊም ልማታዊ መንግስት ሲል! ሕዳሴ ግድብ ሲል! ካድሬዎቹ በማግስቱ እርሱ ያለውን ማስተጋባት ነበር ስራቸው። በሰለጠነው አለም የሚኖረው የዲያስፖራ ፖለቲከኞችም ጀሌዎች አሏቸው። መሪዎቻቸው አንዳርጋቸው ጽጌና ብርሃኑ ነጋ ...«ሆይ! ሆ! ሆይ! ከሻእቢያ ጋር ሰርተን ወያኔን እንጥላለን!» ሲሉ ጀሌዎች በጣም ስሜታቸው ይነካና ዛሬውኑ ወያኔ የወደቀ ይመስላቸዋል።
***
ይኼን ትዝብት እየጣፍኩ እያለሁ አብርሃ ደስታ የሚባለው የአረና ትግራይ አባል፤ አረና የውህደት ጥያቄ ለሁሉም ፓርቲዎች ማቅረቡን በተመለከተ የጻፈውን መጣጣፍ ከfreedom4ethiopia.com ላይ በማየቴ የሚከተለውን አስተያየት በድህረ ገጽ ላይ አሰፈርኩ፤ “እንደኔ አረና መጀመሪያ ክልላዊና ጎሳዊ(ትግራይ) አደረጃጅቱን ጥሎ እውነተኛ አገራዊ ፓርቲ ከሆነ በሁውላ ነበር ለውሕደት ጥያቄ ማቅረብ የነበረበት። የጎሳ ፖለቲካ በራሱ ችግር የለውም ብሎ መናገር ቅንጦት ነው። የጎሳ ፓለቲካ ውስጣዊ ባሕሪያት ስግብግብነትና እንሣዊነት ናቸው። ኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ ጎሳዎች ስላሉ ሁሉም በጎሳቸው ስም ፓርቲ ካቁዋቁዋሙ በሚጦዘው የስልጣን ፍክክርና በሚገነትሩት የጎሳዎች መለያ ኢትዮጵያን ለማስተዳደርም ሆነ እንደ አገር ለማቆየት አይቻልም። 22 አመታትም ተመኮረ። አልሰራም። ታዲያ የማይሰራ ነገር ምን ያደርግልናል? ለምን በአንቀልባ አዝለነው እንዞራለን? ፖለቲካ ፓርቲዎች የፖለቲካ ሥልጣን ለመያዝ ነው የሚቁዋቁዋሙት። አብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብም ከጎሳ-ዘለል አደረጃጀት ውጭ ባለ አስተዳደር እንደሚጠቀም በቅንጅት ጊዜ በሰጠው ድምጹ አረጋግጦአል። መቼ ነው ታዲያ ፖለቲከኞች ከልባቸው የሕዝብን ትርታ ለማዳመጥ ፋቃደኛ የሚሆኑት? ፈራ ተባው ብዙም አይጠቅምም።” ይህ አስተያየት በhttp://freedom4ethiopian.wordpress.com/2013/11/06/23434-3/comment-page-1/#comment-3141 ለሕዝብ እንዳይደርስ ታቅቦአል። ይህ ድህረ ገጽ የግንቦት-7 ንብረት መሆኑን ባላውቅም በጣም አፍቃሪው ነው። ልብ በሉ ወያኔ ብቻ አይደለም አፋኙ!
***
ዳቾች ዮንግ ፖለቲከኛ ይላሉ። ነገሩ ልጅ ያቦካው ለራት አይበቃም ወይም የልጅ ነገር ሁለት ፍሬ አንዱ ብስል አንዱ ጥሬ እንደሚባለው ነው። ዮንግ ፖለቲከኛ በቂ ዝግጅት ያላካበተ ስልጣኑን በትክክል ሊጠቅምበት የማይችል ማለት ነው። አፈጮሌና መሰሪም ማለትም ነው። ዮንግ አምባገነን መሪዎችን ለመግለጽም ጥሩ የዲፕሎማሲ ቁዋንቁዋ ሆኖ በዳች የፖለቲካ ስነጽሁፍ ውስጥ በተደጋጋሚ ይጤናል። ለምሳሌ የኢትዮጵያ አስተዳደር ዮንግ ነው ማለት፤ አምባገነን፣ አጥፊ፣ ሃላፊነት የጎደለው፣ የማያገናዝብ፣ አርቆ የማስብና ለመሪነት ብቃት የሌለው ማለት ነው።
***
በመቀጠል በአንጋፋው ጋዜጠኛ አቶ ሙሉጌታ ሉሌና የፓልቶኩ ንጉስ አቶ ብርሃኑ ዳምጤ(አባ መላ) በቀደም ከሲሳይ አጌና ጋር፤ የግንቦት-7ንና የሻእቢያን ግንኙነቶች አስመልክቶ በሰጡት ዮንግ አስተያየቶች ላይ ትዝብቴን ላካፍላችሁ። በመጀመሪያ የአቶ ብርሃኑ ዳምጤና የአቶ ሙሉጌታ የሰላምታ ልውውጥ የሰለጠነ በመሆኑ ወድጄዋለሁ። ድሮ እንደሚተዋወቁ ከንግግራቸው መረዳት ይቻላል። አቶ ሙሉጌታ “እንኩዋን በአንድ መርከብ ላይ ለመሳፈር አበቃን” ያሉት ከልባቸው ነው።
ይኸ ነገር የሚያስታውሰን በተለይ በክፉ ጊዜ የኢትዮጵያውያንን አብሮ የመስራት ችሎታና ፍላጎት ነው። ‘አመልህን በጉያህ’ የሚለውን የምንይልክ አዋጅ ወርሰነዋል ልበል? አንዳንድ የኢትዮጵያ ጠላቶች ኢትዮጵያውያን የጋራ ጠላት ሲመጣባቸው ሳይነጋገሩ ይግባባሉ ብለው የሚሰጉት ለዚህ ይመስለኛል። ኢትዮጵያውያን ከአገራቸው ጋር ያላቸው ቁርጭት እጀግ የተወሳሰበና የጠበቀ ስለሆነ፤ በአገራቸው ላይ አደጋ ሲደቀን ሁሌ ከራሳቸው በፊት አገራቸውን አስቀድመው ስለሚያብሩ የድሮው ቁርሾአቸውን ወደ ጎን ለማድረግ በታሪክ ብዙ እንደማይቸገሩ፤በአድዋ ጦርነት፣ በቀጣዩ የኢታሊያ ወረራ፣ በሶማሊያ እንዲሁም የባርነት ተምሳሌት ሆና በቀረቺው ኤርትራ ላይ አብረው በጠላቶቻቸው ላይ ባደረሱት ክስረቶች ይታወቃሉ። አዎ ባንዳዎችም ነበሩ። ታዲያ ይኼ በየቦታው በሰበብ አስባቡ ተኩዋርፎ የተለያየው ሰው ከነዚህ ሁለት ኢትዮጵያውያን እርቅ ትልቅ ትምህርት ወስዶ በዚህ ክፉ ቀን ወደ አንድነት መጥቶ እንደ ሻእቢያ ያሉ ጠላቶቹ ያሴሩበትን ሴራ ሊበጣጥስውና ሊያመክነው ይገባል። ሻእቢያ በኢትዮጵያ አገራችን ጉዳይ ላይ ጣልቃ የመግባት ምንም መብት እንደሌለው፤ ደግሞ ደጋግሞ ማሳየት ያስፈልጋል! የሻእቢያ ቀጥተኛም ሆነ ተዘዋዋሪ ጣልቃ ገብነት አገራችንን ለማፍረስ የተጠነሰሰ ሴራ እንደሆነ፤ የኢትዮጵያ አምላክ ክብር ምስጋና ይግባውና፤ ሻእቢያ ካሰማራብን ሰላይ ተስፋዬ ገብረአብ መጋለጥና እርኩስ ስራዎቹ ትኩስና ተጨማሪ ማረጋጋጫና ትምህርት አግኝተናል። ቀደም ሲልም ቢሆን ሻእቢያ እነ ኮሎኔል ታደሰ ሙሉነህን ደገፍኩ ብሎ ቀልባችንን ሊሰቅል ቢፈልግም፤ በተጉዋዳኝ ‘ጎጃም ቡዳ’ ተብሎ ጭቆና ስለደረሰበት መገንጥል አለበት ብሎ፤ ስቲግማ የሚባል መጸሃፍ ተደርሶለት በነጻ ሲያሰራጭ የነበረው ተቃዋሚ መሳይ አጭበርባሪ የኢትዮጵያ ጠላትና የውሸት ፕሮፌሰር ሙሴ ተገኝን ቀላቅሎ ነበር። ዛሬም ኦነግን፣አብነግና ደምህትን ማሰለፉ ብቻ እንደማያዋጣ ስለገባው፤ ትናንት የኢትዮጵያ ሕዝብ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ የመረጠውን የቅንጅት ደጋፊዎች እንደማባበያ ከረሜላ ለመጠቀሚያ ቢያሰልፋቸው ለእኛ አዲስ ነገር አይደለም። በነገራችን ላይ ብርሃኑ ነጋ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በሚያስተምር ጊዜ በሻእቢያና በወያኔ ጦርነት ወያኔን መደገፉን ሻእቢያ እንደማይረሳለት መገንዘብ አለበት። በተጨማሪም በእርሱም ከፍተኛ አስተዋጽኦ በቅንጅት የተስተዋለው የሕዝብ ትርታ የሻእቢያ ትልቁ ቅዠትና ሽብር መሆኑ መጤንም አለበት።
***
የአቶ ሙሉጌታና አቶ ብርሃኑ ቃለ መጠይቅ የተሰራጨው፤ የሻእቢያው ሰላይ እንደተጋለጠና መጽሃፉም በነጻ ከታደለ በሁዋላ ቢሆንም በሁለቱ ግለሰቦች አስተያየቶች ውስጥ ግን ስለ ተስፋዬ ምንም የተነገረ ነገር የለም። እንደኔ ለምን ሻእቢያ በተስፋዬ ገብረአብ ያስልለናል? የሚለውን ያልዳሰሱት ቃለ መጠይቁን ከማድረጋቸው በፊት መረጃዎች ስላልደረሳቸው ይመስለኛል። ወይም በኢሳት ላይ ተስፋዬን መተቸት ስለማይቻል ነው። ለምን? ሻእቢያ እንዳይቆጣና ጫወታ ፈረሰ ዳቦ ተቆረሰ እንዳይል። የሆኖ ሆኖ አንድ የታዘብኩት ነገር ቢኖር ግን፤ አቶ ሙሉጌታ ኢሳት ላይ አንዴ በሲሳይ አጌና የቃሊቲው መንግስት መጽሃፍ ምረቃ ላይ ንግግር እንዲያደርጉ ተጋብዘው፣በቀደም ደግሞ አማረ አረጋዊ በሪፓርተር ላይ በጻፈው ላይ ሲተቹ፤ የሲሳይን መጽሃፍም ሆነ የአማረን ጽሁፍ እንዳላነበቡ ባይደብቁም ትችት ለመስንዘር አለመቆጠባቸው ነው።
እንዴት አንድ ሰው ባላነበበው ነገር ላይ አስተያየት መስጠት ይደፈራል? እንደው አንጋፋ ስለሆነ መብት አለው ማለት ነው? እርሱ ከሚያውቀውና ከሚገምተው ውጭ ሌላ አዲስ ክስተት በየጌዜው አይፈጠርም ማለት ነው?
ሁለቱም ግለሰቦች ግንቦት-7 የሻእቢያ ጌኛ ሆኖ የሚያደርገውን የትጥቅ ትግል ይደግፋሉ። እንደፈረደብን ድጋፋቸውንና ስጋታቸውን መሰረት ያደረጉባቸውን ምክንያቶች ከኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ በመነሳት መፈተሽ አለብን።
***
እንደ አቡነዘበሰማያት ሁለቱም የደጋገሙት ነገር፤ “በፖለቲካ ቁዋሚ ጥቅም እንጂ ቁዋሚ ወዳጅ የለም” የሚል ነው። ቁቅም እንደ ፈስ ተቆጠረች እንዲሉ ደግሞ፤ በቀዝቃዛው ጦርነት ዘመን በአፍሪካ ቀንድ በአሜሪካና በቀድሞዋ ሶቪዪት ሕብረት የተካሄደውን ጣልቃ ገብነት ይህንኑ የፖለቲካ አቡነዘበሰማያታቸውን ከሻእቢያ ጋር አብረን እንዋጋ ለሚለውም ሎጂክ ማጠናከሪያም ያደርጉታል።
ታዲያ እኮ ‘በፖለቲካ ቁዋሚ ጥቅም እንጂ ቁዋሚ ወዳጅ የለም’ ካልን፤ የሻእቢያ ቁዋሚ ጥቅም ኢትዮጵያን በተመለከተ ምንድነው? የሚለውን ደግሞ በድፍረት መመለስ ይጠበቅብናል። ለዚህም ሩቅ መሄድ አያስፈልግንም። እነሆ ከተስፋዬ የስደተኛው ማስታወሻ እንዳነበብነው፤ በአውሮፓ ሻእቢያ የሰጠው ስራ የኦሮሞ ተገንጣዮችን በደረሰባቸው ‘የአማራ ጭቆና’ እንዲቆጩና እንዲገነጠሉ መገፋፋት ነው። እነርሱም የተስፋዬን ስራ ወደውለት በመርዝ የተፈተፈተ ቂጣ ተብሎ አቶ ሙሉጌታ በሚያሳትሙት የጦቢያ መጽሄት ሳይቀር በተተቸው የቡርቃ ዝምታ ስራው ተስፋዬን በሃርለም ከተማ እስከመሸለም ደርሰዋል። የጫልቱ ገጸባሕሪም ይኽንኑ የአምቼን ተልእኮ የሚያጠናክር ነው። ተስፋዬ ገብረአብ፤ ሻእቢያ፣አሜሪካና እንግሊዝ የሚፈልጉትን የአፍሪካ ቀንድ ፌዴሬሺን እቅድ በመጽሃፉ ሲያራምድ፤ ገብሩ ታረቀኝን በመጥቀስ ሮተርዳም ከተጋበዘበት ቦታ ሄዶ… “ኢትዮጵያ የሚለውን ከፍ አድርጎ ወደ የአፍሪካ ቀንድ ኮንፌዴሬሽን ማድረግ” ይሽላል ሲል ተልኮውን ገልጾአል። እዚህ ላይ ልብ ብለን ማየት የሚገባን ነገር አለ። ኮንፌዴሬሽኑ በስራ ላይ የሚውለው ከሞላ ጎደል የዛሬዎቹ የወያኔ ክልሎች ተገንጥለው ኢትዮጵያ እንደ አገር ከጠፋች በሁዋላ መሆኑን ነው። ግንቦት-7 በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ አልደራደርም ብሎ ቢደነፋም የኢሳያስ ጌኛ እስከሆነ ድረስ በሻእቢያ መጫኛ ከመቀርቀብ ሌላ ምርጫ የለውም።
አቶ ሙሉጌታ እግዜር ይስጣቸውና ከኢሳያስ ጋር የመስራቱን አደጋም ነግረውናል። ኢሳያስ ሃሳቡን ከቀየረ ሁሉም ነገር ከንቱ ልፍት እንደሚሆን አልደበቁንም። ይሁን እንጂ ኢሳያስ የራሱ አጀንዳ እንዳለው ቢነግሩንም፤ አጀንዳ ያሉትን ነገር ግን አላብራሩም። ምናልባት በሚስጥር የተያዘውን ነገር ሊሆን ይችላል። ከሕዝብ የተደበቀ ሚስጥራዊ ውል እንዳለ ምንም ጥርጥር የለውም። አዎ! እንደኔ ከኮንፌዴሬሽኑ ትግበራ ውጭ ሌላ እርባና ያለው በምስጥር የሚያዝም ነገር የለም። እንደዛ ባይሆን ኖሮ ኢሳያስ በዜሮ ‘የኢትዮጵያን ተቃዋሚዎች’ በመርዳት የራሱን ደህንነትም አደጋ ላይ መጣልና ገንዘብም በከንቱ የሚያፈስበት ጉዳይ የለም። ይሁንና አቶ ሙሉጌታ አንጋፋነታቸውን መከታ አድርገው፤ አንድ አሲቂኝና እርስ በእርሱ የሚጋጭ አጸያፊ ነገር ተናግረዋል። ይኸም ለመስዋትነት የተዘጋጀውን ዜጋ ከሻእቢያ ጋር ሆነህ ታብብ እንደሆነ ነው እንጂ አታፈራም የምንለውን «አፋችሁን አትክፈቱ» ማለታቸው ነው። ይኼ ተራ ስድብ ምንም የፖለቲካ ፍይዳ የለውም።
ለካስ አንጋፍ ጋዜጠኛው የተሰደደው አፉ በወያኔ ስለተዘጋ አይደለም? በነጻ አገር ሆነን በአገራችን ጉዳይ አስተያየት ስንሰጥ እኛ ያልነው ሁሉ ትክክል ነው ብለን ለመመጻደቅ አይደለም። ታዲያ የመናገር መብታችንን እንዴት ‘አንጋፋው ጋዜጠኛ’ ይከልክሉናል? አሳዛኝ ነው።
***
እንግዲህ ከሻእቢያ ጋር የመስራቱ አደጋ ለኢትዮጵያ ሕላዌ ምን ያህል አደገኛ እንደሆነ፤ በአንድ በኩል ሻእቢያ ተገንጣይና ኢትዮጵያዊ ተቃዋሚዎችን በቁጥጥሩ ስር አድርጎ ማስታጠቁ፤ በሌላ በኩል ደግሞ እነ አምቼን በማሰማራት ፕሮፓጋንዳ መስራቱ ቁዋሚ ጥቅሙን፤ ማለትም ኢትዮጵያን የመበታተን ስራውን በሰከነ መንገድ እያካሄደ እንደሆነ መረጃዎች ዋይ! ዋይ! እያሉ እንደሚያስረዱን አይተናል። በተጨማሪም የሚያሳዝነው የኢትዮጵያ አይንና ጆሮ እየተባለ የሚነገርለት ኢሳት የተባለው የሬዴዮም ሆነ የቴሌቪዝን ማስራጫ ስለ ተስፋዬ ገብረአብ አንድም ነገር ለመተንፈስ አለመቻሉ ነው። ኢሳት አይንና ጆሮ ሳይሆን ጀርባ ነው የሆነው በዚህ ጉዳይ ላይ። እስካሁን ከፍ ሲል ያነሳናቸውን ነጥቦች ትሥስሮቻቸውን ልብ ካልን፤ ዛሬ የኢትዮጵያውን ተቃዋሚዎች ዋና አለቃ ኢሳያስ መሆኑን ልንክደው የማንችለው መራራ ሃቅ ሆኖ እናገኘዋለን። እንግዲህ የሻእቢያ ቁዋሚ ጥቅም እንዳልተለወጠ ካስተዋልንና ይኸም ቁዋሚ ጥቅሙ ኢትዮጵያን አጥፊ እንደሆነ ከተገነዘብን፤ ወያኔ በግንቦት ስባት ተተክቶ አዲሱ የሻእቢያ ወዳጅ ቢሆን የሻእቢያን ቁዋሚ ጥቅም ይለውጠዋልን? በጭራሽ! ግንቦት-7 ይሁን እነ ኦነግ በሻእቢያ ስር ስለሆኑና ምንም የመደራደሪያ አቅም ስለሌላቸው፤ ቁዋሚ ጥቅም እንጂ ቁዋሚ ወዳጅ የሚለው ለእነርሱ አይሰራም። ዳኛውም ተጫዋቹም ሻእቢያና ሌሎች የውጭ ጠላቶች ናቸውና። በቀዝቃዛው ጦርነት ጌዜ አሜሪካና ሶቪየት ሕብረት ያደረጉት የወዳጆች ለውጥ ዞሮ ዞሮ የጎዳው ሶማሊያንና ኢትዮጵያን ነው። እነርሱ ግን በማናቸውም ወቅት ጥቅማቸውን የማስጠበቅ አቅም አላቸው።
ኢትዮጵያ በወቅቱ በሶቪየት እርዳታ የሶማሊያን ወረራ ልትመክት የቻለችውም የዚያን ጊዜ አነሰም አደገም ኢትዮጵያዊ ብሄረተኛ አገዛዝና እንደ አየር ኃይል ያሉ ጠንካራ ተቁዋማት ስለነበራት ነው። ከዚያም ከቀዝቃዛው ጦርነት ማክተም በሁዋላ ጎርባቸው ኢትዮጵያን ለአሜሪካ አሳልፎ ስለዳረጋት፤ አሜሪካ የኢትዮጵያን ሰራዊት አፋርሶ እነሆ 22 አመታችን በወያኔ ሰራዊት እየማቀቅን እንገኛለን።
***
አባ መላ ፖለቲካም ሆነ ማንኛውም ስራ አደጋ አለው ባሉት እስማማለሁ። ይሁን እንጂ ከዚህ ባሻገር አገርን በሚያህል ጉዳይ ላይ፤ ከጠላት ጋር መስራት የሪስኩ/የአደጋው መጠን ምን ያኽል ነው? ብለው በጥልቀት አስበውበት የተናገሩት አንድም ነገር አልተደመጠም። አባመላ ማጤን የሚገባቸው፤ በግል ሕይወት እንኩዋን ቢሆን ዛሬ አንድ ሃላፊነት የሚሰማው ሰው ራሱን ሳያሸንፍ፤ ልጅ አይወልድም። ምክንያቱም ያልተመቻቸ ኑሮው የልጆቹን የወደፊት እጣ አስጊ ሊያደርገው እንደሚችል ይሰጋልና። የመጣ ይምጣ ብሎ በዘፈቀደ ልጅ ቢወልድና ማስተማር ባይችል፤ ልጆቹ ከርሱ የተሻሉ ላይሆኑ የሚችሉበት አደጋ ከፍተኛ ነው። ወደ አገር ጉዳይ ስንመጣ ደግሞ፤ ከጠላት ጋር አብሬ ስርቼ፣ አንዱን ጠላት ሽውጄ ሌላ ጠላት አጠፋለሁ ብሎ ፎክሮ ጠመንጃ ማንሳት እጅግ ከፍተኛ አደጋ አለው። ታዲያ ይኼን አደጋ ሳያጤኑ በስሜት ጭልጥ ብሎ ከመንጎድ ለምን ሌላ አማራጭ አይፈለግም? የትጥቅ ትግል ለማካሄድ ከኤርትራ ሌላ የትኛውም ጎረቤት አገር አስተማማኝ እንዳልሆነ ተደጋግሞ ይደመጣል። በሌላ በኩል ደግሞ አወጋን የሚባል ድርጅት በጎጃም እንደሚንቀስቀስ ኢሳት ራሱ እየደጋገመ እየነገረን አይደለም እንዴ? አባመላ? አባ መላ ከሻእቢያ ጋር የመስራቱ ውጤት ኢትዮጵያን በማፍረስ ቢጠናቀቅ ተጠያቂው ወያኔ መሆኑን ነግረውናል። ያልነገሩን ትልቅ ጉዳይ ግን፤ኸረ ለመሆኑ ኢትዮጵያ ከፈረሰች በሁዋላ የት ተሆኖ ነው ወያኔን በሃላፊነት መጠየቅ የሚቻለው የሚለውን ነው? የት አገር ተሆኖ? ኤርትራ ወይስ አሜሪካ ተቀምጦ? በታሪክ መዛግብት ለማለት ነው? እኛ ግን አባመላንም ቢሆን አሜሪካ እየኖሩ የኢትዮጵያን ወጣቶች በሻእቢያና በወያኔ እሳት ውስጥ እንዲማገዱ በማግባባታቸው፣የጥይት እራት እንዲሆኑ በመግፋፋታቸውና አገራችንን በመበታተናቸው፤ ልንከሳቸው ብንፈልግ አገሪቱ ከጠፋች በሁዋላ የትም ሆነን ክስ ማቅረብ እንደማንችል አስቀድመን ተገንዝበናል። በዚህም መሰረት አገራችን ዛሬ ተዳክማ ስለምትገኝና እንደ ሻእቢያ ያሉ ጠላቶቹዋም ስላደቡባት የመገነጣጠሉዋ አደጋው ከፍተኛ ስለሆነ፤በውስጥ ጉድያችን ላይ የሻእቢያን ጣልቃ ገብነት አንፈቅድም። ሻእቢያም እወቀው! ይድረስ ለሻእቢያ! ድራሽህ ይጥፋና! በሌላ በኩል ወያኔ ስልጣን ከያዘ ጀምሮ እስከዛሬ በአገር ቤት ሰላማዊ ትግል የሚያካሂዱት የፖለቲካ ሆነ የሲቪክ ድርጅቶች፤ ለአገራቸው ሕላዌ ከወያኔ የበለጠ እንደሚጨነቁ፣ እንደሚሰው፣ እንደሚታሰሩና እንደሚገፉ በየጊዜው የምናየው ነው።
‘አገር ቤት በወያኔ አገዛዝ ስር የሚታገሉ ድርጅቶች እኮ የሚነግሩን የሰላማዊ ለውጡ እንዲጋጋም ተጨባጭ አስተዋጽኦ እንድናደርግ ነው። ይኼም የሚያሳየው በአገራችን ውስጥ ያሉት ተቃዋሚዎች ኢትዮጵያ እንደ አገር እንድትቀጥል፤ ከወያኔ የበለጠ ሃላፊነት እንደሚሰማቸው የሚያረጋግጥ ነው። እነዚህ ተቃዋሚዎች ኢትዮጵያ ብትፈርስ ተጠያቂው ወያኔ ነው የሚል የአባ መላ አይነት ፍረጃ አንድም ቀን አላንጸባርቁም። በርግጥ መለስ ዜናዊም አፍራሹን የጎሳ ፖለቲካ እያራመደ ኢትዮጵያ ብትፈርስ፤ሆን ብሎ የተደረገ ስራ አድርገን መቁጠር እንደማይገባን ስብኮናል። አሽፎብናል። አባ መላም ያሉን ከመለስ ብዙ ፈቀቅ ያለ አይደለም። ከጌታ የተወሰደ አመል ቶሎ አይለቅም። ቅርብ አይደል ከሞቱ ስ? ጌዜ መውሰዱ መች ይቀራል ብለው?
ስለዚህ ዛሬ አገራችን በተወሳሰበ ችግር ውስጥ ስለምትገኝ፤ ችግሮቹዋን ለመፍታት፤ ልጆችዋ ብቻ የሚቆጣጠሩት መፍትሄ ነው መበጀት ያለበት። በስሜት ብን’ተከተክ አስተማማኝ ውጤት አናመጣም። ግንቦት-7 አገር ውስጥ መዋቅር ፈጥሮአል። ታዲያ ለምን ወደ ጠላት ጉያ ከመግባት፤ አገራዊ መዋቅሮቹን አያጠናክርም? ለምን ከአወጋን ጋር አያብርም? ከሻእቢያ ጋር ማበር ከእባብ እንቁላል እርግብ መሻት ነው። ሻእቢያ የሰላም ጸር ነው። ባርነት አፍቃሪ ነው። የአፍሪካ የነፃነት ተምሳሌት የሆነቺውን ኢትዮጵያ ለመግደል የተረጨ የቅኝ ግዛት መርዝ ነው። ግንቦት-7 አዳምጥ! ዮንግ አትሁን። በአገርህ ላይ አትቆምር። ልብ በል፤ ክፉህን ግን አልመኝም።

Comments
Post a Comment