በቃን አቦ! ጥሬውን ከብስል!
የግንቦት-7 ከሻእቢያ ጉያ መሸጎጥ ብዙ እያነጋገረ ነው። የኢሳቱ ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና በኤርትራ የፋሽት አገዛዝ ላይ ያለንን አላመኔታ ለማለዘብና የግንቦት-7 የአገር ማፍረስና አፋራሽ አጀንዳም ድጋፍ እንዳያጣ፤ እጅግ በኢትዮጵያውያን የተከበሩትን ካፒቴን ተሾመ ተንኮሉን ምስክርነት ይዞ ቀርቡዋል። እንደሚታወቀው የካፒቴኑ መጽሀፋ ሰቅጣጭ የሆነውን የወያኔን ፍሽትነትና ዘረኝነት ያጋለጠ ነው። ካፒቴኑ በዚሁ ሳምንት ከሲሳይ ጋር ባካሄዱት አጭር ቃለ መጠይቃቸው አስመራ ሲቪል አውሮፕላን ማረፊያ ጄታቸውን አሳርፈው፤ከዚያም ወደ ካናዳ በጥገኝነት ሲሄዱ የኤርትራ አገዛዝ ችግር እንዳልፈጠረባቸው መስክረዋል። ኢስያስ ይኼን ያደረገው ገና በጦርነቱ ወቅት ነው። ማንም ሰው ሊገምት እንደሚችለውም ለካፒቴኑ የተደረገው ‘ውለታ’ ሊሎች ከወያኔ ማምለጥ የሚፈልጉትን በማበረታታት ወያኔን ለማዳከም የተቀየስ ስልት መሆኑን ነው። እንኩዋን ይህችንና፤ በትጥቅ ታሪክ ዘመናቸው ወያኔም ሆነ ሻእብያ ትግል በቃኝ ያሉትን ወደ ሱዳን ድረስ ይሸኙዋቸው እንደነበር፤ በ1980ቹ ኢታሊያ አገር ተማሪ የነበርን ሰዎች እናውቃለን። አዲስ ነገር አይደለም፤ አቶ ሲሳይ።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፤ እኛ የምንለው ጉዳይ ከካፒቴኑ ምስክርነት ጋር ምንም ግንኙነት እንደሌለው ሲሳይ የሚያጣው አይመስለኝም። እኛ የምንለው፤ የትጥቅ ትግል አካሄደን ወያኔን በመጣል፤ ህዝባዊ ስርዓት እንገነባለን የሚለው ጉዳይ እውን ሊሆን የሚችለው ከሻእቢያ ጉያ ውስጥ ሆኖ አይደለም ነው። ምክንያቱም በዚህ አቅጣጫ የታገሉ እንደ አርበኞች ግንባር ያሉት እስከዛሬ ድረስ አንድ ቀበሌ እንኩዋን ማስለቀቅ ያልቻሉት በሻእቢያ የለበጣና የከፋፋይ ፖለቲካ ስለተሽመደመዱ ነው። ለምሳሌ ባለፈው እሁድ በሞረሽ የፖልቶክ ክፍል ከሻእቢያ ያመለጡ የአርበኞች ግንባር ታጋዮች እንደሰማሁት፤«ኮሎኔል ታደሰ ሙሉነህ ከውጭ አገር ወደ አስመራ ይዞአቸው የመጣቸውን ሁለት የሳተላይት ሬድዮ መገናኛዎች ሻእቢያ ካለምንም ምክንያት ወስዶበታል።» አንዳርጋቸው እባክህ ተቀበልና ተጠቅምባቸው! ...«አርበኛው የሚማርካቸውን ስናይፕሮችና ጥሩ ክላሾች ሻእቢያ እየመረጠ ወስዶአቸዋል። አርበኛው እንዲይዝ የሚፈቀድለት የከረከሰና የተጣመመ ክላሽ ብቻ ነበር።»
እንግዲህ ለምን ይኼን ያደርጋል ሻእቢያ? መሳሪያ እንደሆነ ሞልቶታል? ምክንያቱ ግልጽ ነው። ኢትዮጵያዊ የአገር ፍቅር ስሜት ያዳበሩ ቡድኖች በአዲስ አበባ ስልጣን እንዲይዙ አይፈልግም። ይኼም ካለምክንያት አይደለም። አንዴ ስልጣን ከያዙ ወይ ውሕደት አለበለዚያ ሳይውል ሳያድር አስብን አናፍጠው እንደሚነጥቁት ይረዳልና። ኢሳያስ በሽፍትነት ዘመኑ፤ ወያኔን እንደ ድርጅት ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር ሲችል ይኼን ባለማድረጉ በጣም ተጸጽቱዋል። ያለፈውን ስህተትም ለመድገም ከእንግዲህ ስለማይፈልግ በተለይ ደምሄትን በራሱ አምሳል አጠናክሮ ፈጥሮታል። በደምሄት ላይ የሚደረገው ቁጥጥርም እጅግ ከፈተኛ ነው። ለምሳሌ፤ “ከወያኔ ከድቶ ደምሄትን የተቀላቀለው ፍስሃ ሃይለማሪያም፤ከአውሮፓና ከአሜሪካ የተቃዋሚ ድርጅቶች ጋር፤ከሻእቢያ እውቂያ ውጪ ግንኙነት ሲያደርግ ስለተደረሰበት፤ በሻእቢያ ወዲያውኑ ተገድሎአል።” ሻእቢያ ቀልድ አያቅም። የርሱን ፕሮጋራም ከማስፈጸም ዝንፍ ካልክ በየደረጃውና እንደ ሁኔታው እየተከታተለ ይመነጥረሃል።
እንግዲህ አቶ ሲሳይ አጌና፤ ሽቅብ ቁልቁል ብሎ ካፒቴኑን ቃለ መጠይቅ ያደረገው ሻእቢያ እምነት የሚጣልበት ድርጅት ነው የሚለውን ከንቱ መልእክት ለማስተላለፍ ነው። ይሁን እንጂ ይኼ የተለመደ የኢሳት ጥሬውን ከብስል መቀላቀል ፕሮፓጋንዳ በኢሳት ላይ ያለንን እምነት እያሳሳ ከማምጣት ሌላ ምንም ፍይዳ አይሰጥም። የኢሳት አድማጭ ሁሉ ጀሌ እንዳልሆነ ኢሳት ቀደም ሲል ከተሰነዘሩበት ትችቶች ትምህርት ማግኘት ይገባው ነበር። ግን የፖለቲካ ተጽእኖ ስላለበት በግድ የሚታዘዘውን ከማድረግ አለመቆጠቡን እናያለን።
ለምሳሌ ቀደም ሲል ፋሲል የኔአለም በሐረርጌ ኦነግ በአማራው ላይ ያደረገውን ጭፍጨፋ ኦነግ ራሱ ሳይክድ፤ እንዳላደረገና ወንጀሉን ለማጠብ ታች ላይ በማለቱ ተገቢ ተቃውሞ ተነስቶ ነበር። በነገራችን ላይ ባለፈው እሁድ እራሱ ፋሲል የኔአለም በለንደን በመራው የኢሳት ሕዝባዊ ስብሰባ፤ የኦነጉ ተወካይ፤ ኦሮሞዎችን የኢትዮጵያ ዜጎች ሳይሆን “የኦሮሞ ዜጎች” ብሎ ነው እርፍ ያለው። በሌላ አነጋገር ለመገንጠል ያለውን ፍላጎት በጭራሽ አልሸሸገም ማለት ነው።
ይኽ ብቻ ሳይሆን፤ ደረጀ ሃብተወልድ ምንይልክን እንዴት እንደሚያየው ሲጠይቀው፤ እንደ ኦሮሞ ጨፍጫፊና ኢምፓየር መሥራች አድርጎ ነው የፈረጃቸው። የአድዋ ድልንም ባይክድ። ለመሆኑ በአድዋ ጦርነት ገበየሁ አልተሰውም? ባልቻስ አልተተኩም። ጎበና ዳጬስ የምንይልክን ዙፋን ተመኝተው ግለበጣ አልሞከረሙ? ከተያዙስ በሁውላ፤ …«ጎበናን የሚአክል ጀግና ዙፋኔን ተመኜ ብዬ አልገድለውም» ያለው አባ ዳኘው አልነበሩም? ጎበና ቀንቶአቸው በትረስልጣን ቢጨብጡ ኖሮስ? አጤ ብለው ዙፋኑ ላይ ጉብ ከማለት ማን ያግዳቸውስ ነበር? በነበር አይሆንም እንጂ ታሪክ። የኦነጉ ተናጋሪ፤ የኢትዮጵያን ህዝብ የመካከለኛው ክፍለ ዘመንን ታሪክ በጭራሽ አላነሳም። ኦሮሞ እስከ ራያና አዘቦ ድረስ በአገሩ ኢትዮጵያ እንደሚኖር አልተነሳም። የኦነጉ ሰውዬ ኢምፓየሮች ዘመናቸው ስላልሆነ መፍረስ አለባቸው ብሎናል። አስተሳሰቡ ከቁጭትና ከጥላቻ ውጭ ስላልሆነ የፖለቲካ አስተሳሰቡ በ19ኛው ክፍለ ዘመን ላይ እንደ ኢሳያስ አፈወርቂ ሁሉ ደርቆ የቀረ ነው። ከዚህም በመነሳት የምንገነዘበው፤ በራሱ በግንቦ-7ና በኦነግ ያለው የፖለቲካ ልዩነት በኢትዮጵያ ኦነግና ኦብነግ ሊያደርጉ ከሚፈልጉት ሪፈረንድም ውጭ ምንም ተቀራራቢ ነገር አለመኖሩ ነው።
አንዴ አንድ የወላይታ ተወላጅ ኢትዮጵያዊ፤ “እድሜ ለምንይልክ ከጦና ባርነት ያወጣኝ ሲሉ ተናግረው ነበር።” ይኸ አባባላቸው ምንይልክ ከትንሹ ጦና የበለጠ ትልቅ አገር ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ስለፈጠሩና እርሳቸውም በመጠቀማቸው ነው። አሊያማ ምንይልክ ጦናንስ ወግተው የለ? ያውም ጦርነቱ የዋዛ አልነበረም። አርሲም ሲዘምቱ እኮ ያሉት፤ የአርሲ ባሪያ የለኝም። እኛ ድሮሞ የአያቶቻችን ነው ብለን መጣንበት እንጂ ከግራኝ በሁዋላ የደረሰበት እንደሌለ እርሳቸውም አልዋሹም። ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ወያኔን ማስወገድ የምፈልገው አገሬ እንድኖር ስላልስቻለኝ ብሎአል። ሁላችንም እንስማማለን። ይሁን እንጂ ብርሃኑ እርሱ የሚአሽኮረምመው ኦነግም አገሩን እንዳአገሩ እንደማያይለት እንዳያስተው ነው። ታዲያ እንደዚህ ያለ መሰረታዊ ልዩነቶች ካሉ፤ ነገ ጥዋት የግንቦት-7 ጦር ከጎሳ መንጋዎች ጋር መረብን እንደተሻገረ በሻእቢያ የረቀቀ የድርጅት ስራ በኦነግና በደምሂት የማይዋጥበትና የማይደመስስበት ሁኔታ ላለመፈጠሩ ምን ዋስትና አለ? የቁጩ ግንቦት-7 መመስረት እንደሆነ ለሻእቢያ በጣም ቀላል ነገር ነው።
የሆኖ ሆኖ ይኼ የተያዘው የጦርነት መንገድ በጎ ነገሮችም ሊፈጥር ይችላል። ወያኔ በዚህ አሰላለፍ ስልጣኔን ልቀማ እችላለሁ ብሎ ከሰጋና የአሜሪካኖችን ፍቃድ ካገኘ፤ ኤርትራን በቀጥታ ወሮ ሽብርተኛውን ኢሳያስ ከጨወታ ውጭ ማድረግ ይችላል። አንድ የኢትዮጵያ ካንሰር ተወገደ ማለት ነው። እልል በይ አገሪ!! ጦርነቱ የከፍ ስለሚሆን ወያኔም መዳከሙ የሚጠበቅ ነው። አሁን በጦሩ ውስጥ ያለውን ጉምግምታም ከግንዛቤ ካስገባንና የሰላማዊ ትግሉ ተጠናክሮ ከቀጠለ የወያኔን አገዛዝ እድሜ ለማሳጠር የተመቻቸ ሁኔታ ይፈጠራል ማለት ይቻላል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፤ ባለፈው የአምስተርዳም ስብሰባ አንዳንድ ሊጤኑ የሚገባቸው ነገሮች ተነስተዋል። መለስ ዜናዊንና አንዳንድ የዛሬ የኦነግ አባላትን ዊንጌት ትምህርት ቤት በነበሩበት ጊዜ የእንግሊዝ ደህነት መልምሎ፤«ነጻ መውጣት» ከፈለጉ እርዳታ ለማድረግ ዝግጁ እንደነበር ተነግሮአል።
ኢሳያስም መጀመሪያ በቀኃሥ ጀብሃን እንዲመታ መቀጠሩ፤ ቀጥሎ አሜሪካኖች እንደመለመሉትና፤ ስልጣን ከያዘ ጀምሮም አካባቢውን እንዲህ ሲያምስ አሜሪካኖች ዝም ብለው የሚይዩትም፤ «አገሮች ሰላም እንዳያገኙ ማተራመስ ከሚለው የውጭ ፓሊሲያቸው ጋር የርሱ ድርጊትም ስላልተጋጨባቸው ነው» የሚል ነው። ይኸም አገርን ማተራመስ የሚለው የአሜሪካ የውጭ ፖሊስ በመካከለኛው ምስራቅ በተግባር መዋሉን በአይናችን የምናየው ሲሆን የዚህን የውዝልቅ ማስፍፍት ፖሊሲም ሱዛን ናዎሚ፣ በዘ ሾክ ዶክትሪን ስራዋ ማብራራትዋ በጉባኤው ግንዛቤ ተወስዶአል። ኢሳት ይኼን ከሞላ ጎዳል ቀድቶታል ግን ‘ከአቅሙ በላይ’ በመሆኑ ነው መሰለኝ አልዘገበውም።
በመጨረሻም በለንደኑ ስብሰባ ኢሳትን በሚመለከት ደረጀ ሃብተወልድን የሰጠውን መልስና ምስክርነት ሳላመሰግን አላልፍም። ደረጀ ከቤቱ ኢሳት ነጻ ሚዲያ እንዳልሆነ መጠቀሱና በፌስቡክም የግንቦት-7 ነው የሚለውን ጉዳይ ማንበቡን እንዳለ አስቀምጦ፤ እርሱ ግን በኢሳት ውስጥ “ካለምንም ተጽእኖ እንደሚሰራ” መስክሮአል። ደረጀ እውነት ነው የተናገረው። ለምን? ቢያንስ በሁለት የእንወያይ የኢሳት ፕሮግራሞች ላይ ደረጃ፤ “ የዶ/ር ብርሃኑ ንግግር በጣም እንደሚስማማው” ነገሮናል። ታዲያ እንዲህ ከሆነ ዶ/ር ብርሃኑ ለምን በአንተ ላይ ተጽእኖ ያደርግብሃል? ይሁን እንጂ ኢሳት የግንቦት-7 ነው የሚለውንም ማመንህ አንድ ርምጃ ወደፊት እንደሄድክ ያስቆጥራል። አሳዛኙ ነገር ግን፤ እንዲህ እርስ በእርስ የሚቃረን አስተያየትና መግለጫ ስንሰማ፤ አርቲስት ታማኝ በእስራኤል ስለ ኢሳት ባለቤትነት በቅርቡ ያደረገው ንግግር ውሽት እንደሆነ ራሳችሁ ሳታውቁት ማጋለጣችሁ ነው። ኢሳት ይፈረስ ያለ የለም። ሙሉ ነጻነት ከሌለው ግን ወሳኝ መረጃዎችን ሊያቀብል አይችልም ነው ጉዳያችን። ኢሳት ከግንቦት-7 መላቀቅ አለበት። ግንቦት-7 ለስልጣን ብሎ በሻእቢያ የተሸበበ ፈረስ ነው። ግልቢያው የት እንደሚያደርሰው ወደፊት የምናየው ነው። ሲሳይ አጌናም ለሙያህ ክብር ይኑርህ፤ ጥሬ ከብስል መቀላቀልህን--ተወነ!!

Comments
Post a Comment