6 አስተያየቶች፤ በዴሞክራሲና ሁለንተናዊ ልማት በኢትዮጵያ...
መጽሐፍ፤ ዴሞክራሲና ሁለንተናዊ ልማት በኢትዮጵያ፤ በብርሃኑ ነጋ
6 አስተያየቶች፤ ከቦጋለ ካሣዬ አምስተርዳም
ስለ
መጽሐፉ፤ በምረቃው እለትም ሆነ
ከዚያም በሁዋላ የተሰነዘሩትን አስተያየቶች አዳመጥኩ። አነበብኩ። አንብቤው ከጨረስኩ በሁዋላ ግን
አብዛኞቹ አስተያየቶች ሙገሳ
ብቻ ሆነው
ነው የታዩኝ። የግል
(ተዛማች) ትችቴንና አስተያየቴን በስድስት ነጥቦች ላይ
አቀርባለሁ።
1.መፈናቀል
ደራሲው በመግቢያው ላይ
ከልጁ ኖህ
ጋር ስለ
አደረገው የስራ
‘ውልና’ በገዛ ልጁ
ችሎታ መኩራቱን በመጻፉ የብዙዎቻችንን ስሜት
ነክቶታል። ኖህ
እጅግ ደስ
የሚል ፍሬ
ነው። ቅር
የሚለው ነገር
ግን የአሜሪካ ሲሳይ
መሆኑ ነው።
ሌላም የሚስያተክዝ ነገር
በአእምሮ ይመጣል። አባባ
ነጋ በአገራቸው ውጣ
ውረዱን ተቁዋቁመው የተዋጣላቸው ከበርቴ ሆኑ።
ራሳቸውንም ሆነ
አገራቸውን ጠቀሙ። ልጃቸው ብርሃኑ ግን
ገና በ17
አመቱ የፖለቲካ ጉጉት
አደረበት። ከዚያም ‘በአህያ አስተሳሰብ’ የሚል
ስድብ መዘዝ
ከተቃጣ ዱላ’
ነፍስ አውጭኝ ተርፎ፤ አሲንባ ሸፈተና በሱዳን በኩል
አሜሪካ ተሰዶ
እዚያው ተማረ። በፖለቲካ ጉጉት
ምክንያት ወደ
አገሩ ተመለሰ። ከዚያስ? ከንቲባ፣ ቀጥሎም ጠቅላይ ሚንስትር ሊሆን
ይችል ነበር። ወይኔ!ወንድሜን! ስልጣን ለትንሽ አመለጠቺውና እንደገና አገሩ
መኖር አልተመቸውም። አሁን
ወደ አሜሪካ ተመልሶ አሜሪካኖችን ያስተምራል። ዛሬም
ለአርባ አመታት የቀጠለው የፖለቲካ ጉጉቱ
አለመርካቱ ብቻ
ሳይሆን፤ አቅጣጫውም አነጋጋሪ ሆኖአል። ኖህና
ሌሎች ኖሆችስ? አሜሪካዊና አውሮፓውያን ሆነው
ቀልጠው መቅረታቸው አይደለም እንዴ?
የፖለቲካ ዝንባሌ ካላቸው የነገ
ኦባማዎች የመሆንም እድል
አላቸው። የኢትዮጵያ ጉዳት
ዘረፈ ብዙ
ነው። ከእነ
አባባ ነጋ
የቀጠለው ኢትዮጵያዊ ትውልድ በአገሩ እንዳያብብና እንዳያፈራ የቀጠለው መፈናቀል ማቆሚያው ገና
አይታወቅም።
2.መሬት
ደራሲው የመሬትን ጥበትና መራቆት በሚመለከት ያቀረባቸው ጉዳዮች አሳሳቢዎች ናቸው። መሬት
የግል ይሁን
ወይስ የመንግስት ወደሚሉት ቁልፍ
ውይይቶች በቀጥታ ለመግባት አልፈለገም። ታዲያ
ዛሬ በመሬት የመንግስት መሆን
የሚታየውን አስከፊ ሙስና
አስመልክቶ፤ መሬት
የግል ቢሆን
ሙስናውን ለመዋጋት ያስችላል በሚል
ፈራ ተባ፤
የግል ይዞታን እንደሚደግፍ በጉዋሮ በር
ዞሮ ሊነግረን ይፈልጋል። መሬት
የግል ይሁን
ብሎ የቆረጠ የፖለቲካ አቁዋም እንዳይዝ የቀፈደደው የጎሳ
ጉዋዶቹ እንዳያይቀየሙት ለመሆኑ የተደበቀ ነገር
የለውም። ደራሲው እንዳለው ይኸን
መጽሃፍ ለመጻፍ ያነሳሳው Why nations fail የሚለው መጽሃፍ ከሆነ፤ የዚሁ
መጽሃፉ ዋና
ፍሬ ነገር በግለሰቦች ነጻነት ላይ
ያጠነጠነ ስለሆነና፤ የግል
ንብረት
የመያዝ መብትም አንዱ
ዋናው ቁልፍ
የእድገት መሰረት ተደርጎ ሰለቀረበ በመሬት ይዞታ
ላይ እንደ
አንድነት፣መኢአድና የሰማያዊ ፓርቲዎች ደፋር
አቁዋም ሊኖረው በተገባ ነበር። በአጭሩ ደራሲው ስልጣን ቢይዝ
አራሹ ኢትዮጵያዊ በዜግነቱ መሬትን በግል
የመያዙ መብቱ
ምን ሊሆን
እንደሚችል በግልጽ አልተቀመጠም። በዚህ
ቁልፍ ጥይቄ
ላይ የጠራ
አቁዋም የማይዝ መሪ
የኢትዮጵያ ብሄራዊ አገራዊ ስሜት
እንዳይጠናክር ደንቃር ፈጣሪ
ከመሆኑም በላይ
ገበሬው ይሁን
ከተሜው በድሕነት ቢኖር
ግድ የሌለው ነው። መሬት
የግል ካልሆነም የአካባቢ ቁርቁዋሶን መከላከል አይቻልም። ከደርግ ጀመሮ
የታየው የምርት ማሽቆልቆልና የድሕነት መባባስ ዋናዎቹ ምክንያቶች፤ የአራሹ ዋስትና ነጻነት ማጣትና መሬትና አራሹ
አለመገናኘታቸው ናቸው።
3
‘የኦሮሞ ሕዝብ’
ደራሲው እንደ
ኦነግ፣ወያኔና ሴአይኤ የኦሮሞ ሕዝብ
ትልቅ ሕዝብ
እንደሆነ ጽፎአል። ይኼ
ግን በጭራሽ ሐሰትና ኦሮሞን ከኢትዮጵያ ለመነጠል የሚደረግ መሰሪ
የፖለቲካ ቀመር
አካል ነው።
ለነገሩ የወያኔ የመጀመሪያው ሕዝብ
ቆጠራ ‘አማራን’ ነው አንደኛ ያደረገው። ሆኖም
ቁጥሩ ቶሎ
ተቀናነሰና አንደኛው ኦሮሞ
ነው ተባለ። ቀጥሎም አማራ
የማምከን እቅድ
ወጣ። ሴአይኤ ቁጥሩን የሚያገሽበው ሆን
ብሎ ኦሮሚያ እንድትመሰረት የሚፈጥረው ማደናገሪያ እንጂ
ኦሮሞን ከአማራ ለይቶ
አያውቀውም። የወያኔና የሌሎች ጎሰኞች አንድ
መሰረታዊ ችግር
ግን አንድ
ሰው አማራ
የሚባለው ምን
ሲሆን ነው?
ኦሮሞስ የሚባለው ምን
ሲሆን ነው?
የሚለውን የማይመልሱ በመሆናቸው ነው።
እኛ ግን
በእርግጥ የምናውቀው ነገር
ወያኔ ስልጣን ከያዘ
ጀምሮ፤እስካሁን ያልተቆጠረ ሕዝብ
እንዳለ ነው።
ይኸም ከኦሮሞ፣ከአማራ፣ከጉራጌ፣ከትግሬ፣ከወላይታ፣ከሃዲያና ከንባታ፣ከሲዳማ፣ከአፋርና ሱማሌ
ወዘተርፈ በጦርነት፣በንግድ፣በስደት፣በሃይማኖት፣በጋብቻ፣በቁዋንቁዋ ወዘተ
የተቀላቀለው ሕዝብ ነው።
ለእኔ ይኸ
እስካሁን በትክክል ያልተቆጠረ ቅይጥ
የሕዝብ ክፍል
ነው አብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ
መባል ያለበት። አንድ
ስልጣን እጨብጣላሁ የሚል
ፖለቲከኛ፤ ያደገበትን ሕብረተሰብም ሆነ
ማሕበረሰብ ጠንቅቆ ማወቅ
አለበት። ያንን
ካላወቀ ግን
የሚጋተው የውሸት ቁጥር
ያሳስተውና በአየር ላይ
የተንሳፈፈ ትንተና ውስጥ
እንዲገባ ይገደዳል። ትልቁ
የኢትዮጵያ ሕዝብ
ቁጥር የተቀላቀለው ነው
እንጂ ኦሮሞ
ወይም አማራ
የሚባሉት አይደሉም። የጠላት ወሬ
ነው።
4
.አፓርታይድ
ደራሲው ስለ
ደበቡ አፍሪካ ድሕረ-አፓርታይድ የጻፈው በጣም
ትምህርታዊ ነው።
አፓርታይድ ሲወገድ ነጮቹ
የኢኮኖሚ ጥቅማቸው ሳይነካ ነው
የፖለቲካ ስልጣን ያስረከቡት። አሁን
የደቡብ አፍሪካ መንግስት ነጮቹ
የአገሪቱን ሃብት
ስለተቆጣጠሩ ለጥቁሮች የስራ
እድል የመፍጠር ጉዳይ
አዳጋች ሆኖበታል። ታዲያ
ቢቸግረው መዋእለ-ንዋይ
ለማፍሰስ ወደ
ደቡብ አፍሪካ የሚሄዱ የውጭ
ዲታዎች ጥቁሮችን እንዲቀጥሩ ቅደመሁኔታ ያቀርብባቸዋል። ዲታዎቹ ግን
የፈለጉትን የመቅጠር መብታቸው በመገፋቱ ሁሉም
በበጎነት አያዩትም። በዚህም ምክንያት ፈሰስ
ከማድረግ ተቆጥበው ወደተሻለ አገር
የሚሄዱ አሉ።
ስለዚህ አፓርታይድ ቢፈርስም አሁንም የደቡብ አፍሪካ ጥቁር
ዜጎችዋ የሃብትዋ ተቁዋዳሽ ሳይሆኑ፤ የበይ ተመልካችነታቸው ቀጥሎአል ማለት ነው።
ይኸ ለአንድ መንግስት ትልቅ
ፈተና ነው።
የመጣ ይምጣ
ብሎ መሬት
ለጥቁሮች ያከፋፈለው ሮበርት ሙጋቤ
የደረሰበትን ወርጭብኝ ሁላችንም እናውቃለን። ታዲያ
ደራሲና ፖለቲከኛ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ፤
ይኼን ጉዳይ
ተረድቶ፤ እኔስ
ነገ ስልጣን ብይዝ
በኢትዮጵያ የአፓርታይድ አይነት ስርአት ዘርግተው አግባብ ባልሆነ መንገድ ሃብት
ያካበቱትን ወያኔዎችና ጀሌዎቻቸውን ምን
አደርጋቸዋለሁ? ብሎ በእርግጠኝነት አስቦበታል። ይሁን
እንጂ ምን
ለማድረግ እዳሰበ ፍንትው አድርጎ በመጽሃፉ ውስጥ
አይናገርም። ዳርዳርታው
ግን የት አባታቸው እነዚህን ሌቦች እወርሳቸዋለሁ ስለመሆኑ እርግጠኛ ነገር ነው። ታዲያ
ደራሲው እንደ
ፖለቲከኛ ስልጣን ለመያዝ የሚንቀሳቀስ ሆኖ
እያለ፤ በዚህ
ቁልፍ ጉዳይ
ላይ እንኩዋን ግልጽና ደፋር
የሆነ አቁዋም ቢያራምድ፤ የፖለቲካ ድጋፉ
እንደሚጠነክር የተረዳ አይመስልም። መሪ
እውነተኛ፣ደፋር፣ ሩሕሩሕ ቆራጥ
ካልሆነ ከሕዝብ ጋር
ሊግባባ አይችልም። በሚቀጥለው መጽሃፉ ይኼን
ያድበሰበሰውን ጉዳይ
ዘርዘር አድርጎ በድፍረት ማቅረብ አለበት።
5.
ሰብአዊ መብቶች
ደራሲው ግርማና አየለ
በሚባሉ የሰው
አራጆች ስለተቀጠፈው ሕይወት አንስቶአል። ይሁን
እንጂ አሳራጁን ታምራት ላይኔን አላነሳም። ታምራት ላይኔ
የወያኔ ጌኛ
ሆኖ ለብዙ
ሺህ ኢትዮጵያዊ መፈናቀልና ሕይወት መጥፋት ተጠያቂ ነው።
ዛሬ ይኼ
ወንጀለኛ ‘ክርስቲያን’ በአሜሪካ የተንደላቀቀ ኑሮ
ይኖራል። ደራሲውን ከዋናው አራጅ
አቶ መለስ
ዜናዊ ጋር
ያገናኘውም እሱ
ነበር።
ደራሲው በአማራ አክራሪም ሆነ
በአማራ ጠላትነት እንደሚወነጀል ገልጦአል። የሆኖ
ሆኖ እንደኔ አንድ
አገር ለመምራት የሚያስብ ፖለቲከኛ ከ1991
ጀምሮ በመንግስት ፖሊሲ
‘በአማራው’ ላይ እየተካሄደ ስላለው ዘርፈ
ብዙ ስቆቃ
አንድ መስመር እንኩዋን መጫር
ይገባው ነበር። ስለኦጋዴንም ሆነ
ስለ ጋምቤላ እልቂቶችም ምንም
ያነሳው ነገር
የለም። ልብ
አድሚ ሆኖም
አግኝቼዋለሁ።
6.
እንደመቁዋጫ…
የደራሲው የቁዋንቁው አጠቃቀም ተወዳጅ ሆኖ
ሳለ ማከም
የሚለውን ቃል
ለበጎም ለክፉም መጠቀሙን አስተውያለሁ። በደልን ማከም
ይገባል ሲባል፤ ውጤቱ
አዎንታዊ ነው።
ወያኔ የውሸት ቁጥሮችን ‘አክሞ’ ነው የሚያቀርበው፤ ከማለት ይልቅ፤ ቁጥሮችን አጋሽቦ ወይም
አጋኖ ቢባል
ለኢኮኖሚስቶች ጆሮ
የተሻለ የሚያቃጭል ይመስለኛል።
ደራሲው ከቅንጅት በሁዋላ እነሆ
ሶስተኛ መጽሃፍ ሊያሳትም እየተዘጋጀ ነው።
ኢትዮጵያ ለገጠሙዋት አጣዳፊና የተወሳሰበ ችግሮች ከርሱም ሆነ
ከማንም ግለሰብ ፍጽም
ፍቱን የሆነ
መፍትሄ የሚጠብቅ የለም። ይሁን እንጂ
ደራሲው ስልጣን ለመያዝ ጉጉ
ስለሆነ ለመግባባትም ሆነ
ለመስማማት ብዙ
ትውልድና ትምህርት የሚጠይቀውን የታሪክ ጠባሳ/ንዝንዝ ከፓለቲካው ውስጥ
ባይቀላቅል ይሻለዋል። ለችግሮች ቅድሚያ መስጠት ያስፈልጋል። አሁን
የአብዛኛው ሰው
ችግር የቡዴና/እንጀራ ጥያቄ
ስለሆነ ብልህ
ፖለቲከኛ ይኼንኑ ጥያቄ
እንዴት እመልሳለሁ በሚለው ላይ
ነው መፍትሄ ፈልጎ
፤ እንደ
የመሬት ባለቤትነትን ይዞታ
በመሳሰሉት ጉዳይች ላይ
ከጎሰኞች ጋር
ሳይሆን ከአገረኛው ጋር
በግልጽ ቁዋንቁዋ መነጋገር ያለበት።
Comments
Post a Comment