Posts

Showing posts from 2024

እስከ ስባት ትውልድ!

ልደቱ አያሌው... እስከ ሰባት ትውልድ!                               ቦጋለ ካሣዬ የፖለቲካ ውይይቶች በፖሊሲ ላይ የተመሰረቱ መሆን ቢኖርባቸውም እንደየአገሩ ልሂቃን የፖለቲካ ባህል ይዘታቸውና ቃናቸው ይለያያሉ፡፡ ኢታሊያዊው ፋውስቶ በርቲኖቲ እንደ ልደቱ አያሌው የመናገር ችሎታ ካላቸው ፖለቲከኞች አንዱ ነው፡፡ማህበራዊ ፍትህ ለኢታሊያ ህዝብ ብቻ ሳይሆን ለአለም ህዝብ ሁሉ የሚመኝ ሃቀኛ ሰው ነው፡፡ መሃንዲስ ነው።በሰራተኛ ማህበራት ውስጥም መሪ ሆኖ ሰርቶአል፡፡በስሎ ነው ወደ ፖለቲካ አለም የገባው፡፡ተልእኮው የካቲታሊዝምን ያልተገራ የሃብት ቅንቅን ማጋለጥ እንጂ የካቢኔ ሹመት አይደለም፡፡ የሚናገረው ሁሉ እውነት ስለሆነ ማንም አጭበርባሪ ኢታሊያዊ ፖለቲከኛ ይሁን አድርባይ ምሁር ከእርሱ ጋር በአደባባይ ለመወያየት አይደፍርም፡፡ራእይና እውነት ያለው ሰው ነው፡፡ “la Citta’ degli uomini”/2007 ( የወንዶች ከተማ) የሚል መጽሃፉ ተደጋግሞ ቢነበብ አይሰለችም። የአብይ አህመድ የመደመር ዝባዝንኬን ግን ገልጦ 30 ገጽ መድረስ ትልቅ አቀበት ነው። ሌላ የማውቀው የልደቱ ተመሳሳይ የንግግር ችሎታ ያለው ሰው የዳቹ ያን ማርያኒሰን ነው፡፡ እርሱም የማህበራዊ ፍትህ ጠበቃ ነው፡፡ የሰሜን አትላንቲክ ትብብርን አጥብቆ የሚያወግዝና እንዲሁ እንደ በርቲኖቲ የካፒታሊዝም ቅንቅን የሚራገፍበት አለም ማየት ነው ምኞቱ፡፡ ያን ራሱን በንባብና በልምድ ያዳበረ ሰው ነው፡፡ ውሸት አይወድም፡፡ ልደቱ አያሌው ልደቱ አያሌው በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ የተከሰተው በጉርምስና እድሜው ከመኪና ንግድ ውጭ ምንም የስራም ሆነ የትምህርት ...

ተፈሪው ፋኖ እስክንድር ነጋ!

Image
                                           ተፈሪው ፋኖ እስክንድር ነጋ! ቀ ዳማዊ ማንነታችን አማራ ነው፡፡ የአካባቢ ማንነቶች(ጎጥ) ከቅርብ ታሪካችን የተከሰቱ ናቸው፡፡ ጥንታዊ የአማራነቱን ማንነት ሳያውቅ በአካባቢ ማንነት መኩራራት አጉል መኮፈስና ታሪክን አለማወቅ ነው ሲል እስክንድር ድል ለዲሞክራሲ በሚለው መድብሉ ገና ዱሮ የትጥቅ ትግል ከመጀመሩ በፊት በዝርዝር ጽፎኣል። እስክንድር-ጠሎች ግን እርሱ ድል ለዲሞክራሲ ነው እንጂ ድል ለአማራ አይልም ሲሉ ይከሱታል። በእርግጠኝነት ለመናገር ወይ መጽሃፉን ተንተርሰውታል፣ አላገኙትም ወይም ሃቁን ቢያውቁትም ወደ ስም ማጥፋት ላለመሄድ ህሊናቸው አልቆረቆራቸውም። እ ስክንድር አማራው መንግስት፟፟ - መር የዘር ፍጅት እየተካሄደበት ለከፍተኛ የህልውና አደጋ በመጋለጡና አደጋውም በሰላማዊ ትግል ማስቆም ስላልተቻለ  የፋኖን የትጥቅ ትግል ከጎዋዶቹ ጋር ማስተባበር ጀመረ። ወጣት የነብር ጣቶቹ በተለይ እኔ የማውቃቸው ጌጥዮና ወንድይራድ በአሳፋሪ ሁኔታ ዘመኔ ካሴ(የአማራው አብይ አህመድ) አግቶታል። እንዲሁም ሌሎቹ ስማቸውም የማላቀው ብዙዎች አይኔ ላይ ይመጣሉ። በወጣጥነት እድሜያቸው የሚያደርጉት አስተዋጽኦ ትውልድ የሚኮራበት ነው። እስክንድር ገና ወደ ትጥቅ ትግሉ ከመግባቱ በፊት የባልደራስ መሪ እያለ ከታዋቂ የፋኖ መሪዎች ጋር ተገናኝቱዋል። መክሮአል። አንዴ እንደውም በአዲስ አበባ ዘላለም ከሚባል የአገዛዙ ደጋፊ ጋዜጠኛ ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ፤ የወለጋን ጭፍጨፋ የአካባቢው ልዪ ሃይል ማስቆም ስላ...

ዴሞክራሲ ስር በሰደደበት አገሮች ....

    የካናዳ የሰብዓዊ መብቶች ንዑስ   የውጭ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ፤ የ ኢትዮጵያን ጉዳይ በሚመለከት ያዘጋጀውን ወቅታዊ ግምገማ  አስመልክቶ የተሰጠ አስተያየት። ቦጋለ ካሣዬ/አትዋ ዴ ሞክራሲ ስር በሰደደበት አገሮች የህዝብ ተወካዮች ስልጣን ላይ ያለውን አካል ስራውን በትክክል መስራቱን በጥንቃቄ መገመገም ትልቁ ሃላፊነታቸው ነው። በዚህም መሰረት መረጃዎችን አሰባስበው አገራቸውን ሊጠቅም ይችላል ብለው የሚያምኑበትን የፓሊሲ ሃሳብ ያቀርባሉ።   በዚህም ምክንያት የካናዳ የሰብዓዊ መብቶች ንዑስ   የውጭ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ኢትዮጵያውያንን በማሳተፍ ስለ አገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ ለማዳመጥ በጁን 11/2024 መድረክ ፈጥሮ ነበር። ስድስት ኢትዮጵያውያን ነበሩ እንዲገኙ የታሰበው። የአማራ ተወካይ አለመጋበዙ ስለታወቀ፤ በአማራ ማህበራት በተደረገው የቅሬታ ዘመቻ አማራ እንዲወከል ተደረገና ሰባት ኢትዮጵያውያን ተሳተፉ።   1.      ዶ/ር ዪናስ ብሩ ከአሜሪካ በቪዲዮ ተካፍለዋል። በአለም አቀፍ ተቁዋም ባለቸው ልምድ፣የአብይ አህመድ አማካሪ ስለነበሩና በቁዋንቁዋ ችሎታቸውም የህዝብ ተወካዮቹን ቀልብ ስለሳቡ ብዙ ጥያቄዎች ቀርበውላቸው  የሚያምኑበትን ሃሳብ ለማራመድ የተሻለ እድልና ጊዜ አግኝተዋል።   ይሁን እንጂ ዶ/ሩ እንደተለመደው ስለባውንና ግፍ አይፈሬዎቹን አንድ ላይ እንደ ወዳጃቸው መራራ ጉዲና አጃምለው ሲከሱ ተደምጠዋል።  የዘር ፍጅት በአለም አቀፍ ገለልተኛ አካል እስካልተረጋጋጠ ድረስ በኢትዮጵያውያን አክቲቪስቶች የሚቀነቀነው ተቀባይነት የለውም በማለት፤ የብልጽግና፣የኦነግንና የወያኔን የ...

ውድ ዋጋ!

                                                                ውድ ዋጋ! ፋኖ የአማራን ህልውና ለማስከበር ነፍጥ አንስቶ መዋጋት ከጀመረ አንድ አመት ሊሞላው ነው። ጥሪቱን በመሸጥና ከብልጽግና ወታደሮች በማረከው ትጥቅ ወታደራዊ መዋቅሩን አደራጅቶ፣ በአማራ ህዝብ ስንቅ ተደግፎ በአጭር ጊዜ  እዞችን በመመስረት ለኢትዮጵያም ሆነ ለአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋት እውን መሆን ፤ተአማኒና ተስፋ ሰጪ ኃይል ሊሆን ችሎአል። ወታደራዊ ኃይል በአሁን ወቅት ፋኖ በሸዋ ሁለት፣በጎጃም በጎንደርና በወሎ አንዳንድ እዞች አሉት። ትናንት ደግሞ በመቶ አለቃ ማስረሻ የሚመራ የአማራ ፋኖ ህዝባዊ የጎጃም እዝ ተመስርቶአል፡፡ ሌሎችም ሊፈጠሩ ይችላሉ፡፡ እነዚህን በአንድ ኮማንድ ለማምጣት ስራ እየተሰራ እንደሆነ ከፍኖዎቹ በተደጋጋሚ ሰምተናል። አንዳንድ የወታደራዊ ሙያ ያላቸው ሰዎች ደግሞ ይኼ ሂደት ቶሎ የማይቁዋጭ ከሆነ አንድ ላይ ለመስራት የሚችሉ እዞች በአንድ ኮማንድ ይሰባሰቡና፤ ለጊዜውም ቢሆን ደግሞ ካልቻሉት ጋር በመናበብ አብሮ እየሰሩ ወታደራዊ ድሉን ወደ መቁዋጨቱ ቢኬድ ይሻላል ሲሉ፤ ሌሎች ደግሞ አስቀድሞ ሰራዊቱ በእዝ ደረጃ በመዋቀሩ በቂ አቅም መፍጠሩን ስለሚያሳይ በአንድ አማራ ኮማንድ ስርም ባይኮን፤ እየተናበቡ መዋጋት እንደሚቻል ያሳስባሉ። እዞቹ የተዋጊ ሳይሆን የተለያዩ የሎጂስቲክ ችግሮች እንዳሉባቸው እሙን በመሆኑ እስከ ድል ድረሰ ያልተቁዋረጠ ድጋፍ በተቀናጀ መልክ ያ...

እስክንድር ነጋና አማራ

እስክንድር ነጋና አማራ አንድ ለመንገድ /3/ …  ባለፈው አንድ ለመንገድ/2ኛ/ ዳሰሳ፤ \እስክንድረ ነጋና አማራ/ ከእስክንድር ስራ የተወሰደ መሆኑን ገልጫለሁ። አሁን ወደ መጨረሻው ሶስተኛው ክፍል ደርሰናል። ዳሰሳውን ዘርዘር አድርጌ ያቀረብኩትም እስክንድር እንዴት ስለአማራ ህዝብ እንደሚጨነቅ የጻፈውን ስራ ለማስተዋወቅ ነው። ያነሳሳኝ ጉዳይም   ባለፈው ወር በህብር ሬዴዮ አንድ የፋኖ ‘ቃለ አቀባይ ነኝ’ ባይ መስሪ ወይም ደንቆሮ ስለ እስክንድር የተናገረውን ፍሬፈርስኪ ካዳመጥኩ በሁዋላ ይኼ የእስክንድርና የፕሮፌሰር መስፍን ሙግት ‘ለቃለ አቀባዩም’ ለተቀረው አንባቢ ግንዛቤ ይሰጣል በማለት ነው። አንድ ለመንገድ /3/  እስክንድር ነጋና አማራ እስክንድር በኮሚኒስቶች መስፍርትም ቢኬድ አማራ ጎሳ/ብሄር/ማህበረሰብ ለመባል፤ከአምስቱ መስፍርቶች፤ የጋራ ቁዋንቁዋ፣ስነልቦና ታሪክና መሬትን ያሙዋላል ይላል። የማያሙዋለው የጋራ ኢኮኖሚ ነው። በኢንዱስትሪ የዳበረ ኢኮኖሚ እንኩዋን አማራ ኢትዮጵያም ስለሌላት፤ ነገድ ለመባል የኢኮኖሚውን መስፍርት ማሙዋላት አይጠበቅበትም።ኮሚንስቶችም ሁሉም መስፍርቶች መሙዋላት አለባቸው አይሉም። ይሁን እንጂ ከመስፍርቶቹ መቅረት የሌለበት የጋራ ስነልቦና ነውና በዚህ ረገድም የአማራ ነገዳዊ ማንነት አሌ የሚባል አይደለም። እስክንድር ገሪማ ታፈረ( የታዋቂዊው ፊልም ሰሪ ኃይሌ ገሪማ አባት) ስለ አማራ 25 ዓመታት ሙሉ ያጠኑትን አለቃ ታዬ የሚባሉትን ሊቅ በመጥቀስ እ.ኢ.አ 1973 የጻፉትንም ያጋራናል። ገሪማ አለቃ ታዬ አማራ የሚባለው ህዝብ ትውልዱ ከሴም ልጅ ከኤቦር ነገደ ዮቅጣን መሆኑን አረጋግጠዋል ይላሉ።ጥናታቸውም የተመረኮዘው፤ በአለም ታሪክ ተመራማሪዎች ስራ(ኢዘንበር፣መልዚ፣ፓስቴንና ቫንሲን)፣ከመልኩ(...

መነሻችን አማራ መዳረሺያችን ኢትዮጵያ!

  መነሻችን አማራ መዳረሺያችን ኢትዮጵያ!   አንድ ለመንገድ /2/ ... እስክንድር ነጋና አማራ ቀጥለን እስክንድር በ1996(የዛሬ 20 አመት) በጋዜጠኛነቱ “አማራ የለም” ብለው ከሞገቱት ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማሪያም ጋር ያደረገውን ክርክር በደምሳሳው እንመለከታለን፡፡ እግረመንግዳችንንም ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ፤ “አንዳንድ ምሁራን አማራ የለም ሲሉ ይደመጣሉ፤ የአማራ ጠላቶች ግን አማራውን ለይተው ለማጥቃት ሲቸገሩ አናይም” ብለው አማራ የለም ባዮችን መተቸታቸውን ማስታወስ ተገቢ ነው፡፡ አስራት “ ለአማራ ጦርነት ማስተማር፤ እናት ለልጁዋ ምጥ እንደማስተማረች ይቆጠራል ” ብለው አማራ እንዲዋጋ በጥዋቱ አስጠንቅቀውት ነበር፡፡ዘግይቶም ቢሆን ዛሬ እውነቱን እያየነው አይደለም እንዴ? አማራ እስክንድር ፕሮፈሰር መስፍን አማራ የሚባል ጎሳ የለም፤ [1] ቃሉ ለክርስትና ነው የሚቀርበው ያሉበትን በቂ መረጃ አላቀረቡም ይላል፡፡ ፕሮፌሰሩ እንደ ምንጭ የተጠቀሙባቸው ከሳቴ ብርሃን ተሰማ፣አለቃ ደስታ ተክለወልድ፣ አለቃ አ ጽ ሜና በአባ ዪሃንስ ገ/እግዚአብሄር (ትግርኛ) መዝገበ ቃላት የሰፈሩት ፍቺዎች አንድም ቦታ አማራ ክርስቲያን ማለት ነው የሚል የለባቸውም፡፡ ፕሮፌሰር ያጣቀሱት የአለቃ ደስታ ተክለወልድ፤አማራ ማለት ተጠምቆ ተገዝሮ፤ ማተብ አስሮ ቢልም አማራ የሃይማኖት መጠሪያ ነው አይልም፡፡የአለቃው ማብራሪያ የሳውዲ ዜጋ ለመሆን እስልምና መቀበል ወይም የእስራኤል ዜጋ ለመሆን(ከጥቂት አረቦች በስተቀር) የአይሁዲ ሃይማኖት ተከታይ መሆን እደሚያስፈልግ አይነት ተመሳሳይነት ያለው ነው፡፡ ዐማራ ለመሆን ለምን ክርስቲያ መሆን አሰፈለገ? ሲል እስክንድር ይጠይቃል፡፡ነገሩ ከታሪክ ጋር የሚያያዝ ነው፡፡ እንደ እስክንድር ከሆነ ምክንያቱ ሙስሊ...

መነሻችን አማራ መዳረሺያችን ኢትዮጵያ!

  አንድ ለመንገድ፤ መነሻችን አማራ መዳረሺያችን ኢትዮጵያ! አማራንና ኢትዮጵያን የማፋታት ስራ በናዚዎች ቀጥሎም በፍሽቶች የተቀነባበረ ነው፡፡ግቡም የኢትዮጵያ የተፈጥሮና የሰው ሃይል ለምተው ተፈሪ አገር ከመፍጠራቸው በፊት በነገዳዊ ፖለቲካ ማክሸፍ ነው፡፡ የአፍሪካን አህጉር በዘፈቀደ የሸነሸኑት የአውሮፓውያን ቅኝ ገዢዎች ናቸው፡፡አሁን ደግሞ የአዲሶቹ ቅኝ ገዥዎች አቀንቃኞች(ቲሩሊዝንና ማርካኪስን መጥቀስ በቂ ነው)፤ በአፍሪካ ሰላምና ልማት እንዲፋጠን፤ በጎሳ ሰበብ የሚደረገውን ግጭቶች ለማቆም ይረዳ ዘንድ፤ ትናንት በዘፈቀደ የተፈጠሩትን የአፍሪካ አገሮች አፍርሶ በጎሳ ማወቀር ይሻላል ሲሉ ይደመጣሉ፡፡ በተቃራኒው፤ እንደ ጁሊየስ ኔሬሬ ያሉት አፍሪካውያን ደግሞ፤ አፍሪካን በጎሳ መሸንሸን ሳይሆን ዛሬ ላይ ያሉትን የአገራት ድንበር ማላላትና ቀጥሎም በማፍረስ አፍሪካውያን የወደዱበት እየሄዱ እንዲሰሩና እንዲኖሩ ማድረግ ነው የሚገባው ሲሉ ይከራከራሉ፡፡ ኢትዮጵያ ለጎሳ ፖለቲካ ከኢታሊያ ወረራ ለጥቆ ለሁለተኛ ጊዜ  ቤተ ሙከራ የተደረገቺው፤ ከላይ በጠቀስነው የአዲሶቹ ቅኝ ገዢዎችን ሃሳብ ተንተርሶ ነው፡፡ ሃሳቡን ደግሞ በስራ ላይ ለማዋል ትህነግና ኦነግ በኢትዮጵያ በቅለውና መትተው ስለነበር እጅግ ተስማሚ ነበሩ፡፡ ለሁለቱ ድርጅቶች በውጭ አለም የሚታየው ስስ ልብም ከዚሁ እቅድ ጋር የተስማማ በመሆኑ ነው፡፡ ዲያቆን ዘመድኩን በቀለ  መነሻችን አማራ መዳረሺያችንም አማራ፤የሌሎቹም እንዲሁ፤ መነሻው ኦሮሞ፤መዳረሺያው ኦሮሞ፤ መሆን አለበት የሚል ስብከት ጀምረዋል፡፡ የእነዚሁኑ አዲስ ቅኝ ገዢዎች አቀንቃኝኞችን ጎራ መደባለቃቸው ነው፡፡ በተለይ ክርስቲያን ሆነው ይኼን ዘረኛ አመለካከት መከተላቸው አስተምህሮቱ ያልተዋሃዳቸው መሆኑ አጋላጭ ነው፡፡...