መነሻችን አማራ መዳረሺያችን ኢትዮጵያ!

 አንድ ለመንገድ፤

መነሻችን አማራ መዳረሺያችን ኢትዮጵያ!

አማራንና ኢትዮጵያን የማፋታት ስራ በናዚዎች ቀጥሎም በፍሽቶች የተቀነባበረ ነው፡፡ግቡም የኢትዮጵያ የተፈጥሮና የሰው ሃይል ለምተው ተፈሪ አገር ከመፍጠራቸው በፊት በነገዳዊ ፖለቲካ ማክሸፍ ነው፡፡

የአፍሪካን አህጉር በዘፈቀደ የሸነሸኑት የአውሮፓውያን ቅኝ ገዢዎች ናቸው፡፡አሁን ደግሞ የአዲሶቹ ቅኝ ገዥዎች አቀንቃኞች(ቲሩሊዝንና ማርካኪስን መጥቀስ በቂ ነው)፤ በአፍሪካ ሰላምና ልማት እንዲፋጠን፤ በጎሳ ሰበብ የሚደረገውን ግጭቶች ለማቆም ይረዳ ዘንድ፤ ትናንት በዘፈቀደ የተፈጠሩትን የአፍሪካ አገሮች አፍርሶ በጎሳ ማወቀር ይሻላል ሲሉ ይደመጣሉ፡፡ በተቃራኒው፤ እንደ ጁሊየስ ኔሬሬ ያሉት አፍሪካውያን ደግሞ፤ አፍሪካን በጎሳ መሸንሸን ሳይሆን ዛሬ ላይ ያሉትን የአገራት ድንበር ማላላትና ቀጥሎም በማፍረስ አፍሪካውያን የወደዱበት እየሄዱ እንዲሰሩና እንዲኖሩ ማድረግ ነው የሚገባው ሲሉ ይከራከራሉ፡፡ ኢትዮጵያ ለጎሳ ፖለቲካ ከኢታሊያ ወረራ ለጥቆ ለሁለተኛ ጊዜ  ቤተ ሙከራ የተደረገቺው፤ ከላይ በጠቀስነው የአዲሶቹ ቅኝ ገዢዎችን ሃሳብ ተንተርሶ ነው፡፡ ሃሳቡን ደግሞ በስራ ላይ ለማዋል ትህነግና ኦነግ በኢትዮጵያ በቅለውና መትተው ስለነበር እጅግ ተስማሚ ነበሩ፡፡ ለሁለቱ ድርጅቶች በውጭ አለም የሚታየው ስስ ልብም ከዚሁ እቅድ ጋር የተስማማ በመሆኑ ነው፡፡

ዲያቆን ዘመድኩን በቀለ  መነሻችን አማራ መዳረሺያችንም አማራ፤የሌሎቹም እንዲሁ፤ መነሻው ኦሮሞ፤መዳረሺያው ኦሮሞ፤ መሆን አለበት የሚል ስብከት ጀምረዋል፡፡ የእነዚሁኑ አዲስ ቅኝ ገዢዎች አቀንቃኝኞችን ጎራ መደባለቃቸው ነው፡፡ በተለይ ክርስቲያን ሆነው ይኼን ዘረኛ አመለካከት መከተላቸው አስተምህሮቱ ያልተዋሃዳቸው መሆኑ አጋላጭ ነው፡፡

ፖለቲካ

በፕሮፌሰ አሥራት ወልደየስ ይመራ የነበረው መአህድ በፕሮራሙ ላይ መነሻው አማራ መዳረሻው ኢትዮጵያ መሆኑን ቁልጭ አድርጎ ነበር ያስቀመጠው፡፡ ለመአህድ መፋፋት ግን የተሰናዳ መስክ አልነበረም፡፡አማራው ገና እሱን የማጥፋቱን እቅድ በበቂ አልተገነዘበም ነበር፡፡ ዛሬ ሌላ ቀን ነው፡፡ ይሁን እንጂ ዛሬም ቢሆን ከአብዛኛው ፋኖ ቃለ አቀባዮች ይሁን መሪዎች፤ በመነሻችን አማራ መዳረሺያችን ኢትዮጵያ ልዩነት አላይም፡፡ ልሙጡ ሰንደቅ አለማም የሚወክለው ይኼንኑ ነው፡፡የአስራትና የእስክንድር ክፍለ ጦሮች ስያሜም ይኼንኑ እውቂያ የሚያረጋግጥ ነው፡፡

ፋኖ እስክንድር ነጋ የአማራውን መደራጀት አስፈላጊነት ገና ከጥዋቱ ከተገነዘቡት አማሮች ስለነበር መአህድ ወደ መኢአድ ሲለወጥ፤ ወቅቱ አይደለም፤ የተቻኮላ ነው ካሉት ሰዎች አንዱ ነበር፡፡ልደቱ አያሌው ግን ያኔ ጮርቃም ስለነበር የመአህድን የወጣት ክንፍ ገንጥሎ ኢደፓን መሰረተ፡፡

 

ይቀጥላል

Comments

Popular posts from this blog

የፋኖ አንድነት እንዴት?

እስከ ስባት ትውልድ!

አሞላቃቂ ጥቅመኛ!