ውድ ዋጋ!
ውድ ዋጋ!
ፋኖ የአማራን ህልውና ለማስከበር ነፍጥ አንስቶ መዋጋት ከጀመረ አንድ አመት ሊሞላው ነው። ጥሪቱን በመሸጥና ከብልጽግና
ወታደሮች በማረከው ትጥቅ ወታደራዊ መዋቅሩን አደራጅቶ፣ በአማራ ህዝብ ስንቅ ተደግፎ በአጭር ጊዜ እዞችን በመመስረት ለኢትዮጵያም ሆነ ለአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋት እውን
መሆን ፤ተአማኒና ተስፋ ሰጪ ኃይል ሊሆን ችሎአል።
ወታደራዊ ኃይል
በአሁን ወቅት ፋኖ በሸዋ ሁለት፣በጎጃም በጎንደርና በወሎ አንዳንድ እዞች አሉት። ትናንት ደግሞ በመቶ አለቃ ማስረሻ
የሚመራ የአማራ ፋኖ ህዝባዊ የጎጃም እዝ ተመስርቶአል፡፡ ሌሎችም ሊፈጠሩ ይችላሉ፡፡ እነዚህን በአንድ ኮማንድ ለማምጣት ስራ እየተሰራ
እንደሆነ ከፍኖዎቹ በተደጋጋሚ ሰምተናል። አንዳንድ የወታደራዊ ሙያ ያላቸው ሰዎች ደግሞ ይኼ ሂደት ቶሎ የማይቁዋጭ ከሆነ አንድ
ላይ ለመስራት የሚችሉ እዞች በአንድ ኮማንድ ይሰባሰቡና፤ ለጊዜውም ቢሆን ደግሞ ካልቻሉት ጋር በመናበብ አብሮ እየሰሩ ወታደራዊ
ድሉን ወደ መቁዋጨቱ ቢኬድ ይሻላል ሲሉ፤ ሌሎች ደግሞ አስቀድሞ ሰራዊቱ በእዝ ደረጃ በመዋቀሩ በቂ አቅም መፍጠሩን ስለሚያሳይ በአንድ
አማራ ኮማንድ ስርም ባይኮን፤ እየተናበቡ መዋጋት እንደሚቻል ያሳስባሉ።
እዞቹ የተዋጊ ሳይሆን የተለያዩ የሎጂስቲክ ችግሮች እንዳሉባቸው እሙን በመሆኑ እስከ ድል ድረሰ ያልተቁዋረጠ ድጋፍ በተቀናጀ
መልክ ያስፈልጋቸዋል፡፡ ጎበዝ ፍኖ ካላሽነፈ አማራ ውድ ዋጋ ይከፍላል፡፡
ፖለቲካ
በፍኖ ውስጥ በአደባባይ ደምቆ የሚታየው የፖለቲካ ግብ መነሻችን አማራ መዳረሻችን ኢትዮጵያ ነው።
ይሁን እንጂ ይኼ የፖለቲካ ግብ ለፀጉር ስንጠቃና አማራን ለመከፍፈል እየዋለ ነው፡፡ ሲጀመር የዚህ የፖለቲካ ግብ ከመላው አማራ ሕዝብ ድርጅት የጀመረ ነው። ሲቀጥል
ደግሞ ሃሳቡ ዛሬም የተመረጠው በብዙ አማሮችና ሌሎች ኢትዮጵያውያን መክረውበት በውይይት ስምምነት ተደርሶበት ነው።
የሚደንቀው ደግሞ የመነሻችን አማራ መዳረሻችን ኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች የሚደግፉት የፖለቲካ ግብ፤ መነሻችን አማራ መዳረሻችንም አማራ መሆኑ ነው።
ይኼም አሁን ካለው የወያኔ ህግመንግስት ጋር የሚስማማ ነው።
ታዲይ አሁን በስልጣን ላይ ያለውን አገዛዝ ለመጣል ያውም በነፍጥ ጊዜያቸውንና ህይወታቸውን የሚያጠፉት ለምንድን ነው?
ህይወት ውድ ነው!
ነገሩ ግን ወዲህ ነው፡፡ ልክ የአብይንና የሽመልስን፤ “አሳምን ወይም አደናብር” አካሄድን የተከተለ ነው። ለምሳሌ ከእነዚህ
ተቃዋሚዎች አንዳንዶቹ እንደ መሪያቸው የሚያዩት ዘመነ ካሴን መሆኑን
ይነግሩናል፡፡ እስክንድርን ደግሞ ይጠላሉ፡፡ ይሁን እንጂ ዘመነ ካሴ ራሱ በቀደም በአደባባይ ያራመደው አቁዋም ከመነሻችን አማራ መዳረሻችን ኢትዮጵያ ቅንጣት
ያህል የተለየ አይደለም፡፡ ሆን ብሎው በእስክንድርን በዘመነ መካከል ሽንቁር ለማስፈት ነው ልፋታቸው፡፡ አውቀውም ይሁን ሳያውቁ
እነዚህ አደናጋሪዎች የአማራ ጠላቶች ናቸው፡፡
ተአማኒነት
በፖለቲካ ትልቁ የመሪ እሴት ተአማኒነት ነው። ተአማኒነት ደግሞ የሚገኘው በተግባር ነው። በፕሮፓጋንዳ ጋጋታ፣ በየጽላቱ
በመማልና ስለ እራስ ቆራጥነት በመዶስኮር አይደለም። በኢትዮጵያ ፖለቲካ ይሁን በአለም እንደ እስክንድር ነጋ ተአማኒ ሰው ማግኘት
ቀላል አይደለም። እስክንድር ትምህርቱም ኢኮኖሚክስና ፖለቲካ ነው። በጣም በጥልቀት ለማንበብና ለመጻፍም ችሎአል። ከፖለቲካው መድረክ እርሱን ለማግለል የሚደረገው ሴራ መልሶ የሚጎዳው የአማራን
ህብረት ነው። መሪን ማጠልሸት በውድ ያስከፍላል፡፡ ዘመነና እስክንድር ዘሜና እስኬው ተባብለው አንድ ላይ ለመስራት የማይችሉበት
ምንም ምክንያት የለም፡፡ ከማስረሻና ከዝናቡም ጋር ፍቅር ነው ሊኖር የሚገባው፡፡ ዘመነ ከብአዴን ከወጣ በሁዋላ በኤርትራ በረሃ
ተንገላቶአል፡፡በተደጋጋሚም ታስሮአል፡፡ ጥሩ ተናጋሪና ግርማ ሞገስ ያለው መሪ ነው፡፡ ለአማራ አንድነት ሲባል አንገቴን እስጣለሁ
የሚለው ዘመነ ከእስክንድር ጋር አብሮ የማይሰራበት ምንም ምክንያት የለም፡፡ እስክንድር ከዚህ የተለየ አቁዋም ይኖረዋል ብዬ አልገምትም፡፡
Comments
Post a Comment