ዴሞክራሲ ስር በሰደደበት አገሮች ....
የካናዳ የሰብዓዊ መብቶች ንዑስ
የውጭ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ፤ የኢትዮጵያን ጉዳይ በሚመለከት ያዘጋጀውን ወቅታዊ
ግምገማ አስመልክቶ የተሰጠ አስተያየት።
ቦጋለ ካሣዬ/አትዋ
ዴሞክራሲ
ስር በሰደደበት አገሮች የህዝብ ተወካዮች ስልጣን ላይ ያለውን አካል ስራውን በትክክል መስራቱን በጥንቃቄ መገመገም ትልቁ
ሃላፊነታቸው ነው። በዚህም መሰረት መረጃዎችን አሰባስበው አገራቸውን ሊጠቅም ይችላል ብለው የሚያምኑበትን የፓሊሲ ሃሳብ
ያቀርባሉ። በዚህም ምክንያት የካናዳ የሰብዓዊ መብቶች ንዑስ
የውጭ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ
ኢትዮጵያውያንን በማሳተፍ ስለ አገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ ለማዳመጥ በጁን 11/2024 መድረክ ፈጥሮ ነበር። ስድስት ኢትዮጵያውያን
ነበሩ እንዲገኙ የታሰበው። የአማራ ተወካይ አለመጋበዙ ስለታወቀ፤ በአማራ ማህበራት በተደረገው የቅሬታ ዘመቻ አማራ እንዲወከል ተደረገና
ሰባት ኢትዮጵያውያን ተሳተፉ።
1.
ዶ/ር ዪናስ ብሩ ከአሜሪካ በቪዲዮ ተካፍለዋል። በአለም አቀፍ ተቁዋም
ባለቸው ልምድ፣የአብይ አህመድ አማካሪ ስለነበሩና በቁዋንቁዋ ችሎታቸውም የህዝብ ተወካዮቹን ቀልብ ስለሳቡ ብዙ ጥያቄዎች ቀርበውላቸው
የሚያምኑበትን ሃሳብ ለማራመድ የተሻለ እድልና ጊዜ አግኝተዋል።
ይሁን እንጂ ዶ/ሩ እንደተለመደው ስለባውንና
ግፍ አይፈሬዎቹን አንድ ላይ እንደ ወዳጃቸው መራራ ጉዲና አጃምለው ሲከሱ ተደምጠዋል። የዘር ፍጅት በአለም አቀፍ ገለልተኛ አካል እስካልተረጋጋጠ ድረስ
በኢትዮጵያውያን አክቲቪስቶች የሚቀነቀነው ተቀባይነት የለውም በማለት፤ የብልጽግና፣የኦነግንና የወያኔን የዘር ማጥፋት ወንጀሎች
ወደ ጎን ሊተው ፈልገዋል። ካለነገር አይደለም። እንዲህ የሚያደርጉት አብዛኞቹ የኦሮሞና የትግሬ ፖለቲከኞች በደም የተጨማለቁ
በመሆናቸው ወደፊት ከፖለቲካ መድረኩ ይገለላሉ ብለው በመስጋት ነው። የጀዋር መሃመድ አፍቃሪ መሆናቸውና ባልደራስ ለዴሞክራሲንም
ፀረ-ኦሮሞ ነው ብለው መፈረጃቸው ከዘር ፍጅት ክህደታቸው ጋር
የሚስማማ ነው። ከቅርቡ እንኩዋን ብንነሳ በአማራ ላይ የዘር ማጥፋት የተጀመረው በወልቃይት በወያኔ(በአረጋዊ
በርሄ/የዛሬው የአብይ ሹመኛ) ሲሆን ቀጥሎም በአሶሳ
በኦነግ፣በወያኔና በሻእቢያ ነው። ወያኔ ስልጣን ከያዘ በሁዋላም ሆነ በአብይ ፋሽታዊ አገዛዞች በእቅድ የተካሄዱት የዘር ማጥፋቶች
በሚገባ ተሰንደው ለተባበሩት መንግስታት የስብአዊ መብቶች ድርጅትና ለአለም አቀፍ የወንጀለኛ ፍርድ ቤት ቀርቡዋል።
ክሱ እንዳይንቀሳቀስ የተደረገው
ኢትዮጵያ በፍርድ ቤቱ ልትዳኝ ስለማትችልና(አባል አይደለቺም እንደ አሜሪካና እስራኤል)፤ ጉዳዩን ለፍርድ ቤቱ ለመምራትም
የፀጥታ ምክርቤቱን ይሁንታ ማግኘት ከባድ ስለሆነ ነው። የገንዘብ ችግር የለም። ኢትዮጵያውያን ለጠበቃ የሚሆን 350 ሺህ ዶላር
አዋጥተናል። ዮናስ ግን የተዋጣው ብር ለሌላ ጉዳይ እንዲሆን ይስብካሉ። በአገኙት አጋጣሚም ለክሱ አስፈላጊውን ሰነድ ያዘጋጁትን
ሻለቃ ዳዊትን ስም ያጠፋሉ። እስክነአካቴው ወልቃይትን
ለኤርትራ፣አስብን ለትግሬ ስጥቶ ወደብ ማግኘት እንደሚሻል ሃሳብ ያቀረቡ፤ ህሊናቸውን ከጫማቸው ስር እየረገጡ የሚሄዱ አማራ ጠል
ክፉ ሰው ናቸው። በዚህ ሃሳብ መቃረሚያ መድረክ ላይ አማራ የሚጠቅም ነገር ይናገራሉ ተብሎ አይጠበቅም።
ሌላው የዘር ፍጅት ክሱ ሂደት ያልተጀመረው
እስራኤልን እንደ ከሰሰው፤ ደቡቡ አፍሪካ አገር አይነት ማግኘት ስላልተቻለ ነው። የሆኖ ሆኖ ብሄረተኞች በአማራ ላይ የዘር
ማጥፋት ዘመቻ ፈጽመዋል። በቀደም የኢትዮጵያ የሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ ም/ሊቀመንበር ፤ ዘንድሮ “የእናት ሆድ እንኩዋን
መሸሸጊያ አልሆን” ያለበት ዘመን ነው ብሎው እቅጩን ተናግረዋል። “ወላሂ ከእንግዲህ አማራ አልሆንም”! የሚለው ተማጽኖ የሚነገረን
የዘር ፍጅቱ በአማራ ላይ ያተኮረ፤ ሆን ብሎ የተደረገና የተቀናጀ መሆኑን ነው። ዩናስ የዘር ፍጅት ከሃዲ ናቸው።
2.
ከሰባቱ ሶስቱ የትግራይ ተወላጆች ናቸው። ወጣቱዋና ሽማግሌው የወያኔ
ደጋፊዎች ናቸው። ይህቺ ወጣት ደመግቡና ጥሩ እንግሊዘኛ የምትናገር ናት። ግን ከአፍዋ የሚወጣው የሚያስፈራ የክፍት መርዝ ነው።
ምእራብ ትግራይ! ደቡቡ ትግራይ! ወይም 40% የትግራይ ግዛት በአማራ ተይዞአል ትላለች። መልእክትዋ ግልጽ ነው። የአማራን ዘር
ከመሬቱ እያጠፉ ወልቃይትንና ራይን በትግሬዎች መተካት አማራጭ የለሽ የፖለቲካ አቅጣጫ መሆኑ ነው። ሽማግሌውም ከርሱዋ የተለየ
ነገር አላቀረበም። የቁዋንቁው ችሎታ በጣም የደከመ በመሆኑ ጊዜውን አባክኖአል።
3.
ሶስተኛው የትግራይ ሰው ዮሃንስ በርሄ ናቸው። በታዛቢነት ነው የተገኙት። ሁሉንም የትግራይን ሃጢያት ለወያኔ አሽክመውታል።
የወያኔ ደጋፊዎችን የቅጥፈት አስተያየት አክብረው ሃቃቸው ግን
አራምባና ቆቦ እንደሆነ መስክረዋል። በአማራና በትግራይ ህዝብ መካከል ያለውን የባህል ትሥስርም እንዲሁ በበጎነቱ አይተውታል።
በትግራይ ርሃብ እንዳለና የትግራይ ህዝብም በአብዛኛው ከትግራይ እየተሰደደ በሌላው የኢትዮጵያ ክፍል ሲኖር ማንም እንደማይነካው
አስረድተዋል። ይሁን እንጂ ዩሃንስ ትንሽ ጊዜ ስለነበራቸው
የወልቃይትንና የራያን ጉዳይ ገፋ አድርገው ማንሳት ቢችሉ ኖሮ የበለጠ የወያኔዎችን የከሰረ የጥላቻ ፖለቲካ እርቃኑን ሊያስቀሩት
በቻሉ ነበር።
4.
ሌላው ተናጋሪ አቶ ስማነህ ናቸው። ያነበቡት ፅሁፍ አዲስ ነገር ባይኖረውም ለአማራም ለኢትዮጵያም
ክፍት ያለው አይደለም። አቶ ስማነህ ግን ለተጠየቁት ጥያቄዎች በቂ ምላሽ መስጠት አልቻሉም። የአገሪቱ መሰረታዊ ችግር ምንድን
ነው ተብለው ሲጠየቁ ግራ በመጋባታቸውና ጆሮዬ አልረዳኝም.. ስላሉ አቶ አስረደው ተቀብለው በጎሳ ፌዴራስሊዝሙ ያለውን እንከኖች በመጠቀስ
ጥያቄውን መልሰዋል። ስማንህም ከአስርደው ቀጥለው አስርደው ያሉትን ደግመዋል።
5. አቶ ስማነህ ለምን አማራ በፕሪቶሪያው ስምምነት እንዳይጋበዝ ተደረገ? ተብለው ሲጠየቁ ደግሞ፤ ያለመጋበዙን ምክንያት ለመረዳት “ከአቅሜና ከአቅማችን ውጭ” ነው ሲሊ አስደንጋጭ መልስ ሰጥተዋል። እንዴት? ለዚህ ጥያቄ ብዙ መልሶች መሰጠት ቢቻልም፤ አንዱ ለምሳሌ፤ በሰሜኑ ጦርነት የአማራው የተዋጊ ኃይሎች ያሳዩት የመዋጋት ስልት፣ የገነቡት አቅም፣ያስመለሱት አፀመ እርስታቸውና የአብይ አህመድ መከላከያም በጦርነቱ ጌዜም ይሸርብ የነበረውን ሻጥር የተረዱ በመሆናቸው [1]፤ ለኦሮሞ የፖለቲካ ስልጣን መርጋት ከወያኔ ይልቅ አደጋ የሚመጣው አቅም ከአለው አማራ ነው ተብሎ በኦሮሞ ፖለቲከኞች ስለታመነ ነው። የኦሮሞ ፖለቲከኞች አማራ ለኦሮሞ ክፉ የፖለቲካ ተቀናቃኝ ነው ብሎው ስለሚያስቡ ከወያኔ ጋር ስልታዊ ትሥስራቸውን መበጠስ ባለመፈለጋቸው ነው አማራን ከፕሪቶሪያ ያገለሉት። ከአማራ ጋር ወያኔን መውጋት ጊዚያዊ(ታክቲካል) ህብረት ነበር። ጦርነቱ ካበቃ በሁዋላ ግን በኦሮሞ መዳፍ የገባውን ወያኔ የአማራ የጎን ውጋት ማድረግ የኦሮሞ ፖለቲከኞች የፖለቲካ ቀመር ሆኖ አሁን እያየነው ነው። ይኼን ጥያቄ መመለስ በጣም ቀላል ነበር። አቶ ስማነህ ባይሳተፉ ኖሮ ይኼ ጥያቄ መልስ ሳያገኝ አይቀርም ነበር። ጥያቄው ሊቀርብ የሚገባውም ለአማራ ተወካይ ነበር። ባክኖአል።
6.
የአማራው ተወካይ የአማራን ጉዳይ ለማስረዳት ችሎአል። የህዝብ ተወካዮችን
ቀልብ እንደ ዶ/ር ዮናስ ግን አልሳበም። አንድ ጥያቄ ብቻ ነው የተጠየቀው። አማራ በፕሪቶሪያው ስምምነት ለመሳተፍ ያደረገውን
ጥረቶች ማስረዳት ችሎአል። ይሁን እንጂ ለእውነት የቀረበ ቢሆንም ፋኖ 90% በላይ የአማራ ክልልን ተቆጣጥሮአል ማለት የተአማኒነት
ችግር ሊፈጥር ይችላል። 75% ነው በተደጋጋሚ በፋኖዎችም ሲደመጥ የሚሰማውና።
በመጨረሻም..የአማራ ማህበራት
በኮሜተው ፊት የቀረቡትን አስተያየቶችና ጥያቄዎች የሚያጠራ አጭር ዶክመንት አዘጋጅተው ለፓርላማው አባላት ማቅረብ ይገባቸዋል።
ለመናገር የሚሰጠው ጊዜ በጣም አጭር በመሆኑ ሰው ሁሉ የልቡን ለማለት ያውም በባእድ ቁዋንቁዋ ፈታኝ እንደሆነ ተስተውሎአል።
ደንበኛ ዝግጅት ያስፈልጋል። የተጻፈውን ማንበብ ብቻ ሳይሆን ሃሳቡን በሚገባ ማላመጥና ምንስ አይነት ጥያቄዎች ሊነሱ ይችላሉ
የሚል ቅድመ ዝግጅቶች ለወደፊቱ መደረግ አለባቸው።
[1] ሻለቃ ምሬ(ምህረት) ወዳጆ እንደነገረን ፋኖ ከወያኔ ጋር በሚዋጋበት ወቅት በጀግነት የሚዋጉትን ፋኖዎች አብይ አህመድ
የመከላከያን ሰላዮች እያስረገ ሌላ ጦርነት በሚካሄድበት ጊዜ ያስገድል ነበር።
Comments
Post a Comment