እስክንድር ነጋና አማራ

እስክንድር ነጋና አማራ

አንድ ለመንገድ /3/ … ባለፈው አንድ ለመንገድ/2ኛ/ ዳሰሳ፤ \እስክንድረ ነጋና አማራ/ ከእስክንድር ስራ የተወሰደ መሆኑን ገልጫለሁ።አሁን ወደ መጨረሻው ሶስተኛው ክፍል ደርሰናል። ዳሰሳውን ዘርዘር አድርጌ ያቀረብኩትም እስክንድር እንዴት ስለአማራ ህዝብ እንደሚጨነቅ የጻፈውን ስራ ለማስተዋወቅ ነው። ያነሳሳኝ ጉዳይም  ባለፈው ወር በህብር ሬዴዮ አንድ የፋኖ ‘ቃለ አቀባይ ነኝ’ ባይ መስሪ ወይም ደንቆሮ ስለ እስክንድር የተናገረውን ፍሬፈርስኪ ካዳመጥኩ በሁዋላ ይኼ የእስክንድርና የፕሮፌሰር መስፍን ሙግት ‘ለቃለ አቀባዩም’ ለተቀረው አንባቢ ግንዛቤ ይሰጣል በማለት ነው።

አንድ ለመንገድ /3/  እስክንድር ነጋና አማራ

እስክንድር በኮሚኒስቶች መስፍርትም ቢኬድ አማራ ጎሳ/ብሄር/ማህበረሰብ ለመባል፤ከአምስቱ መስፍርቶች፤ የጋራ ቁዋንቁዋ፣ስነልቦና ታሪክና መሬትን ያሙዋላል ይላል። የማያሙዋለው የጋራ ኢኮኖሚ ነው።

በኢንዱስትሪ የዳበረ ኢኮኖሚ እንኩዋን አማራ ኢትዮጵያም ስለሌላት፤ ነገድ ለመባል የኢኮኖሚውን መስፍርት ማሙዋላት አይጠበቅበትም።ኮሚንስቶችም ሁሉም መስፍርቶች መሙዋላት አለባቸው አይሉም። ይሁን እንጂ ከመስፍርቶቹ መቅረት የሌለበት የጋራ ስነልቦና ነውና በዚህ ረገድም የአማራ ነገዳዊ ማንነት አሌ የሚባል አይደለም።

እስክንድር ገሪማ ታፈረ( የታዋቂዊው ፊልም ሰሪ ኃይሌ ገሪማ አባት) ስለ አማራ 25 ዓመታት ሙሉ ያጠኑትን አለቃ ታዬ የሚባሉትን ሊቅ በመጥቀስ እ.ኢ.አ 1973 የጻፉትንም ያጋራናል።

ገሪማ አለቃ ታዬ አማራ የሚባለው ህዝብ ትውልዱ ከሴም ልጅ ከኤቦር ነገደ ዮቅጣን መሆኑን አረጋግጠዋል ይላሉ።ጥናታቸውም የተመረኮዘው፤ በአለም ታሪክ ተመራማሪዎች ስራ(ኢዘንበር፣መልዚ፣ፓስቴንና ቫንሲን)፣ከመልኩ(የፊቱ አወራረድ፣የአፊንጫው ቀጥታ፣የአይኑ ቦግታ፣የቁመቱ ዘለግታ፣የጸጉሩ አለሳለስ፣የአካሉ ሞገስ በጣም ደስ የሚያሰኝ ባለግርማ ነው)፣ ከጠባዩ(ኩሩ ስለሆነ እንደአባቶቹ ወግ ቅዱስና እርኩስ የተባሉትን እንስሳት በመብላትም ሆነ በመንካት ጥንቁቅ ነው)፣ከስሙ፣ከስመ ሃገሩ፣ከቁዋንቁው(ዐማራ የሚነጋገርበት ቁዋንቁዋ አማርኛ ይባላል። ...መነገር የጀመረበትን ዘመን አጣርቶ ለማወቅ አልተቻለም። ሆኖም ቀዳማዊ ምንይልክ በነገሰበት(ከክርስቶስ ልደት በፊት) ዘመን 12 ቁዋንቁዋዎች እንደበሩና አንዱም አማርኛ ነበር ይባላል።)፣ከአምልኮው፣ከግዝረቱ መሆኑን ያስረዳሉ።

እስክንድር በ16ኛው ክፍለዘመን ወደ ኢትዮጵያ መጥተው መጻህፋቸውን በጣና ሃይቅ በምትገኝ ጎርጎራ ገዳም የጻፉትም ፓርቹጋላዊ አላሜዳን ዋቢ በማድረግ፤ የንጉሰ ነገስቱ ግዛቶች ፤ ትግሬ፣ደምብያ፣በጌምድር፣ጎጃም አማራ፣ከፊል ሸዋና(ሰሜን ሸዋ ማለታቸው ነው) እና እናርያ ናቸው ማለታቸውን ጠቅሱዋል።

እንግዲህ በገሪማ ታፈረ ስራም ይሁን ከአላሜዳ የምንገነዘበው ቁም ነገር አማራ የሚባል ህዝብ በታሪክ እንደነበረ ነው።

ለነገሩ ዛሬም ቢሆን በደቡቡ ወሎ አማራ ሳይንት የሚባል አገር አለ።ይኽ በእንዲህ እንዳለ፤ ፕሮፌሰር መስፍን አማራ የሃይማኖት መጠሪያ ነው ከዚያ ባሻገር ሌላ ቅጥያ የሰጠው ወያኔ ነው ከሚሉት ጋር በግልጽ የሚቃረን ነው።

ከዚህ በተጨማሪ ፕሮፈሰሩ የህዝቡ ትክክለኛ ስሜት አማራ ሳይሆን፤ ወሎዬነቱ፣ጎንደሬነቱ፣ጎጃሜነቱ እና ሸዋነቱ ነው ቢሉም፤ እውነቱ ግን ለምሳሌ ከአላሜዳ ስራ እንደምናየው ጎጃምና ወሎ የሚባሉ ስሞች የረዢም ጊዜ ታሪክ እንዳልነበራቸው ነው። ጎንደር የሚባል ከተማ እንጂ ክፍለሃገር እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ፈጽሞ እንዳልነበር የአላሜዳም ሆነ የመላው ኢትዮጵያ ታሪክ ምስክር ናቸው። እንደ አላሜዳ ከሆነ በኢትዮጵያ ውስጥ ትልቁ ክፍለ ሀገር ሆኖ የኖረው ቤጌምድር ነበር። ወሎ የሚባለው አካባቢም እስከ 1928 የኢታሊያ ወራራ ድረስ በጣም ትንሽ ቦታ ነበር።

ምንም እንኩዋን ፕሮፌሰር መስፍን የኢትዮጵያ ታሪክ በሰሜኑ ክፍል ተገድቦ ያልነበር እንደሆነ ለማሳየት የአጼ አምደጽዮንና የአጼ ሰርፀድንግልን ገድሎች ዋቢ ቢያደርጉም፤ በገድለ ነገስታቱ ውስጥ  አማራ እንድ ክፍለሃገር መጠቀሱን ግን አላማንሳታቸው፤ አማራ ወደ ሃይማኖት ይጠጋል የሚለው መከራከሪያቸውን ስለሚያፈርስባቸው እንደሆነ የማይታበል ሃቅ ነው። በተግባርም ዝም ነው ያሉት።

በተጨማሪም በገድለ ነገስታቱ ውስጥ ጎንደርና ወሎ የሚባሉ አገሮች አንድም ቦታ አለመጠቀሳቸው የሚያሳየው አካባቢዎቹ የትናንትና ስሞች መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ነው። የእነዚህ የአካባቢ ስሜቶችም ካለም የትናንት ነው። ይሁን እንጂ ስለ አካባቢ ስሜቶች የምንነጋገር ከሆነም ማንሳት ያለብን ፕሮፌሰሩ እንዳሉት ስለጎንደር፣ስለጎጃም፣ስለሽዋና ስለወሎ ብቻ ሳይሆን፤ ታሪካዊ የስነልቦና ትሥስር ስላላቸው ስለበጌምድር፣ስለሰሜን ጎጃም፣ስለዳሞት፣ስለላስታ፣ስለዋግ፣ስለየጁ፣ስለሸዋ፣ስለሳይንት፣ስለጠገዴ፣ስለወልቃይት፣ስለጠለምት፣ስለ ወሎና ወዘተረፈ፣እያልን መዘርዘር የግድ ይሆናል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ጎንደሬ ነኝ፣ወሎዬ ነኝ ብሎ የሚኮፈስ ቢጌምድሬ፣ሳይንቴ፣ላስቴ፣የጅዬ ወዘተ ካለም ማንነቱንና ታሪኩን በጥልቀት የማያወቅ ሰው ብቻ ነው።

እስክንድር ነጋ አማራ ከክርስቶስ ልደት በፊት የነበረ ጥንታዊ ህዝብ መሆኑን ለማመልከት ክርስትና ወደ ኢትዮጵያ ከመግበቱ በፊት ከአማሮች የአክሱም ነገስታት መካከል፤ 10ኛው ንጉስ ሳንካ፣ 2ኛው መኮነን፣ 53ኛው ቀዳማዊ ሚኒሊክ፣108ኛው ሰናይ፣110ኛው ዳዊት፣112ኛው በማውል፣115ኛው አሞይን ዘርዝሮአል። በዚህም ረገድ የአማራ ህዝብ ከክርስትና ልደት በፊት ከነበረ አማራ ማለት ክርስቲያን ማለት ነው የሚለው ውሃ የማይቁዋጥር ጉዳይ ነው ሲል አስረግጡዋል።

በመጨረሻም እስክንድር ፕሮፌሰር መስፍን በኢትዮጵያ ፖለቲካ ተጽእኖ የሚያሳድሩ፣እውቀትና ትምህርት የማያንሳቸው ሰው፤ አንድም በቂ ማስረጃ ሳያቀርቡ አማራ የለም ማለታቸው ትልቅ ውዥንብር ከመፍጠሩ በላይ ድርጊታቸው የክህደት ነው ሲል በቁጭት ያጠቃልላል። ይኼም ቢሆነ ከመጻሃፈቸው/የክህደት ቁልቁለት ሌላ ጠቃሜ ነገሮች ስለሚገኙ ቢነበብ ክፍት የለውም ባይ ነው።



[1] ድል ለዲሞክራሲ እስክንድር ነጋ 2013



[1] ድል ለዲሞክራሲ እስክንድር ነጋ 2013

Comments

Popular posts from this blog

የፋኖ አንድነት እንዴት?

እስከ ስባት ትውልድ!

አሞላቃቂ ጥቅመኛ!