መለስ ብዬ ሳየው... (ቦጋለ ካሣዬ)
..."ጥሩ ገንዘብ እዛ የተማሪ እግር ኩዋስ ሜዳ ውስጥ ገብታለች! ሂድና ቶሎ ይዘሃት ና!" ወረፍ ሳይበዛ እንሄድ!" የአቡ እናት የተለመደ ትእዛዝ ነው።
የጥሩ ገንዝብ እናት ከአህይት ሌላ የተለየ ስም ሳይወጣላት ጅብ በላት። ጥሩ ገንዘብ... ገና አሃዱ ተብሎ ከጀርባዋ ላይ ጭነት ያረፋባት ቀን እንደሌሎች ልትለግም ይቅርና ... አልፋ ተርፋ... የአህዮች ፊት መሪ በመሆኑዋ ነው ጥሩ ገንዝብን የመሰለ ስም ከአቶ አሳዬ የተቻረቺው።
ወረፋው ደግሞ የወፍጮ ቤቱ ነው። ጋሽ መሃመዶ ይባል ነበር ተቆጣጣሪው። በጣም ደግ ሰው ነበር። መቼም በህይወት ሊኖር አይችልም.... እድሜ እንደ ማቱ ሳላ ተለግሶት ካልሆነ።
.."አንተ አቡ ቆይ! ቆይ! የጋሼ አሳዬ ልጅ አይደለህ? አዎ! አህያዋን(ጥሩ ገንዘብን) ነጭ ለባሾች ስንቃቸውን ጭነውባት ሄደዋል በለው! አይዚህ አይቆጣኽም!
ነጭ ለባሽ የአገር ፀጥታ ሲደፈረስ ከመደበኛ ሰራዊት ውጭ ሰላም እንዲይስከብር የሚጠራ ዘማች ነው። ነፍጠኛ የሚሉት ነው። አማሮች ብቻ አይደሉም ታዲያ። ሰላሌዎችና ጉራጌዎች አሉበት።
ነጭ ለባሽ የአገር ፀጥታ ሲደፈረስ ከመደበኛ ሰራዊት ውጭ ሰላም እንዲይስከብር የሚጠራ ዘማች ነው። ነፍጠኛ የሚሉት ነው። አማሮች ብቻ አይደሉም ታዲያ። ሰላሌዎችና ጉራጌዎች አሉበት።
ባሌ ጎባ ድሮ ጠሃይ ከጠለቀ በሁውላ ድቅድቅ ባለ ጨለማ ነው የምትዋጠው። ሰማዩ ካልዳመነ ግን ከዋክቦቶችዋ የሚሰጡት ብርሃንና በተለይ ተወራርዋሪዎቹ የሚሰሩት ትእይንት ታይቶ የሚጠገብ አይደለም። ወቼ ጉድ ...አንድ አውራጃ ሙሉ አገር ከዋክብት ለማየት እንድንችል የመንገድ ዳር መብራት እንዳይተከልበት! ብለው አሻፈረኝ ያሉት የፍሪዢያን ፈርንጆች... ደሜን ከደማቸው በመቀላቀሌ ይሆን? ስለ ከዋክብት ሳነሳ ትዝ አሉኝ። ከዋክብትን ማየት ማራኪ ነው።
ጎባ የእዛን እለት ግን ዝናብና ደመና ነው። ይህም ሆኖ ድሮ ከጎባ በስተደቡቡ በጭራሽ በጨለማ የማይታየው የፋሲል ተራራ በአካባቢው በሚንቀለቀል የእሳት ብርሃን ወለል ብሎ ይታያል! ነጭ ለባሽ ነው! የሽፍቶችን ቤት የሚያቃጥለው። ጦርነት ነው! የአቡ እናት ያለቅሳሉ! ..''ሰው ተቃጥሎ ይሆን? ወየው እናቶቼ! ወየው ልጆቼ! ምን በጃቸው?"
... መለስ ብዬ ሳየው.... ነፍስ ካወኩ ጀምሮ ኢትዮጵያን የማውቃት የግጭት አገር ሆና ነው... ሰላም ለኢትዮጵያ!

ይቀጥላል.
Comments
Post a Comment