መለስ ብዬ ሳየው…2
መለስ
ብዬ ሳየው…..
ከቦጋለ ካሣዬ
ነጭ
ለባሽ ሽፍታን ለመውጋት ዘምቷል። አዝማቹ ጣሊያንን በአርበኝነት ያርበደበዱት ጀግናው ፍታውራሪ ተገኔ ተሰማ ናቸው። ወንድማቸው
ካፒቴን አጥሬ ተሰማ፤ ኢጣሊያ ተሸንፎ በማፈግፈግ ላይ እያለ አሳደው ከሰብስቤ ዋሻ ላይ በመማረክ እንደከብት አርደው ደሙን መጠጣታቸውን
ድፍን ባሌ ያውቃል። የነ ከተማም አህያና ቆፍጣናው አጎቱ ዘምተዋል። የአጎቱ ሚስት ዘነበች ጉርሙ መሬት ይቅለላትና በሳንባ
ነቀርሳ በልጅነቱ የተቀጨውን ብዙየን፤ ባሉዋ በዘመተ በሶስተኛው ቀን ወልዳ አራስ ናት። ለአራስ ጠያቂ ተገንፍቶ የሚተረርፈውን ገንፎ ከተማና የአጎቱ ልጅ ጉቱ እየበሉ፤ አፋችሁን ተግሞጥመጡ! ምች እንዳይመታችሁ! የሚሉት ማስጥንቀቂያዎችም ሆነ
ገንፎው ራሱ አንገሽግሾአቸዋል። የልጅ ነገር ሆዴን አመመኝ እንጂ መቼ በቃኝ ያቃል? ከበሉ በሁውላ ሮጠው ለመጫወት የሚሄዱት
የሰፈሩ ልጅ ሁሉ የሚሰበሰብባት ሆን ተብሎ ለእግር ካስ ሜዳ የተሰራች የምትመስለው ሜዳ ላይ ነው። የከተማና የጉቱ አያት ሜዳዋ
ሳር ስለምታበቅል ሳሩን አጭደው ከከመሩ በኋላ ዝናብ እስኪዘንብ ድርስ የሰፈሩ ልጆች ሜዳዋ ላይ ኳስ ቢጫወቱባትም ሆነ
የሩጫ ወድድር ቢያደርጉባት አይቆጡም። ሌላ ጊዜ ግን ውርድ ከራሴ
ነው! ድርሽ ማለት የለም። የተያዘ በሳማ ነው የሚለበለበው።
ነጭ
ለባሽ ውጊያውን እያፋፈመው ነው። የእሳቱ ነበልባል ፋሲል ተራራን ከሩቁ ወለል አድርጎ ያሳያል። ከሜዳዋ ላይ የቃጠሎውን
ትእይንት ለማየት የሰፈሩ ልጆች ተሰብሰበው፤
ኸረ
ጎበዝ!
እህም
ነው!!
ሽፍታ
ጠግቧል
እህም
ነው!!
እንበለው!!
ልጆች
እንደዛ ሲፈነጥዙ እናቶቻችው፤"ኸረ እናንተ ልጆች ወደ ቤት ግቡ!"
"ወየውላቸው
ዛሬ!" በማለት ቢያስፈራሩዋቸው ማን ከቁብ ቆጥሯቸው?
ቃጥሎው
እየበረታ በሄደ ቁጥር ኸረ ጎበዛቸውም ይደምቃል። እንደ ጉቱ ያለው ሙጬ ደግሞ ፉክራ አዋቂ ነው።
«ዘራፍ!!
ቁርቢቱ ገዳይ!
ልቡ
የሞላ እንደገናሌ!
ሳይቆሰቁሱት
አይውጣም አውሬ!» እያለ ያዳምቃል። ጉቱ አይኑ እንደናቱ ሽውራራና ግራኝ ነው። መቼም ወርውሮ ይስታል ማለት ዘበት ነው።
አነጣጥሮ ድንጋዩ ላይ ትፍ! ትፍ! ይልበትና ሲለቀው ኢላማውን ጉዋ! ነው የሚያደርገው!
ከተማም
በኸረ ጎበዙ ዘፈን ዘሎ! ዘሎ! እሳቱም ጭል ጭል እያለ፤ ጭለማውም እያየለ በመምጣቱ ወደ ቤቱ መሄድ የግድ ሆነበት። ከቤቱ
ደጃፍ ሲደርስ እናቱ …
«ምን
ዉጧቸው ይሆን? እስከቤታቸው ተቃጥለው ይሆን?» እያሉ እንባቸው ዱብ! ዱብ ሲል ያያል። እሱም… «ምነው እሙ? ምን ሆንሽ?» ሲላቸው፤
ለማረሳሳት ዘወትር እንደሚያደርጉት ራሱን ዳበስ አድርገው፤...እህቱን፤ «ባዩሽ! አንቺ ባዩሽ! ብለው ተጣሩና ራቱን ሽጭው!
እግሩንም እጠቢው» ይሏታል። ባዩሽም እንደሌላው ቀን፤ «ምንቦጣኝ! ተቀጥሪያለሁ መስለሽ እንዴ?» ብላ አላግተመተመችም። ከቴም
ራቱን እስከዛሬ ከቆራስማው በቀር ባልተለየው ነጭ-ቢንዚን እያማገ አጣደፈው። ሆዱ ሞላ። አገር አማን።
ከተማን
አያቱም ሆነ አጎቱ ከሁሉም ልጆች አብልጥው ይወድታል። አያቱ ገና ስሙን ጠርተው ሳይጨርሱ፤ አቤት! አቤት! አብይ! መጣሁ!ብሎ ትንፍሹ
እስኪቆረጥ ድረስ ሮጦ አጠገባቸው ደርሶ ልብ ብሎ አዳምጦ መልክታቸውን ስለሚያደርስ ይወዱታል። አያቱ ድንች ተቀቅሎ በድልህ ወይም በተልባ እንዲበሉ ሚስታቸው እህተ ማርያም ቡሸን ሲያቀርቡላቸው ገና ሳይቀምሱ፤ “ከተማ!
ከተማዬ!” ብለው ነው የሚጣሩት። ከቴም ሮጦ አጠገባቸው ይደርሳል። ወዲያው እፍ.. እፍ.. እፍ፥ እያደረጉ አብርደው በተልባ
እያጠቀሱ ድንቹን በአፍ በአፉ ያጎርሱታል። ሌላ ጊዜ ደግሞ የበቆሎ እሽት ቅቅልም ሆነ ጥብስ ሲቀርብላቸው ይጠሩትና ያስገምጡታል።
አያቱ ያሽተውን በቆሎ ከቆረጡ በኋላ የሚጣፍጥ የበቆሎ አገዳ ሲያገኙም ከተማ!ብለው ጠርተው ቆርጠውና ልጠው ያበሉታል። ልጣጩንና
ቅጠሉን ደግሞ ለከብቶች ይስጣሉ። አጎቱ ደግሞ የከተማ አባት በስራ ብዛት በየአገሩ ስለሚዞሩ እንዳባትም እንዳጎትም ሆነው በጣም
ያቀርቡታል። አጎቱ ከጋሼ ይርጉ ሉካንዳ ቤት ጥሩ ስጋ አለ ማለትን ከሰሙ ገዝተው ይመጣሉ። ታዲያ የመጀመሪያውን ጥብስ አብረው
የሚቋደሱት የሚገርመው ነገር ከሚስታቸውና ከልጆቻቸው ጋር ሳይሆን ከታላቁ የወንድማቸው ልጅ ከከተማ ጋር ነው።
የኸረና
ዘመቻ ብዙም አልቆየ። የከተማም አጎት አቶ አድነው አንድ የምርኮ ጥርኝና አንድ ጉራቻ(ጥቁር) ባዝራዎች ይዘው ተመልሰዋል።
ጥርኟን ወዲያው ሽጧት። አሮጊት ናት። ለኮርቻም አትሆንም። ጉራቻዋ ግን አድነው አንድ ብር ከፍለው የአባባ አዳል ሃለሌ ስለመታት
በአመቷ ሴት ዳላቻ በቅሎ ወለደች። ከነጭ ለባሽ ዘማች ማንም ስው አልሞተም። አቶ አድነው ስለ ኸረና ዘመቻ ለከተማ ብዙ ነገር ነግረውታል።
አንዱ የማይረሳው ስለአክስቱ ባል አቶ ደርቤ የነገሩት ቅዥት ነው። አቶ ደርቤ በእንቅልፍ ልባቸው፤ «መጡብኝ! ደረሱብኝ! ከልሉኝ!
ኽረ ልጆቼን ላሳድግበት! ወይኔ!» እያሉ ሰለሚወተውቱ ፍታውራሪ ይሄን ሰምተው የኋላ ደጀን እንዲሆኑ አዘው ነበር አሉ። ይሁን
እንጂ ያም ሆኖ ፍርሃቱ ተጠናውቷቸው ስለቀረ፤ ማታ ዘማቹ ሲሰፍር የርሳቸው ቅዥትም ለዘማቹ ትልቅ መሳለቂያና መዝናኛ በመሆኑ አቶ
አድነው ወዲሁም ጋብቻ ስለሆኑ ስለ አቶ ደርቤ ሆነው በጣም ያፍሩና ይሽማቀቁ ነበረ።
አድነው
ከተማን እንደትልቅ ሰው ቆጥረው፤ «ደርቤ? ቡኬ! ፈሪ! ነው። ሰው እንዳይመስልህ» ይሉታል።
ከተማም
ያንን ከሰማ በኋላ የአክስቱን ባል የሚመስል ሰው ሁሉ ሲያይ ፈሪ ይመስለዋል። እርሱም ከአቅሙ ጋሽ ደርቤን እንደሰውም ቆጥሮት
አያውቅም። ጋሽ ደርቤ ከከተማ አክስት ሁለት ቀያይና ቄጠማ የመሳሰሉ ሴት ልጆች ወልደዋል። ወንድ ልጅ ለመውለድ ከአክስቱ
ሞክረው ስላልተሳካላቸው ሌላ ሴት በድብቅ ወሽመው ወንድ ልጅ መውለድ ችለው ነበር። የከተማ አክስት ይኸን ስምታ “ደርቤ ወንድ
ልጅ ስለማይበረክትለት ተውት ደግ አደረገ” ብላ ትዳራቸው ቢቀጥልም ጋሽ ደርቤ ወደ አዲሱዋ ሚስታቸው ቀልባቸው ስላደላ ትዳራቸው
ፈረሰ። ጋሽ ደርቤ ከዚያ በሁዋላ በኑሮው ተቆሳቁሎ ነበር። ጋሽ ደርቤ አቅሙን አያውቅም እያሉ የከተማ አባት አቶ ካሳሁንም ሆነ
የአቶ ካሳሁን የልብ ጓደኛ አቶ ንጉሴ ሲያሟቸው ከተማ ያዳምጣል። ደርቤ በብር 10 ብርሌ ጠጅ ከመጠጣት ይልቅ በብር አራት
የሚሽጥ፤ ከጠላ የማይሻል ቅራሪ ቢራ የሚባል ስለሚጠጣ ለጋባዥ አስቸጋሪ ነው። አቅሙን አያቅም እያሉ ያሟቸዋል። ጋሽ ደርቤ
ፈሪ፣ወንድ ልጅ ፈላጊና አቅሙን የማያወቅ!...... ይቀጥላል
Comments
Post a Comment