Posts

Showing posts from 2014

አማራ፣ ኦሮሞ፣ ሰብአዊ መብቶችና ድርጅቶቻቸው

                              አማራ፣ ኦሮሞ፣ ሰብአዊ መብቶችና ድርጅቶቻቸው የደላቸው... የሰው ልጅ ይቅር፤ ማንኛውም ህመም ሊሰማው የሚችል ፍጡር አይጠቃ! አይገደል! ብለው እሪ! እሪ! ይላሉ። ያነባሉ። እንቅልፍ አይወስዳቸውም። የሌሎች ስቃዮች እነርሱንም ያስቃያቸዋል። አንዴ ተማሪ እያለን የደብረ-ብርሃንን የብርድ ልብስ ፋብሪካ ልንጎበኝ ሄድን። አስተማሪያችን ፕሮፌሰር ፓንዲታ የሚባል ህንድ ነበር። ለምሳችን ስጋ ያለበት ሳንዱውች ተዘጋጅቶአል። የደብረብርሃን ብርድ ለጠኔ ዳርጎን ነበርና ሰፍ ብለን ሳንዱቻችንን መግመጥ ጀመርን። አስተማሪያችን ግን ከንፈሩ ደርቆ አይን አይናችንን ያየናል። ለመብላት ፈልጎአል። "ለምን አትበላም?" ብለን ብንጠይቀው፤ "ስጋ አልበላም። እምነቴ ማንኛውንም ፍጡር አትግደል ይላል።" ብሎን እርፍ! በሆላንድ የእንሳስት መብት ተሙዋጋች የፖለቲካ ፓርቲ አለ። አሁን ዳች ፓርላማ ውስጥ ሁለት መቀመጫዎች አሉት። ፓርቲው መሬት ማንኛውንም የሰው ልጆች ፍላጎቶች ለማሙዋላት ትችላለች። ይሁን እንጂ የሰዎች ስግብግብነትን ለማሙዋላት አትችልም ብሎ ያምናል። እንደ ፓርቲው ከሆነ ለምሳሌ የእንስሳትና እንስሳት ተዋጽኦ እንዱስትሪ፤ 30% በተፈጥሮ ይገኙ የነበሩ የእንሥሣትና የእጽዋት ዘሮችን በማጥፋት ተጠያቂ ነው። ከብቶችንም ለማደለብም ሆነ የወተት ጎርፍ ለማምረት መኖ በገፍ ስለሚያስፈልገው፤ በዚህም ሳቢያ መሬት ከድሃ ገበሬዎች ስለሚቀማ፤ የአለም ርሃብ እየተባባሰ የመጣበት አንዱ ዋናው ምክንያት ከእንስሳትና እንስሳ ተዋጾእኦ እንዱስትሪ ተግባር ጋር የተያያዘ መሆኑን ያረጋግጣል። በተጨማሪም የእርድ እንሳሳት ሲታረዱ ...

ኤድስ የመጣብን ከወያኔና ከሻእቢያ ጋር ተቀናጅቶ ነው!

ኤድስ የመጣብን ከወያኔና ከሻእቢያ ጋር ተቀናጅቶ ነው! በቅርቡ የወያኔ-ትግሬ አገዛዝ መራዊን በኤድስ እንዳጠቃው የተሰራጨውን መረጃ ያነበቡ ሁለት ነርሶች የሚሉት አላቸው። እንደ ነርሶቹ ከሆነ በኤድስ ሕዝብን ማጥፋትና መበከል የተጀመረው ደርግ ወድቆ ወያኔና ሻእቢያ ስልጣን ከያዙ ቀን ጀምሮ ነው። ነርሶቹ ዛሬ በአውሮፓ ነዋሪዎች ናቸው። ቀደም ሲል በጎንደር ሆስፒታልና በበለሳ የጤና ጣቢያዎች የሰሩ ናቸው። እንደነርሱ ከሆነ በተለይ የኤድስን ቫይረስ ያስረጩ የነበሩት በበሽታው የተበኩሉት ኤርትራውያን የሻእቢያ ወታደሮች ነበሩ። ብዙዎቹም የሻእቢያ ወታደሮች በበሽታው መሞታቸውን ይናገራሉ። ጉዳዪም በቶሎ ስለተደረሰበት በጎንደር በሽታውን እንዴት መከላከል እንደሚቻል በቂ ትምህርት በወቅቱ ይሰጥ እንደነበር ነርሶቹ ተናግረዋል። ተመሳሳይ ትምህርት ግን በጎጃም ስለመሰጠቱ መረጃ የላቸውም። በሌላ በኩል ጋይንት ውስጥ ወያኔ-ትግሬ ህዝቡን መርፌ በመውጋት በኤድስ ማጥቃቱን ያልተረጋገጡ ምንጮች ይጠቁማሉ። ኸረ ለነገሩ ኤድስን ለመከላከል በጎንደር ይሁን በሌላው ኤትዮጵያ የተሰጠው ትምህርት ምን ያህል ተከታታይነት አለው? ወያኔና ሻእቢያ ስልጣን ከያዙ 23 አመታቸው ነው። በዚያኔ ለአቅመ አዳም የደረሱት ሊጠነቀቁ ይችላሉ። ተከታታይ ትምህርትና ምክር ግን ለታዳጊው ከወላጆቾች፣ ከሃይማኖት አባቶችና ተቁዋሞች ካልተሰጠው አደጋው ሊረሳ ይችላል። ለኤድስ መዳህኒት ተገኘ ከተባለ በሁዋላ እንኩዋን በአውሮፓ ሰው ዘና ማለት በመጀመሩ ብከላው አልጠፋም። ዛሬም ሰዎች ይጠቃሉ። በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዘመን ረሃብ በወሎና በትግራይ ገብቶ ሰዎች እያለቁ ነው በመባሉ፤ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አስተማሪዎች፤ እንደ ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌና ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያ በቦታው ሄደ...

‘ጄኔራል’ ወያኔ፤ በአማራ ጥላ መደንበር እስከመቼ?

“ስምና ቁንጫ ባዶ ቤት ይወዳል” ይሉ ነበር አበው። ካለነገር አይደለም። የወያኔ-ትግሬ ሰራዊት በቁጩ(fake) ጄኔራሎች የሚመራ ነው። አብዛኞቹ መደበኛ የሚሊትሪ ሳይንስ የተከታተሉና ልምድ ያላቸው አይደሉም። ስብሃት ነጋና መለስ ዜናዊ የሾሙዋቸው ተጋዳላይዎች ናቸው። ልምዳቸውና ጀብዱዋቸው ያው አማራ ገዳይ! እያሉ መፎከርና ደርግን አሸነፍን! እያሉ ለ23 ዓመታት የቀጠለው አደንቁሮታቸው ነው። እንደ እውነቱ ከሆነ ደርግ ራሱን በራሱና በቀዝቃዛው ጦርነት ማክትም ምክንያት፤ ርዳታ ለማግኘት ባለመቻሉ፣ እንዲሁም አሜሪካኖችም መንግስቱ ከስልጣን እንዲወርድ ስለፈለጉና ስለሰሩ ነው የወደቀው። ደርግ እንኩዋንም ወደቀ። እሺ… ወያኔ-ትግሬ ደርግን አሸንፈሃል ብለን እስኪ ሃራይ! ሃራይ! ሐቂ እዩ!! እንበልለት፤ ከበሮ እየደለቅን… ደስ እንዲለው። ታዲያ የወያኔ-ትግሬ ጄኔራሎቹ ቁጩ ካልሆኑ፤ ለምን በሰራዊቱ ውስጥ ከ62 ጄኔራሎች ውስጥ 57ቱ ትግሬዎች ሆኑ? ቁጩ ካልሆኑ እኮ በሰራዊቱ ውስጥ ለምሳሌ ከ62ቱ  30 ተጋሩዎችንም ቁልፍ የሰራዊቱን ስልጣን አስይዞ የዘር መድሎውን ስርዓት ለማስቀጠል ይቻል ነበር። ይኼ ግን ሲሆን ለምን አናይም? በተለይ ወያኔ ትግሬ ለምን በሰራዊቱ ውስጥ ለወሬ ነጋሪ አንድ አማራ ጄኔራል ቢኖር ከስልጣን ያባርረዋል? ያውም ይኼም ጄኔራል ከወያኔ-ትግሬዎች የተለየ ትምህርትና ልምድ እንዳለው የሚታወቅ ነገር የለም። ነገሩ ግልጽ ነው። ወያኔ-ትግሬ ከዐማራ ሕዝብ ሆነ ከተቀረው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር የማይታረቅ ቅራኔ ውስጥ ስለገባ በፍርሃት እየጠንቀጠቀጠ ነው። ይኽ ሁሉ የፍርሃቱ ነጸብራቅ ነው። ዓማራን በተለይ እርቦት በአጎረሰው እጁን ነክሶታል። መሬቱን መሬቴ ነው ብሎ ነዋሪውን እያተገረው ይገኛል። ያፈናቅለዋል። ያመክንዋ...

ስግብግቡ ወያኔ-ትግሬ !

ከ24 ዓመታት በሁዋላ ወደ አገሬ ስመለስ፤ ተለውጦ ሳይሆን ብሶበት ያገኘሁት በእድፍ ሳቢያ የሚተነፍግ የአውቶብስ ውስጥ ሽታ ነው። አውቶብሱ መቼም የማይጭነው ነገር የለም። አንዳንዱ ሎሚ ገዝቶ እያሽተተ ይጉዋዛል። አብዛኛው ግን ትንፋጉን ተላምዶታል። እኔም ዋጥ አድርጌ ተላመድኩትና ቆሎዬን እየበላሁ ወሬዬን እየሰለኩ ተጉዋዝኩ። ይኽ የስንፍና ሳይሆን የድህነት ምልክት ነው። ሕዝቡ በቂ ውሃ አገልግሎት አግኝቶ ቢሆን ኖሮ፤ መሬት የራሱ ሆኖ፤ ኑሮውን እንዲያሻሽል የወያኔ-ትግሬ አገዛዝ አፈናቅሎ መሬቱን ለባእዳን ባይሠጥበት ኖሮ፤ የትንራስፖርቱም ሆነ የሌላው ንግድ በወያኔ-ትግሬ ሞናፖሊ ስር ባይወድቅ ኑሮ፤ በአጠቃላይ አድሎ የሌለበትና ውድድር የሞላበት ስርአት ቢኖር ኖሮ፤ የሕዝቡ የኑሮ ደረጃ በራሱ ጥረት ከፍ ሊል ይችል ነበር። ወያኔ-ትግሬ ግን ለራሱ ቀፈት ሳንቲም ከመልቀም ሌላ ለሕዝብ ሁለንተናዊ እድገት ሃጃ የለውም። የዛሬ የወያኔ-ትግሬ የባንዳ ልጆች ስግብግብነት፤ ከደጃጅ ውቤ ቅንቅን ጋር በጣም ይመሣሰላሉ። መይሳው ካሳ ትግራይን ሲያስገብሩ፤ የትግራይ ህዝብ ለአስከፊ ረሃብ ተጋልጦ ነበር። ታዲያ የውቤ ሰፈር በቁጥጥር ስር ወድቆ ሲፈተሽ እጅግ ብዙ የተከማቸ እህል ይገኛል። ቴዎድሮስ ..”ይኽን ሁሉ እህል ለመቼ ነው በል ያስቀመጠከው?” ቢሉዋቸው፤ “ለክፉ ቀን ነዋ!” ብለዋቸው እርፍ። የእብድ ቀን አይመሽም! ..”ከዚህ የበለጠ ክፉ ቀን አለን?” ብለው ቴዎድሮስ ለተራባው ህዝብ እህሉን እንዲከፋፈል ትእዛዝ ሰጡ። አጼ ምንይልክ ከአድዋ ጦርነት በሁውላ፤ የትግራይን ድህነት አይተው፤ ለማንኛውም ድሃ እንደሚያዝኑት ሁሉ ያደረጉት ነገር ምንድን ነበር?፤ …” ማሪያምን ሃረርጌን ለትግሬ ስጥቻለሁ” ነበር ያሉት። ራስ መኮንን ተከትለው ብዙ ትግሬዎች ወደ ...

ኢትዮጵያዊ ነኝ። ትውልዴ ከሰሜንም ከደቡብም ነው። ዘሬ ለተገፉት ያደላል። አዎ! ዛሬ ዓማራ ነኝ።

ኢትዮጵያዊ ነኝ። ትውልዴ ከሰሜንም ከደቡብም ነው። ዘሬ ለተገፉት ያደላል። አዎ! ዛሬ ዓማራ ነኝ። በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ የሚከሰቱትን ጉልህ ችግሮችና መደረግ የሚገባቸውን መፍትሄዎች በድፍረትና በአደባባይ የተናገሩትና ያቀረቡት፤ እስክንድር ነጋ፣ በቀለ ገርባ፣ ፍሬሕይወት አለሙ፣ አንዱ አለም አራጌ፣ ኣብርሃ ደስታና ሊሎችም ቃሊቲ እየማቀቁ ናቸው። ብዘዎችም ተሰውተዋል። ተሰደዋል። ዛሬም በአገር ቤት ድምጻቸውን ካለፍራቻ የሚያሰሙ ብዙዎች አሉ። ውጤት ግን አልተገኘም። ፖለቲካ ወደድክም ጠላህም በትንሹ ፤ ማን ጥሩ ትምህርት፣ሥራ፣ ጤና፣ ቤት፣ሃብት ወዘተ ያግኝ ወይስ አያግኝ የሚለውን ፖሊሲ ነዳፊና አስፈጻሚ ነው። ሕይወታችን በሙሉ በአገርም ሆነ በአለም-ዓቀፍ አድሎአዊ ፖለቲካ ምርጫዎች የተጠነፈገ ነው። ኢትዮጵያውያን የፖለቲካ ችግራችን ስላልተፈታ ዛሬም ፈራ-ተባ በሚል ትግል ላይ ነን። በአገራችን ስልጣን ዛሬም አልተገራ። ጭራሽ ሊገራ ቀርቶ፤ የስልጣን ወንጀሎችን ለመስማትም ሆነ ለማመን አስቸጋሪ ሆኖአል። የፖለቲካ ጉዳያቸውን በስነስርአት የፈቱ አገሮች፤ ስለ ፖለቲካ ትዝ የሚላቸው ምርጫ ሲደርስ ብቻ ነው። ፖለቲካም አስቸጋሪና ውስብስብ ሙያም ስለሆነ፤ እውቀት፣ዝግጅትና ራእይ ያለው እንጂ ማንም እንደ ወያኔ-ትግሬ አይነት ወሮበላ ገብቶ አያንቦጫርቅበትም። ወያኔ-ትግሬ፤ ወያኔ ስሙም ትግርኛ ስለመሆኑም እርግጠኛ አይደለሁም። ለቁዋንቁዋ ተናጋሪዎች ጉዳዮን እንተወውና፤ ወያኔ አብዮት ነው የሚለውን ትርጉም ለመቀበል አዳጋች ቢሆንም በመዝገበ ቃላት ሰፍሮአል ሲባል አንብቤያለሁና አብዮት ነው እንበል። ሰለዚህ ወያኔ-ትግሬ ሲባል የትግሬን የዘረኛ አብዮት የሚያንቀሳቅስ ድርጅት ማለት ነው። አብዮት ደግሞ በአመጽ የፖለቲካ ለውጥ ማ...

ወያኔ-ትግሬ፤ መራዊን በኤድስ ቀጣው!

Image
                                   ወያኔ-ትግሬ፤ መራዊን በኤድስ ቀጣው!                      ከአሻግሬ ይግለጡ(የብእር)፤ መራዊ፤ መስከረም 2007 ፋሺስቱ የወያኔ-ትግሬ ሰርዓት፤ የመራዊን ወረዳ ህዝብ በኤድስ በሽታ እንዲጠቃ፤ ሁኔታዎችን በማመቻቸት የቂም በቀል እርምጃ መውሰዱን ሁነኛ ምንጮች አጋለጡ። መራዊ በምእራብ ጎጃም የምትገኝ ወረዳ ናት። በ1997 በተደረገው አገራዊ ምርጫም እንደ ድፍን ጎጃም ሁሉ ነዋሪዋ ቅንጅትን መምረጡ ይታወሳል። “…በዚህ ቂም የያዘው የወያኔ-ትግሬ ፍሽት አገዛዝ፤ ከራሱ ጦር ውስጥ በኤድስ ቫይረስ የተጠቁትን ወታደሮች መርጦ ምንም የፀጥታ ስጋት በሌለባት መራዊ ወረዳ ካምፕ ሰርቶ ያሰፍራቸዋል። ከዚያም ወታደሮቹ ሴተኛ አዳሪዎችንም ሆነ በገንዘባቸው ሊያዞምቱ የሚችሉትን ሌሎችን መገናኘትና ብሎም መበከል ይጀምራሉ። በዚህም የተነሳ በአጭር ጊዜ ውስጥ ቁጥሩ ያልታወቀ ሰው በበሽታው ሊጠቃ ችሎአል።   ዛሬ በመርሃዊ ብዙ ሰው የኤዴስ በሽተኛ መሆኑን በአይን አይቶ መመስከር እንደሚቻል እነዚሁ በቅርቡ ወደ ቦታው ሄደው ያዩ የአይን ምስክሮች አረጋግጠዋል።” ከዚህ ቀደም እ.ኢ.አ በ2000 ዓ.ም በጎጃም ማቻክል ወረዳም፤ አማራውን በክትባትና በኪኒን ስም በማምከን ፋሽቱ ወያኔ-ትግ...

ግንባር? ውህደት? እየተስተዋለ!

       ግንባር? ውህደት? እየተስተዋለ!                 ‘ነጻነቴን ከኢሳያስ መንጋጋ አገኘዋለሁ ማለትህን ተወኝ!’                         ቦጋለ ካሣዬ (አምስተርዳም ኦገስት) በኢሳያስ አፈወርቂ ‘እየተደገፉ’፤ ወያኔን ከስልጣን ለማስወገድ የትጥቅ ትግል እናካሄዳለን የሚሉ ሶስት ድርጅቶች አንድ ግንባር ለመፍጠርና ወደፊትም ለመዋሃድ መስማማታቸውን በቅርቡ የግንቦት-7ቱ ኢሳት በሰበር ዜናው ነግሮናል። የዲያስጶራውም ሰሞነኛ መነጋገሪያ ነጥብ ሁኖአል። ከዜናው ትንሽ ቀደም ብሎ የኢሳቱ ዋና ሰው ፋሲል የኔአለም፤ የወያኔ መውደቂያው ዶርሶአል ሲል ተቁነጥንጦ በፊስቡኩ ላይ የለጠፈው የመልካም ምኞት ብስራት፤ ፍጥምጥሙ ያለቀ ጉዳይ መሆኑን ያመላክታል። ዜናው ወያኔ በማንኛቸውም መንገድ ተወግዶ ለማየት ለሚሹ ገራገር ኢትዮጵያውያን ክፋት ያለው አይደለም። ሌላም ሰው ቢሆን ጭቆና ባለበት የትጥቅ ትግልን ማስቆም እንደማይቻል ስለሚገነዘብ፤ ተዋጊዎቹ ግንባር መፍጠራቸውን ክፉ ነገር ነው! ብሎ ቢያንባርቅ የፖለቲካ ሀሁ ያልገባው ቂላቂል ተብሎ ሊቆጠር እንደሚችል አይስተውም። ለነገሩ ጠላት አይናቅምና፤ ግንባሩን እንደ ክፉ ነገር ሊያይ የሚገባው ወያኔ ይሆን እንዴ? ‘ናይ ፖለቲካ ናጽነት አይኮነን ሆድ ናጽነት !’ በቅርቡ ወያኔ መጪውን ምርጫ ተከትሎ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን ...

እኛ ተማሪ እያለን.... ሕንድ በዛ!

                    እኛ ተማሪዎች እያለን፤ ሕንድ በዛ ! እ . ኢ . አ በ 1964 ነው። ባሌ ጎባ ነው አገሩ። ትምህርት ቤቱም አዝማች ደግለሃን ይባል ነበር። ከ 7 ኛ እሰከ 12 ኛ ክፍል የሚከታተሉ ተማሪዎችን የሚያስተናግደበት፤ ከድንጋይና ከእንጨት የተሰሩ ክፍሎችም ነበሩት። ተራራ ብቻውን ታሪክ የሚሰራ ይመስል፤ ታሪካዊ ስሙ በደንቆሮው ደርግ ጊዜ ተፍቆ ባቱ ተራራ ተብሎአል። ታዲያ በዳግልሃን ት / ቤት ውስጥ ሕንዶች በዙ ! ተባለ። አሁን ልብ ብዬ ሳየው፤ ‘ ሕንዶች ’ እንላቸው የነበረው፤ ፊሊፒኖችንም ጭምር ነው። አንድ ሕንድ ወይም ፊሊፒኖ አስተማሪ በአንዴ ሂሳብ፣ጆግራፊ ወይም ታሪክ እንዲያስተምር ይመደባል። እንግሊዠኛና ሂሳብ የሚያስተምሩም ነበሩ። አንዳንዶቹ አስተማሪዎች በቂ ዝግጅት ስላልነበራቸው ሽምድደው የመጡት ነገር ጥያቄና መልስ ከጎበዝ ተማሪዎች ሲያስነሳ ብስጭት ውስጥ ይገባሉ። ወይም በነገ ይደር እየተባለ ጥያቄዎች ሳይመለሱ እንዲረሳሳ ያደርጋሉ። እኛ ገና የሰባተኛ ክፍል ተማሪዎች ነበርን። ከኢትዮጵያውያን በስተቀር አንድም የውጭ አገር ዜጋ እኛን እንዲያስተምር አልተመደበም። ታዲያ ከላይ የሆነውን ያወጋዋችሁ፤ ሕንዶች በዙ ! ጥሩ አስተማሪዎች ስላይደሉ፤ እነርሱ ሊያስተምሩን አይገባም። ሌላ ጥሩ አስተማሪዎች ይመደቡልን፤ እያሉ የዳግለሃን የተማሪዎች ካውንስል ከተማሪዎች ጋር ...