አገር ቤት ደርሶ መልስ....
ባህርዳር... እንደ ደረስን ወደ ሆቴላችን በባጃጅ ለመሄድ ሃሳቡ ነበረን። ሻንጣችንን ከመኪናው ላይ ያወረደው ልጅ ግን፤ ..."ጋሼ እኛ ባጃጅ የሌለን ምን ስርተን እንብላ? ሆቴላችሁ እዚህ ቅርብ ነው። ኑ ተከተሉኝ"!.... እንዳለውም አምስት ደቂቃም ሳንራመድ ደረስን። እውነቱን ነው። አሳዘነኝ። አንድ ወዳጄ እንዳጋጣሚ ለስራ ጉዳይ እዚያው ባህርዳህ መጥቶ ሆቴል ይዞ ስለነበር... ጣና ባህሩ ዳር ወስዶ ጥሩ ራት ጋበዘን። ይሁን እንጂ ልጄ አይነቱ በዛበት መሰለኝ... አሞት አደረና በሚቀጥለው ቀን ያቀድነው ፕሮግራም ሊካሄድ አልቻለም። እኔም መጽሃፍ እያነበብኩ ከሆቴሉ ሳልወጣ ዋልኩ። አንድ ዘመድም ስለነበረኝ ረፋዱ ላይ የርሱን ልጆች ላይ ሄድኩኝ። በማግስቱም ጥዋት የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ የባህርዳር ጽ/ቤት ካረፍኩበት ሆቴል ቅርብ ስለነበር ሰተት ብዬ ሄጄ ተዋወኩዋቸው። የፖለቲካ ፕሮግራማቸው ገና አልቆ ስላልተበተነ ላገኘው ባልችልም፤ በመሬት የግል ይዞታና በኢትዮጵያ የወደብ ጥያቄ ላይ ጥሩ የሃሳብ መለዋወጥ አድረግን። ስለ አብንና አዴፓ ግንኙነት በሚመለከት ከነርሱ የተሰጠኝ መልስ ግን ስጋት ውስጥ ጣለኝ። አዴፓ አብንን ለማጥፋት እንደሚሰራና አብን በህዝቡ ድጋፍ ብቻ ህልውናው ሊጠበቅ እንደቻለ አስረዱኝ። አዴፓ ያሰረባቸውን አባሎቻቸውንም ህዝቡ እንዳሰፈታቸው ነገሩኝ። ይኼንኑ ስጋቴን አዲስ አበባ ተመልሼ እኔ አባል ለሆንኩበት የአማራ ህልውና የኢትዮጵይ አንድነት ድርጅት ሰዎች ነገርኩዋቸው። የአማራ ህልውና ለኢትዮጵይ አንድነት አመራሮች ከሁለቱንም ከፍተኛ የፖለቲካ ድርጅቶች አመራሮች ጋር ተነጋግረዋል። ድርጅቶች እየተቀራረቡ ሲመጡ ሊፈታ የማይችል ምንም አይነት ጉዳይ እንደማይኖር ነው የሚያስቡትና እን...