አገር ቤት ደርሶ መልስ...
አገር ቤት ደርሶ መልስ...
ከስምንት አመታት በሁዋላ ኢትዮጵያ ደርሼ ተመለስኩ ። ብቻዬን አልሄድኩም። ጎረምሳውም ዘንደሮስ ተለይቼህ አልቀርም ስላለ ሁለት ራሴን ሆኜ ነው የሄድኩት።
በቶሮንቶ አለም አቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ የኢትዮጵያን አየር መንገድ ዴሪም ላይነር ለመሳፈር... በተሽከርካሪ ወንበር ላይ የተቀመጡ ስድስት አሮጊቶች ተገፍተው ቀደም ብለው ገቡ። አንድም በሚገፋ ተሽከርካሪ ወንበር ላይ የተቀመጡ ሽማግሌ ባለማየቴ ይመስለኛል ...አንድ ትዝብት ትዝ ብሎኝ ብቻዬን ፈገግ አልኩ። እንዲህ ነው ነገሩ። ..."አባቶቻችንና እናቶቻችን ይጨቃጨቃሉ። በተለይ ውሃ ቀጠነ ብለው ነገር የሚያነሱት ብዙውን ጊዜ አባቶቻችን ናቸው። ታዲያ እግዚአብሄርም ይኼን አየና... እነሱን ቀድሞ በመውሰድ እናቶቻችን ቀሪውን እድሜያቸውን እፎይ ብለው እንዲያሳልፉ ያደርጋል ይባላል።" እነሆ በድሪም ላይነር የሰሜን አሜሪካ ክረምት ሲገባ ወደ ኢትዮጵያ...ሲወጣ ደግሞ ወደ አሜሪካ እየበረሩ እፎይ ማለት ነዋ! እናቶች ይመቻችሁ! አባቶችም አደብ ግዙ!
በአሊታሊያ፣ በአሜሪካ፣በካናዳ፣በኬኤሌም፣ በሉፍንታዛና በብሬትሺ ኤር ወይስ በተደጋጋሚ በርሬያለሁ። በእነዚህ አየር መንገዶች ውስጥ አንድ የጎላ ፊት ይታያል። አብዛኛው ተሳፋሪ ፈረንጅ ነው። አልጠላውም። ግን ብቸኝነት ይሰማኛል። በኢትዮጵይ አየር መንገድ ስበር ሁለተኛዬ ነው። የተሳፋሪው ፊት.... አፍሪካውያን፣እስያውያና ፈረንጆችንም ስለሚያካትት አለም አቀፋዊ ነው። በዚህም መሰረት በበረራ ወቅት የባይተዋርነት ስሜት በጭራሽ አይኖርም። በመቀጠልም የደስ ደስና ትህትና ያላቸው እህቶቻችን ለአዋቂ ይሁን ለልጆች ተሳፋሪዎች የሚያሳዩት እንክብካቤ የሚደነቅ ነው። ምንም የመሰልቸት ፊት አያሳዩም። በተጠሩ ቁጥር ከነፈገግታቸው ከች ነው የሚሉት። ከአስራ ሁለት ሰአት በላይ አየር ላይ ተንጠልጥለን አዲስ አበባ ገባን። 'የገዛ አገሬን' ቪዛ ገዛሁና እቃዬን ይዤ ልትቀበለኝ የመጣቺውን እህቴን እዚያው ከአውሮፕላኑ ጣቢያ ሳልወጣ አገኛታለሁ ብዬ አስቤ ነበር። በሁዋላ እንዳየሁት ለካስ እንግዳ ተቀባዮች የፀሃይ ይሁን የዝናብ መጠለያ በሌለው አውላላ ሜዳ ላይ እንዲንቃቁ ተደርገዋል። ይኼ በምንም መስፈርት ተቀባይነት የለውም። መንቃቂያ ሜዳው ጥሩ ጥሩ ሱቆች ሬስቶራንቶች የስፖርት መስሪያዎችና የመሳሰሉት ተሰርቶበት ከዋናው የቦሌ አየር ማረፊያው የመሳትወት ግድግዳ ጋር ቢጋጠም እንግዳ ተቀበዩም ሆነ እንግዳው አይጉላሉም። በብዙ የአውሮፕላን ማረፊያዎችም የሚደረገው ይኼው ስለሆነ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ክፍሎች መፍትሄ ሊፈልጉ ይገባል። በሌላ በኩል ከዚያው ከቦሌ ሶስት መቶ ሜትር ራቅ ብሎ አየር መንገድ የራሱን ተሳፋሪዎች ሊያስተናግድበት የሚችል ሆቴል እየሰራ መሆኑን አሳዩኝ። አንዳንድ ሰዎች እንደሚሉት አየር መንገዱ ከበረራ በተጨማሪ የሆቴል ንግድ ውስጥ ከገባ የሆቴል ነጋዴዎችስ ምን ሰርተው ይብሉ የሚል እሮሮ ያሰማሉ።
አዲስ አበባ የትራፊኩ ጭንቅንቅ አይጣል ነው። ምናልባት መኪና ለመንዳት አደገኛ ከተማ ሊባሉ ከሚችሉት ቀዳማዊነት የምትይዝ ይመስለኛል። ይሁንና ገና ጅምርም ቢሆን አሁን አንድ አጭሬ ባቡር አላት። ወደ ስራ ሲኬድና ሲመለስ ባሉት ሰአታት ባቡሩዋ በሰው እጭቅ ትላለች። ባለመኪኖች፣ታክሲ ነጂዎችና እግረኞች ደግሞ የባቡሩ ሃዲድ በዘፈቀደ በመዘርጋቱ ድሮ በአቁዋራጭ የሚያስኬዱት መንገዶች ሁሉ መተላለፊያቸው ስለተዘጋ... ወደ አንድ ቦታ ለመድረስ ዙሪያ ጥምጥም በመሆኑ ሰአትም ሆነ ነዳጅ ይባክናል እያሉ ይበሳጫሉ። መቼም ይኼን ችግር መፍታት ከባድ አይደለም። የውስጥ መሾአለኪያዎች መስራት አንዱ አማራጭ ሊሆን ይችላል። ከአራት ኪሎ ጆሊ ባር አንስቶ እስከ ትምህርት ሚኒስቴር መስሪያ ቤት የተሰራው አስቀያሚ ድልድይ አይነት ግን የከተማውን መልከጥፉነት የባሰ ስለሚያባብስ እንደመፍትሄ ተቆጥሮ ሌላ ቦታ ባይገለበጥ ይሻላል።
ላሊበላ
ላሊበላ፣ጎንደርና ባህርዳርን ለማየት ተነሳን። አራት ቁጥር ያለው ስልክ ደውለን የአውሮፕላን ትኬት እንደምንፈልግ አስታወቅን። ለሁለት ሰው አርባ ስድስት ሺህ ሶስት መቶ ብር ነው ሂሳቡ ተባልን። ዋጋው አክሱምንም የጨመረ ነበር። ይሁን እንጂ አክሱም ለመሄድ ተመልሰን ላሊበላ ወይም ባህርዳር መምጣት ስለነበረብን ጊዜ ማቃጣል አልፈለግንምና... ብሄራዊ ትያትር ፊት ለፊት ያለው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቢሮ የተሻለ አማራጭ ለመፈለግ ሄድን። እኔ በኢትዮጵይ አየር መንገድ በመብረሪ አምስት ሺህ የሞላ ብር እንኩዋን አትከፍልምተባልኩ። ልጄ ግማሽ የውጭ ደም ስላለውና በኢትዮጵያም አየር መንገድ ስላልበረረ የኔን ሶስት እጥፍ ዋጋ እንዲከፍል ተጠየቀ፡ ቀደም ካለው አርባ ስድስት ሺህ ብር ጋር ሳወዳድረው አክሱምንም ባይጨምር የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወኪል ነን ብለው ትኬት የሚሸጡ ድርጅቶች የሰው ገንዘብ በመቦጨቅ የተካኑ ሳይሆኑ አይቀርም ብዬ ተገረምኩ። ትኬታችን ከመቆረጡ በፊት ክፍያ ይቀድማል። ይሁን እንጂ ገንዘብ ተቀባይዋ አንድ ናት። ቢሮው ደግሞ ጭንቅንቅ ስላለ ግፊያው አይጣል ነው። ለመክፈል ተራ መጠበቅና ከማያውቁት ሰው ትንሽ ራቅ ብሎ መቆም በጭራሽ የሚታወቁ መሰረታዊ ስነ-ስርአቶች አይመስሉም።
አንድ ሰአትም ሳንበር ከአዲስ አበባ ተነስተን ላሊበላ ደረስን።ላሊበላ ሆቴል እንድናርፍ ምክር ተሰጠቶናል። ቱሪስቶችን ለመቀበል ያሰፈሰፉት ታክሲዎችና የየሆቴሉ የሰርቪስ መኪናዎች ጋር ጠጋ ስንል.... ላሊበላ ሆቴል እወስዳቸዋለሁ ባለን መኪና ላይ ተሳፈርን። ከሆቴሉ ያደረሰን ሰውዬም የተማረ የቱሪስቶች አስጎብኚ ስለነበር ወዲያው የላሊበላን ድንቅ የድንጋይ ፍልፍሎች ቤተክርስቲያናትንም ሆነ ማህረነ ክርስቶስን እንዲያስጎበኘን ተዋዋልን። በአስጎብኚው እውቅት እጅግም ረካን። ጎብኝታችንን ከጨረሰን በሁዋላ... ወደ አዝማሪ ቤት ባጃጅ ይዘን ሄድን። ፈረንጁ ሆነ አበሻው እየጨፈረ ግንባር ላይ ብር ይለጣጠፋል። ከምሽቱ አራት ሰአት ላይ ወደ ላሊበላ ሆቴል ባጃጅ ተከራይተን ሄድን። ባጃጁ ያደረሰን ሆቴል ግን እኛ ያረፍነበት አይደለም። እኛን ለካስ ላሊበላ ሆቴል ነው ብሎ የወሰደን ሰው ያስያዘን ሆቴል እንድናርፍ የተመከርነው ላሊበላ ሆቴል ሳይሆን ላል የሚባል ሆቴል ነው። ላል አገውኛ ነው። አስጎብኚው እንደሸወደን ስናውቅ ሳቅን። ብዙም አልከፋን በእውቀቱ ክሶናልና።
ጎንደር
ከላሊበላ ወደ ጎንደር ሰላሳ ደቂቃም አልበረርን። ወቅቱን ያልጠበቀ መጥፎ ዝናብ እየዘነበ ደረስን። እንደ አጋጣሚ ዶ/ር አብይና አቶ ኢሳያስ የመጡበት ቀን ስለነበር ጎንደር በወታደር ተጥለቅልቃለች። ጎንደርን ድሮም አውቃታላሁ። እምብዛም አልተለወጠች። የፋሲልን ቤተ መንግስት ከመጎብኘታችን በፊት ለሁለት ቀን ራስ ዳሽንን ለመጎብኘት ከንትራት ያዝን። በጥዋት ተነስተን ወደ ደባርቅ ከዚያም ወደ ስሜን ተራራ አቀናን። ከጎንደር ትንሽ ወጣ ብሎ ሸንኮር ወደ ሚባል ትምህርት ቤት ተማሪዎች ሲሄዱ አየሁና..." ሸንኮር ለምን ተባለ?" ብዬ ሹፌራችንን ጠየኩት። .."ከሸንኮራ አገዳ ጋር ሳይቆራኝ አይቀር ብለህ ጋሼ"? ብሎ ሲለኝ ሳቅ አልኩና..."ሊሆን ይችላል... ግን ሰሜን ሸዋም ሸንኮራ የሚባል አገር አለ። ሸንኮራ አገዳ ግን የሚበቅልበት አይመስለኝም። የሆኖ ሆኖ በአፍን ኦሮሞ... ሸን ማለት፤ አምስት ኮራ ደግም፤ ኮርቻ ሲሆን ስያሜውም ለአምስት ኮርቻ የሚመስሉ የተያያዙ ተራሮች የተሰጠ ሳይሆን አይቀርም" አልኩት የፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌን ስራዎች በማስታወስ።. ጎንደሬ የኦሮሞ ደም ደሜ ነው የሚለው እንደዚህ ካለው ታሪካዊ ትሥስር በመነሳት ነው ብዬ ፖለቲካውንም መሬት አስነካሁት። ገለጣዬ በጣሙን ተወዳጅነት አገኘ።
ደባርቅ ላይ አንድ ክላሽ የያዘ ጠባቂ፣ አንድ እንጊሊዘኛ የሚናገር አስጎብኚ፣ አንድ አብሳይና ረዳቱ ተቀላቀሉንና ወደ ስሜን ተራራ ፓርክ አመራን። ፓርኩ የዱር፣ለማዳ እንስሳትና ስዎችም የሚኖሩበት ነው። ወደፊት ነዋሪዎቹንና ለማዳ እንስሳቶቻቸውን ለማንሳት እቅድ እንዳለ አስጎብኛችን ነገረን። በመንገዳችን ላይ ባቡን ዝንጀሮች፣የተለያዩ ሚዳቆችንና በማየትና ተራራውን እያማተርን ጨነቅ ደረስንና ዋሊያ ለማየት የሁለት ሰአት መንገድ በእግራችን ሽቅብ ወጣን። አንድ ብቸኛ ዋልያ አየንና ቀርበን ለማየት ብንሞክርም አልተሳካም... ሸሽን። ወደ ማደሪያ ቦታችን እየተመለስን ሳላ ብዙ ዋሊያዎች ራቅ ብለው ሲንጎማለሉ አየንና ደስታ ተሰማን። ቀኑ ጉማማ ስለነበር ዋሊያዎቹ እንደልብ የሚታዩበት አልነበረም። ደግሞ መንገዳችን ላይ ሶስት ልጅ አገርዶች የደረቀ ጭራሮ ሰባብረውና ጠፍረው ወደ ቤታቸው ተሸክመው ሲሄዱ ደረስንባቸው። ለካስ እዚያው እየኖሩ ለማገዶ የሚሆን እንጨት መስበር ክልል ኖⶂአልና... አስጎብኛችን ክላሽ የታጠቀውን ጠባቂያችንን ሴቶቹን አግቶ መቆጣጠሪያ ጣቢያው ድረስ እንዲያደርሳቸው አዘዘው። እኔ አሻፈረኝ! አልኩ። እናንተ አሁን ስራችሁ የእኛ አስጎብኚና ጠባቂ ስለሆነ ልጆቹን ልታግቱ አትችሉም። እነርሱም ሁለተኛ አይለምዳቸውም..አይደል ልጆች?...በአንድ አፍ "አዎ ጋሼ"! እግዚአብሄር ያክብራቸው እገታው ቀረና ትተናቸው ሄድን። ዋሊያ ካየን አይቀር ጨነቅ ለአዳር ብርዱ አይቻልምና ወደ ሳንቃ በር እንሄድ ስላሉ ወደዚያው አመራን። ከጎንደር እስከ ደባርቅ ያለው መንገድ አሸዋ ፈሰስ አስፋልት ነው። የስሜን ተራራ መንገድ ግን ጠጠራማ ነው። ወደ ጨነቅም ስንሄድ ይሁን ከጨነቅ ስንመለስ ለመኪና በጣም አደገኛ የሆኑ ቦታዎች አሉ። አደገኝነታቸው ደግሞ በተፈጥሮ የመጣ ሳይሆን መንገዱ በደንብ ስላልተሰራ ነው። እንደውም ለመኪና አመቺ ያለሆነው ቦታ ላይ ፈረሥ አከራዮች አሉ። ሰው ይወርድና በፈረስ ቁልቁለቱንና አቀበቱን እንዲወጣ ያደርጋሉ። የእኛ ሾፌር ግን ደፋር ስለነበር ወደ ጨነቅ ስንሄድ ከመኪና ሳንወርድ ይዞን ወረደ። ስንመለስ ግን መኪናዋ ዳገታማና እጅግ ብልሹ የሆነውን መንገድ መውጣት ተሳናት። ወርደን አንድ! ሁለት! ሲስት! እያልን ገፍተን ዳገቱን አስወጣናት። ይኽ መንገድ የማይሰራው ያው በተንሰራፋው ሙስና ነው ይላሉ እጅግ በአስተዳደሩ የተማረሩር ጎንደሬዎች።
ሳንቃ በር ማደሪያ ተብሎ የገባንበት ቤት ውስጥ አምስት አልጋዎች አሉት። ሁለቱን አልጋዎች እስራኤልያውያን ይዘዋቸዋል። እኔና ልጄም ሁለቱን ያዝን። የቤቱ ወለል ሲሚንቶ ነው። ይቀዘቅዛል። አልጋውም የዛገ ነው። የምንቀመጥበት ወንበር የለውም። ከቤቱ ደጃፍ ግን የተነባበሩ የፕላስቲክ ወንበሮች አሉ። የማደሪያውን ሃላፊ .."እነዚህ ወንበሮች አይደሉም እንዴ?" ብዬ ጠየኩት። አንዳቸውም አይሆኑም ለመቀመጫ ተሰባብረዋል። ለመንግስት እንዲጠገኑ ብወተውትም እስካሁን አልተሰሩም" አለኝ። ..." እኔ አንተን ብሆን ኖሮ ራሴ እጠግናቸው ነበር" አልኩት። እጅግ የሚያሳፍር ነው መንግስት የተባለው ድርጅት ለሰው ልጅ ማደሪያ እንዲህ ያለ ከከብት በረት የማይሻል ቦታ መስራቱ። አሁን በል አልጋውን አንጥፍልን!" አልኩት።" እነቀው እነቀው አሰኘኝ ሰውየውን... የጸዳ ልብስ የለበሰና የተመቸው ቀብራራ ቢጤ ነው። ስለ ሽንት ቤቱ ከልጄ መረጃ ስለደረሰኝ ዝርም አላልኩኝ።
እራት እስኪደርስ ብሎ አብሳያችን ፈንደሻና የጦሲኝ ሻይ አፍልቶ ሰጠን። እስራኤልያውያኑ እንደኛ አብሳይ ይዘው አልመጡም። ጠባቂ ብቻ ነው ያላቸው። ምግብም የላቸው። ደግሞ አመጣጣቸው ለሰባት ቀን ነው። እንዲቁዋደሱን ጋበዝናቸው። ደስ ብⶀአቸው ሻይኑም ፈንደሻውንም በሉ። ይኼን ያየው አብሳያችን ግን አልተደሰተም። ጠጋ አለኝና ..."ጋሼ እናንተ ከፍላችሁ ነው። እንደነዚህ ያሉ ቱሪስቶችን እናቃቸዋለን። ገንዘብ አጥተው ሳይሆን ለማውጣት ስለማይፈልጉ ነው። ደግሞ ስትሰጣቸውም የሞኝነት ስለሚመስላቸው ፊት አለመስጠት ነው"! ብሎ ወደ ማብሰሉ ሄደ። ቀጥሎ ሾርባ መጣልን። በጣም ግሩም ነበር። ያበጠው ይፈንዳ ብዬ ሾርባም ሰጠናችው። ከዚያ ትዝ ሲለን እኛ ከጎንደር ዳቦና ፍራፍሬ ይዘን ስለመጣን እርሱን ሰጥተናቸውና ከአገረኞቹ ጋር ጥሩ ራት ከበላን በሁዋላ እሳት አንድደን ወግ ተጀመረ።
አብሳያችን በጣም ባለሙያና ተጫዋች ነው። አንዴ አለ... ኢዴስ ከመስፋፋቱ በፊት በልጅነቱ ቀልቡን የጣለባት ልጅ ቤት ሆን ብሎ ከመሸ እንግዳ ሆኖ ይሄዳል። ልጅቱዋ ደግሞ ቤቱዋንም ሆነ አልጋዋን ከአንድ ተማሪ ሴት ልጅ ጋር ተጋርታ ነው የምትማረው። ምን የመስለ ሽሮ ሰሩልኝና አብረብ በላን። አማራጭ ስለሌለ ሶስታችንም አንድ አልጋ ላይ ተኛና! ቀልቡ የጣለባትን ልጅ ..."ገና ዳሰስ ሳደርጋት...ኢው...ትንፋሹዋ ቁርጥ! ቁርጥ!..." ከዚያማ ምን ይጠይቃል። .."ታዲያ ከዚያች ሽጨርስ ጉዋደኛዋ ..በእርግጫ አትለኝም! አይ መታደል ልጅነት... እርሱዋንም ድግም! አየህ ዝምድና ቢኖራቸው ኖሮ አይቀናኝም ነበር!"
- አንድ ሰፈራችን ረጅም ሴት ነበረች። ደንዳናም ናት። ማንም ወንድ ካለፍላጎቴ ሊደፍረኝ አይችልም ብላ የምትኩራራ.... ታዲያ አንዴ ሳትስበው ሁለት እጆቹዋን የፍጥኝ አስርኩና አንደኛውን እግርዋን ትከሻዬ ላይ አውጥቺው ዓመቻቸሁዋትና....(ጠባቂያችን ጣልቃ ገብቶ እንደ እንግሊዛ!) ..የልቤን ላደርስ ስል ..." ደህና ዋላችሁ? ... እዚህ ቤት! የሚል ምቀኛ እንግዳ አያስጥለኝም!"። ጠባቁያችን አብሳዩን ታዝቦት .."ለካስ አንተ ለሚስትህ ታማኝ አይደለህም! እኔ አንድ ከፈረንሳይ የመጣች ቱሪስት አይታኝ ብትነፈርቅብኝ በጭራሽ ጋሼ ሚስት አለኝ ብዬ አሻፈረኝ አልኩ።"
- አንድ ደግሞ እንዲሁ አብሮን እሳት ለመሞቅ የመጣ የሌላ ቱሪስቶች አስጎብኚ ...አንዴ ሁለት የእንግሊዚ አገር ሴቶች ለማስጎብኘት አብሮ ይመጣል። ታዲያ አዳር ላይ እነርሱ ድንኩዋናቸውን ተክለው ይተኛሉ። እርሱ ማደሪያ ፍለጋ እንደሚሄድ ሲነግራቸው አብሮ ከእነርሱ ጋር መተኛት እንደሚችል ሲነግሩት ማመን ያቅተዋል። ከዚህም መካከላቸው ገብቶ ይተኛና ምንም ሳያደርግ...እንቅልፍ በአይኑ ሳይዞር ማደርሩን ሲነግረን ....አብሳዩ ..."ወይኔ! እኔ ብሆን ኖሮ! የሞትክ ሬሳ! ሳቅ በሳቅ! ከት! ከት! ነው!
- አንዱ አስጎብኚ ደግሞ አልጋ ይጠፋና ከአንድ እስራኤላዊት ቱሪስት ጋር በአንድ አልጋ ለመተኛት ይስማሙና ይተኛሉ። አጅሬ ታዲያ ቱሬስቱዋን መዳበስ ሲጀምር ትናሳና በቦቅስ አሩን ማብላት ትጀምራለች! የእስራኤል ወታደር ናት! ከት! ከት! ከት!
ፖለቲካ
መቼም የወያኔና ቀደም ሲልም የደርግ ግፍ ሰውን በፖለቲካ አብስሎታል። ስለ አለፉት ምርጫና ስለወደፊቱ ምርጫ የሚያስቡትን ጠየኩዋቸው። ..."ጋሼ..አንድም ቀን እኮ በምርጫ የምናቀውን ሰው መርጠን አናቅም። የመረጥነው ንብን ብቻ ነው!"...ከት ከት! በሚቀጥለው ምርጭ... እንተያያለን። አየህ ጋሼ የሚያስጠቁን እኮ የራሳችን ስዎች ናቸው። እስካሁን የተወሰደብንም መሬትም እናስመልሰው ነበር። እንዲሁም ጎንደር የአረፉኩበት ሆቴል ንቁና ትሁት አስተናጋጆች ጋር ስለ ጎንደር ብዙም አለመለወጥ ምክንያቱ ያው ሙስናና ወያኔ እንደነበሩና በመጪው ዘመን ግን የከተማውም እድገት ይሻሻላል ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉ አልሸሸጉኝም። ጎንደርን ከመልቀቂ በፊት አንድ ማየት ያለብኝ ቦታ እንዳለ ውስጤ ነገረኝ። የህዝብ አመጽ የተቀጣጠለበት የኮሎኔል ደመቀን ቤት! ባጃጅ ይዤ ደረስኩ። ውስጤን ደስ አለው። በአጠቃላይ ጎንደር ቢቆሳቆልም ሰው ቀጥተኛ ነው። የሚወደድ።
ወደ ባህርዳር
አሁን ቀጣዩ ጉዞ ወደ ባህርዳር ነው። የጎንድረ ከተማ መናኽሪያ ስምንት ኪሎሜትር ርቀት ላይ (አዘዞ) ተሽቀንጥሮአል። ከሃያ ደቂቃ በሁዋላ ወደ ባህርዳር ለመሄድ ይነሳል የተባለው መለስተኛ አውቶብስ..እስኪ ንቅንቅ...! ካልሞላ አልሄድም አይልም! ስድስት ሰዎች ሆንና .."አሁን ካልሄድክ ትንሽ መኪና ተከራይተን መሄዳችን ነው" ብለን አደምን። ..."ሃያ ደቂቃ ስጡኝ " አለን። ሰጠነው። መኪናው ሞላለት... ባህርዳር ደረስን።
ይቀጥላል

Comments
Post a Comment