አብይ አህመድ፤ ትን! ብሎት ግጥም ቢልስ?
ሳር ቅጠሉ፤ አብይ! አብይ! ሆኖአል፡፡ አማን! አማን አንዶም! ፤ መንጌ መንጌ! የተባሉበትም ጊዚያት ነበሩ፡፡ መለስ ዜናዊ መሌ ተብሎ አያቅም፡፡ ራሱም ባንዳና አያቱም ባንዳ ስለነበሩ እኛም እንደጠላነው እርሱም እንደጠላን አምላክ ጠራልን፡፡ አዎ...ድፍን ትግሬ ይወደው ነበር። ከዚያም ዱቤ መጣ፡፡ ዱቤ ማለቴ እርሱም ሆነ ሌላ ማንም ሳያስበው ጠቅላይ ሚኒስተር የመሆኑን ድንገተኛነት ለመጠቆም ነው፡፡ ሃይለማርያም በትምህርቱም ሆነ በተመክሮው ከማንም ባያንስም ጥርስ የሌለው አለቃ ሆኖ ወንጀልም ፈጥሞ ተሰናበተ፡፡
አማንን መንግስቱ በላው፡፡ መንግስቱም 17 የስልጣን አመቱን ሰው ሲገድልና በመፈክር ኢምፔሪያሊዝምን ሲደመሥስ፤ ስልጣን ህዝባዊ ይሆን ዘንድ ምንም ስራ ሳይሰራበት አለቀና ለስደት ተዳረገ፡፡ ለነገሩ ነው እንጂ ከመንግስቱ መቼም ዴሞክራሲ ይጠበቃል ብዮ አይደለም፡፡፡
ወያኔ ስልጣን በያዘ ማግስት የመንግስቱን ሰለባዎች እየሰበሰበ ማስለቀስ ጀምሮ ነበር፡፡ አንድ በጣም በሳል እመቤት ይኽንኑ ታዝባ፤ ለሃይሌ ገሪማ የሰጠቺው አስተያየት እስከዛሬ አይረሳኝም፡፡ ብዙም ሰው ግን የረሳው ይመስላል፡፡ እመቤቲቱ ምን አለች? ቃል በቃል ባይሆንም መልእክቱዋ....የእኛ ነጻ መሆን እኮ የሚለካው ደርግ በመውደቁ አይደለም። የሚለካው ሕዝቡ እውነተኛ የስልጣን ምንጭ ሲሆን ብቻ ነው ነበር ያለቺው። አረገቴ? አብይ! አብይ! አብዬዎች?
የፖለቲካ ባህላቸው ያልበሰለ ሰዎች ስሜት ይገዛቸዋል፡፡ ደግ ነው ብለው የሚይስቡት መሪ ላይ እምነታቸውን ይጥላሉ፡፡ አንድ ግለሰብ መሪ ግን እንደ ሸክላ ተሰባሪ መሆኑን ላንዳፍታም ያጤኑት አይስመስልም። እስኪ ዛሬ አብይ ትን ብሎት ቢያልፍ ነገ አገሪቱ ምን ትሆናለች? ሌላ አብይ እንደሆነ አይመጣም፡፡ ኢትዮጵያ እስካሁን ወደሁዋላ የቀረቺው ጠንካራ ህዝባዊ መሰረት ያላቸው ተቁዋማት ስለሌሎዋት ማንም ሃይለኛና ባላጊዜ እየተነሳ ህዝቡዋን ሊያሸብርና ሊያደናገር በመቻሉ ነው፡፡ ይኼ እንዲያከትም አብይ እስረኛ ከመፍታት፣ የታመመ ከመጠየቅ፣ በውጭ አገር ሄዶ በአማርኛ ከመናገርና ከመሳሰሉት ስሜት ከሚነኩ ነገሮች በላይ ወደ ስርአት ለውጥ ሊያመጡ የሚችሉ ተጨባጭ ስራዎች ላይ ማተኮር አለበት፡፡
አብይ ቀጥታም ባይነግረን ኢትዮጵያን በ 10 አመታት ውስጥ መለወጥ እንደሚቻል ጠቁሞናል፡፡ በሌላ አነጋገር ፓርቲውን ይዞ ገና ሁለት ምርጫ ለመዝልቀ ሃስብ አለው ማለት ነው? በመቶ ፐርስንት ባያሸንፍም 60 ፕርሰንት አሸነፍኩ እያለ ፍትሃዊ ባልሆነ ምርጫ ሊገዛ ይችላል፡፡ የዛሬ አስር አመት ግን አገሪቱ አሁንም በጠንካራ ተቁዋሞች ሳትደገፍ ከአብይ ለተሻለ ወይም ለባሰ ሰው ልትዳረግ ነው ማለት ነው፡፡
ምን ይጠበስ? አቦ እኝ አትበል ነው? እነ እምቡር እምቡሬ... አብይን በጥቃቅኑ ነገሮች ሁሉ ፤ አስከበረን! አኮራን! ከሚሉ ሙገሳዎች ወጥታችሁ፤ አብይ የደቡቡ አፍሪካው ዴክለርክ የተጫወተውን የሽግግር ሚና በኢትዮጵያም በእርሱ አመራር እንዲደገም ብተወተውቱት ከታሪክ ተወቃሽነት(ወቀሳ የሚያማችሁ ከሆነ) ልትድኑ ትችላላችሁ ነው፡፡

በተጨባጭም፤
1. ሁሉንም የፖለቲካ እስረኞች ይፍታ፡፡
2. ሁሉም የፖለቲካ ድርጅቶች፣ የአገር ሽማግሌዎችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ያቀፈ አገራዊ ጉባኤ እንዲጠራና ቢያንስ ለሁለት አመታት የሚቆይ የሽግግር መንግስት እንዲቁዋቂዋም ያድርግ፡፡
2.1 የሽግግር ወይም የአደራ መንግስቱ ብዙ ስራ ይኖረዋል፡፡ ዋና ተልእኮው ግን፤ አብይ የስልጣን ተፎካካሪዎች ብሎ የሚጠራቸው ሁሉ ተወዳድረው ህዝብ አደራ የሰጣቸው ስልጣን እንዲረከቡ ማድረግ ነው፡፡ እጅግ ወሳኝና አጣዳፊ ጉዳይ ነው፡፡ አብይ ይኼን ቀና መንገድ ካመቻቸ ለመጀመሪያ ጊዜ በታሪካችን እውነትም የሚያኮራና የሚያስከብር አገር ይኖረናል ማለት ነው፡፡ እርሱም በታሪክ የተከበረ ቦታ ይኖረዋል ፡፡
3. ይኼን ካላደረገ ግን የአብይ የጫጉላ ዘመኑ ቢበዛ ከስድስት ወር አያልፍም፡፡ ህዝብ ተስፋ የጣለበትን ካላየ ፊቱን ማዞርና ግንባሩን ማጨማደድ ይጀምራልና፡፡

Comments
Post a Comment