ለሰላማዊ የስልጣን
ሽግግር ሚሊዮኖች ወደ አደባባይ!
ቦጋለ ካሣዬ፤ አምስተርዳም ኦገስት 2014
በኢትዮጵያ
የስልጣን ሽግግር በሰላም ወይም
በጦርነት
ሊመጣ ይችላል ብሎ ውር’ርድ ውስጥ ሳይገባ፤ በሰላም ብቻ እንዲሆን ተግቶ መስራቱ የስልጣን ሽግግሩንም ሆነ ውጤቱን ስለማዊና ያማረ እንደሚያደርገው ሳይታለም የተፈታ ነው።
አሃዱ ሰላም
«ጠመንጃ
ደህናሁኝ!»
በማለት
ከዛሬ
23 አመት ጀምሮ፤ የስልጣን
ሽግግር
በኢትዮጵያ
ሰላማዊ
መሆን
አለበት
ብለው
ማስተማር
የጀመሩት
አንዱና
ዋናው
ሰው ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም
ናቸው።
ይኼን ያሉበት ብዙ ምክንያቶች ሊኖሩ ቢችሉም፤ አንዱ በሰሜን ኢትዮጵያ ባካሄዱት
የመስክ
ጥናቶች
በአገራችን የችጋርና
የርሃብ
ዋና
ምክንያት
የስልጣን አለመገራት እንደሆነ
ስለደረሱበት ነው ማለት ይቻላል። ስልጣንን
ለመግራት ደግሞ ሕዝብ ስለመብቶቹ እንዲያውቅ ማድረግ ሁነኛ ነገር ነው። ፕሮፌሰሩ በዚህ የተነሳ ይመስላል በተግባር
ኢሰመጉን
ከመሰሎቻቸው
ጋር
መስርተው
በኢትዮጵያ
ስለ ሰብአዊ መብቶች
ግንዛቤ እንዲያድግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረግ የጀመሩት።
ሰላማዊ ትግልና ድርጅቶች
“ማንን ትደግፋለህ ቢሉት?..መቸስ አይተን ወደ አደላው ነው እንጂ!”
እንዲሉ በትኩሱ ከሕዝባዊ ትግል ወደ አገዛዙ ሸርተት ካለው ኢዴፓና ብልጭ ብሎ ድርግም
ካለው
ቀሰተ
ደመና
በስተቀር፤
ትግላችን
ከሰላማዊ
መንገድ
እጥፍ አይልም በማለት
የቅርጽና
የይዘት
ለውጥ
እያደረጉ
በሰላማዊ
ትግል
ለውጥ
ለማምጣት
የሚንቀሳቀሱ
ድርጅቶች
አሉ። አባሎቻቸውና መሪዎቻቸው እስራት፣ከስራና
ከንብረት
መባረርና
መፈናቀል
ይሁን
ሞት
አልቀረላቸውም።
ሰላማዊ
ትግል የቅንጦት ወይም የፈሪዎች
ሳይሆን
እጅግ
የመንፈሰ
ጠንካሮች
እንደሆነ
የሚከፉሉት
መስዋትነት
መስካሪ
ነው።
ሕዝቡን
እስካሁን
ለስልጣን
አላበቁም
እንጂ
በጦርነት
እንታገላለን
ከሚሉት
የበለጠ
ስራና
አኩሪ
ታሪክም
አስመዝግበዋል። የማይናቅ ልምድ አካብተዋል።
በቅንጅትና
በሕብረት
ተሰባስበው
አገዛዙን፤
አክ!
እንትፍ!
አልፈልገውም!
ብሎ
ሕዝቡ
በግንቦት-7-1997
የሰጠበትን
ድምጽ
ሊያስቆጥሩ
መቻላቸው
አንዱ
ታሪካዊ አስተዋጽአቸው ነው።
በሰላማዊ
መንገድ
የሚታገሉ
ድርጅቶች፤
ከሕዝብ
መሃል
ሆነው
የሕዝቡን
ችግር
እየቀመሱ
መፍትሄ
የሚሉትንም
እየተማከሩ
የሚሰሩ
ድርጅቶች
ናቸው።
ከሕዝብ
ጋር
መነጋገርና
መግባባት
መቻል
ደግሞ
የስልጣን
ትልልቆቹ
አካሎች
ናቸው።
አምባገነኑ
አገዛዝ
ሕዝብ
የሚያናውጠው
ቀን
ሲቃረብም፤
እነዚሁ
ሰላማዊ
ትግል
የሚያከሄዱ
ድርጅቶች
የስልጣን
ሽግግርን
ሰላማዊ
እንደሚያደርጉት
ሳይታለም
የተፈታ
ነው።
ይኼ
ደግሞ
በጎነትም
አለው።
እንዴት ቢሉ፤ ሌላ
በባእድ
ዳፍ
ስር
ሆኖ
የማናቀው
የተራበ
ተጋዳላይ ከምንይልክ ቤተመንግስት
ገብቶ፤
ባለተረኛ
ነኝ! እንዳይልብንና
እስከ
እናካቴውም
አገራችንን
እንዳይበትንና
ስቆቃችን
እንዳይቀጥል
ዋስትና
ይሰጣልና።
የወያኔ ደጋፊዎችና አባሎቹም ቢሆኑ የቂም በቀል ሰላባ እንዳይሆኑና
ደም እንዳይፋሰስ፤ የሕዝብ አመራር ሊሰጡና ሊደመጡ የሚችሉት እነዚሁ ከሕዝቡ መካከል ተገኝተው በሰላማዊ መንገድ የሚታገሉ ድርጅቶች
ብቻ ናቸው።
ሚሊዮኖች ወደ አደባባይ!
በቅርቡ
በአዲስ
አበባ ዩኒቨርሲቲ የፍልስፍና መምህር
የሆኑትና
በዩኒቨርስቲው
ብዙ
መንገላታት
እየደረሰባቸው
ያሉት
ዶ/ር
ዳኛቸው
እንዳሉት፤
የሰላማዊ
ትግሉ
ሚሊዮኖችን
ማነሳሳት
ከቻለ፤
ወይም
በሚችልበት
ቀን
በኢትዮጵያ
ለውጥ
ሊመጣ
እንደሚችል
ራሱ
ወያኔም
ሳይቀር
በእርግጠኛነት
የሚያውቀው
ነገር
መሆኑን
ነው።
በሚሊዮን የሚቆጠር ሕዝብ ኢላማ
ላለው
ግብ
ቆርጦ
ከተነሳ
ማንም
ሊያቆመው አይችልም። ፊዴራል ይሁን አጋዚ መፍትሄ
አይደሉም።
በተለይ
ዛሬ በሰማያዊ ፓርቲ ውስጥ
ገብተው የሚታገሉ ወጣቶች ለሰላማዊ
ትግሉ
እመርታ
ስጥተውት
ስናይ፤
ያ!
የምንናፍቀው
የህዝባዊ ድል አቅጣጫውን ያገኘ ይመስለናል። የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ንቅናቄም አሁን
ከሚያደርገው
ትግል
ከፍ
ብሎ፤
በስርአት
ለውጥ
ላይ
ማተኮር
አለበት።
በአገር ቤት የኢትዮጵያ
ኦርቶዶክስ/ካቶሊክና/ትሮተስታንት
ቤተክርስቲያናት
አባቶች
አብዛኞቹ
ለስጋቸው
በማድራቸው
ስለ
ክቡር የሰው ልጅ መብትቶች ይሁን ስለ አገር ትንፍሽ
ሲሉ አይሰሙም። የመንፈስ
ጥንካሬያቸው እጅግ የደከመ ስለሆነ ከወያኔ ጫማ ስር ወድቀዋል። ቤተ-ምእምኑ የስርዓት ለውጥ እንዲመጣ
በየቤተከርስታናቱ ዘንድ ጫና በማድረግ በጉልህ
መንቃነቅ
አለበት።
እንግዲህ
ትግል
እንዲህ
እንዲህ
እያለ
ተጠራቅሞ
ነው
ሚሊዮኖችን
ማነቃነቅ
የሚቻለው።
ስለማዊ ትግሉና እንቅፋቶች
እዚህ
ላይ
ሰላማዊ
ትግሉ
ገጥሞት
የነበረውን
እንቅፍት
መለስ
ብሎ
ማየቱ፤
ዛሬ
ላለንበት
የትግል
ደረጃም
ሆነ
ለወደፊት ጥቅም አለው። ለምንድን
ነበር
የቅንጅት
የህዝብ
እንደራሴዎች
ዘብጢያ
ወርደው
ከተፈቱ
በሁዋላ
መከፋፈል
የተከሰተው?
የወያኔ እጅ አንዱናን ዋነኛው እንቅፋት ነው። ይኸ ደግሞ ስልጣኑን
በብቸነት ለመያዝ ከሚፈልግ አካል የሚጠበቅ ነው። በሌላ በኩል ደግሞ ራሱ በቅንጅት
ውስጥ ከቁዋጥኝ
የበለጠ
ክብደት ያለውን፤ የሕዝብ
አደራ
ወይም እንደራሴነት ከቁም
ነገር
ባለመቁጠር የተነሳ የስልጣን ጉጉት ችግር ነበር ለማለት
አያዳግትም።
የግለሰቦች
ለስልጣን
መቾኮል ምን ያህል
አሳዛኝ
እንደነበር
ከሁሉም
ወገኖች
በተደረሱት
መጻሕፍትና
የአደባባይ
ስራቸው
ተረድተናል።
መራራው
ሃቅም
ለቅንጅት
መፍረስ
ከተቃዋሚው ጎራ አይነተኛ
ሚና
የተጫወቱት
ቅንጅትን
በሰተመጨረሻው
የተቀላቀሉት
ነበሩ። ዲያስፖራውም አፍራሽ ተልእኮአቸውን ሃግ ከማድረግ ይልቅ፤ አብሮ
የእነርሱን ጩኸት እንደገደል ማሚቱ አስተጋብቶታል። ይሁን እንጂ ዛሬ ምንም ለውጥ ያላስገኘ አካሄድ እንደነበር ዞር ብሎ ሊያየው
የሚገባው ሰዓት የደረሰ ይመስለኛል።
እነዚህ
የስልጣን ጉጉዎች የሕዝብን አደራ ከማክበር ይልቅ፤
በቅንጅት
መንፈስ
ተደራጅቶ
ሊቀጥል
ይችል
የነበረውን
የአንድነት መንፈስ ፤ ዛሬም ባልደከመ የሰላ ምላስና ሸራቸው እንዲፈርስ
ከአደረጉ በሁዋላ፤ ግንቦት-7ን መስርተው ተቃራኒ የትግል
አቅጣጫ
በመቀየስ
ከሻእቢያ ጉያ ስር ተወተፉ። በዚህም ምክንያት
በተለይ ከዲያስጾራው ለሰላማዊ
ትግሉ
ሊውል
ይችል
የነበረውን
ጊዜ፣
የሰው
ኃይልና
ገንዘቡን
አባከኑት።
ዛሬም ከኢህአፓ ወደ ወያኔ፤ ከወያኔ ወደ
ቅንጅት፤
ከቅንጅት
ወደ
ግንቦት
-7 አሁን
ደግሞ
ታፍነው
ወደ
ወያኔ
መንጋጋ
የገቡት የእሳት ራቱ
የአቶ
አንዳርጋቸው
እጣ
ፈንታም
ዋናው
ምክንያት፤
በማንኛውም
መንገድ
ስልጣን
መያዝ
በሚል
ግንቦት-7
የሚከተለው
አደገኛና የከሰረ የፖለቲካ መርህ ለመሆኑ
ውጤቱን
አይቶ
መካድ
አይቻልም።
ለሕብረት የአላማ ጥራት
በኢትዮጵያ
ውስጥ
በሰላም
የሚታገሉ
ድርጅቶች
ስልጣን በጠመንጃ መያዝ የለበትም ብለው ስለሚያምኑ፤ ለዲያስፖራው ድጋፍ የተመቹ
ናቸው። አብዛኛው ዲያስጶራም፤ በምንም መንገድ ቢሆን ከአስመራ
ተነስቶ
አዲስ
አበባን
የሚቆጣጠር
ታጣቂ
የኢትዮጵያ
ሕዝብ
የሚመኘውን
ሰላምና ብልጽግና ሊያመጣ ከቶም
እንደማይችል
መስማማት አለበት። የዚህን አስፈላጊነት በተመለከተ ትድሄት
የሚባለው
የትግሬ/ሻእቢያ
ጦር፤
የአቶ
አንዳርጋቸውን
መታፈን
አስመልክቶ
ያወጣው
መግለጫ
ማጤኑ ብቻ በቂ ነው። የትድሄት
መግለጫ በኢትዮጵያ የሚደረገውን የሰላማዊ ትግል በጣም
የሚያንጉዋጥጥውና
የሚኮንነው ለምንድን ነው? መልሱ ቀላል ነው። መልሱ፤ ነቀርሳዋ ኤርትራ የኢትዮጵያ
ሕዝብ
ተረጋግቶ
ለእድገትና
ለብልጽግና
እንዳይሰራ
የምትሸርበው
የፖሊሲዋ
ነጸብራቅ
ነው።
የግንቦት-7ም የመርህ ፍርሽነት ይኽንኑ አለመገንዘቡ ነው።
ግንቦት ሰባት፤ በኢትዮጵያ ውስጥ ስር የሰደደ ትግል ለማካሄድ ከመጣር ይልቅ ሻእቢያን በቆረጣ ሸውዶ ስልጣን ለመያዝ የሚባዝን ስብስብ
ነው።
ጦርነት
ለጦርነት
በር
ከፋቹ በስልጣን ላይ ያለው
አገዛዝ
ነው።
ወያኔ
ሕዝብ
እንደሚጠላው
ያውቃል።
በሰላም
የፖለቲካ
ትግል
የሚያካሄዱ
ድርጅቶችም
እውነተኛ
ምርጫ
ቢካሄድ
እንደሚያሸንፉት
አያጣውም። የሆኖ
ሆኖ
በአሁኑ
ይዞታው
ለስልጣኑ
አስጊ
ታጣቂ
የለም
ብሎ
ስለሚያምን፤
ስልጣን
መልቀቅ
ወይም
ማካፈል
አይፈልግም።
ማንኛውም
ጭቆና
ደግሞ
የሚያስከትለው
አመጽን
ስለሆነ፤
በኢትዮጵያ
የሚደረገውን
የሰለማዊም
ሆነ
የጦር
ትግል
እየጠነከረ
መሄዱ
አይቀሬ
ነው።
የኢትዮጵያ
ሕዝባዊ አብዮታዊ ሠራዊት፣ ከፋኝና የቀድሞው አርበኞች
ግንባር
ጦርነት
አካሄደው
መራራ
መስዋእትነት
ከፍለዋል።
ይሁን
እንጂ ኤርትራን
መንደርደሪያ
ያደረጉት
ጦረኞች የጎላ እንቅስቃሴ አድርገው
አናይም።
አንዱ
ዋናው
ምክንያት
ከአጋም
የተጠጋ
ቁልቁዋል
ሲያለቅስ
ይኖራል
አይነት ሆኖ ነው።
ለኢትዮጵያ
አንድነትና
ዴሞክራሲያዊ ስርዓት መረጋገጥ
እንታገላለን
እያሉ ከአጋሙ እሾህ ሻእቢያ
ጋር
በመታከክ
ይደማሉ።
ኢትዮጵያን
እንበትናለን
የሚሉትም፤የሻእቢያ
አሽከርነታቸው
ስልታዊ
እንጂ፤
ሻእቢያ
ከወያኔ
የበለጠ
አሽከር
እደማይሆኑት
ሰለሚያውቀው፤
ኩሊነት
እያሰራቸው
የቁም
እሰረኛ
አድርጎአቸዋል። ሻእቢያ ራሱ ትእዴን የሚለውን የትግሬ
ጦር
መስርቶ
እየቀለበ፤
አያዋጋውም።
ወያኔን
ለማስፍራራት
ይሁን
ለመከላከል
አይታወቅም።
የክት
አድርጎታል።
እንግዲህ
ግፈኛውን
አገዛዝ
በጠመንጃ
ለውጠን
በኢትዮጵያ
ሕዝባዊ
አስተዳደር
እንዲመሰረት
እናደርጋለን
የሚሉ
ታጣቂዎች
እንዳሉና
እንደነበሩ
ሁሉ፤
ወያኔን
አስወግደን
ኢትዮጵያንም
ገነጣጥለን
እናጠፍለን
የሚሉ
እንደ ኦነግ ያሉ የእንግዴ ልጆችም አሉ። እነዚህ የእንግዴ ልጆች ከአንዳርጋቸው
በፊት አስመራ ቢከትሙም፤ አንድም ቀበሌ ከወያኔ ነጻ አላወጡም። አመራሮቹ የመታፈን
አደጋ
እሳኩሁን ባይገጥማቸውም
የሻእቢያ የቁም እስረኛ መሆናቸው ይታወቃል።
የጦርነቱ
ትግል
አደገኛ
ነው።
እንደ
ሰላማዊ
ትግሉ
ውጤቱ እርግጠኛ አይደለም።
እርግጥ ነው፤ በሰላማዊ ትግሉ ውስጥም
ግንጠላን
የሚያቀነቅኑ
እንደ
ነጋሶና
ቡልቻ
ያሉ
ሽማግሌዎች
አሉ።
ይሁን
እንጂ
የሰላማዊ
ትግል
ዋና ባህሪው የሰከነ
ውይይት
ማካሄድ
ስለሆነ
የእንደኒዚህ ያሉ
ከዳርቻ
የመጡ
አዋኪዎች
ውሸት በውይይት ስለሚጋለጥ የውሃ
ላይ
ኩበት
ሆነው
እንደሚቀሩ
ምንም
ጥርጥር
የለም።
በኢትዮጵያ
የሰሜን
ክልል
ከሻእቢያ
ቁጥጥር
ውጭ
የሚንቀሳቀሱ
ታጣቂዎች አሉ ሲባል ይሰማል። እነዚህ
ሕዝቡ
የሚደግፋቸው
ከሆነ
ወያኔን
በእርግጠኝነት
ሊያስወግዱ
የሚችሉ
ናቸው።
እንደውም ተጠናክረው ወያኔ ወሎን ማስተዳደር እንዳይችል አድርገው
ካወኩት ትልቅ ፈተና ውስጥ ይከቱታል። እንዲደራደር ያስገዱታል። አሊያም
በአፊንጫው ሊደፉት ይችላሉ። ይሁን እንጂ እነርሱም ስልጣን
ቢይዙ ስልጣንን
ሕዝባዊና
ሕጋዊ
ማድረጋቸው
አጠራጣሪ
ነው።
ስልጣን
እኮ
ማለት
በአፍሪካ፤
ቪላ
ቤት
ነው።
መርሴዴስ
ነው።
ከስድስት አሃዝና በላይ የበለጠ የባንክ ደብተር ባለቤት
መሆን
ነው።
ቢሆንም
ጦርነት ብንመኘውም አይቀርምና፤ ከተረዱም መረዳትና ማደግ የሚገባቸው ከሻእቢያ ቁጥጥር ውጭ የሆኑት ታጣቂዎች ብቻ ናቸው። ይኼን
በተጠናከረ መንገድ ለማቀኛጀት በተለይ፤ ከግንቦት -7ቱ የኢሳት ሬዴዮ
ሌላ አማራጭ ማጠናከር ያስፈልጋል። የግንቦት-7 ፖለቲካ ትልቅ ጋሬጣ መፍጠሩ እያደር እያታወቀ ቢሆንም ጋሬጣው ገና ሙሉ ለሙሉ
አልተገፈፈም። ግንቦት-7 አናቱ በገመድ በወያኔ ተሸብቦም ቢሆን፤ በቅርብ አንድ እንኩዋን ቀበሌ ከወያኔ ካላስለቀቀ፤ የትጥቅ ትግል
የሚለው ሹፈቱ ገሃድ እንደሚወጣና ማንም ሳይገፈትረው ከስሞ እንደሚቀር ጥርጥር የለም።
መደምደሚያ
በኢትዮጵያ
በሰላማዊ መንገድ የስልጣን ሽግግር ለማምጣት፤ ከ23 አመታት ጀምሮ የተሰሩት ስራዎችና የተገበዩት ልምዶች ጥሩ መሰረት ጥለዋል።
ድርጅቶች እስካሁን የተከተሉት የሰላማዊ የትግል እንቅስቃሴ እንዳለ
ሆኖ፤ ሚሊዮኖችን አደባባይ ላይ በማሰለፍ ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር በኢትዮጵያ እንዲመጣ መስራት አለባቸው ። ለዚህ ስራ መቀናጀት
ወይም መናበብ ይገባቸዋል። ዴያስፖራውም ለውጥ የሚመጣው ኢትዮጵያ ውስጥ ስራ ሲሰራ እንጂ ከአስመራ ከበሮ በመደለቅ ብቻ እንዳልሆነ
ተገንዝቦ፤ ሚሊዮኖችን የስልጣን ሽግግር በሰላማዊ መንገድ እንዲመጣ ለማነሳሳት፤ በትጋት እየሰሩና ወደፊትም ለመስራት ፈቃደኛ ለሚሆኑ
ድርጅቶች ያልተቆጠበ ድጋፉን ማድረግ አለበት። እስካሁን ወያኔን እናስወግዳለን ወይም እናንበረክከዋለን በሚሉ መፈክሮች ከዲያስፖራው
የታለበው ገንዘብ አንድ ቀበሌ እንኩዋን ከወያኔ ነጻ ማውጣት ካላስቻለ፤ አማራጩ፣ አጭሩና እርግጠኛው መንገድ ሚሊዮኖችን አደባባይ
አሰልፎ ስልጣን እንዲገራ ለመስራት ቆርጦ መነሳት ነው።
Comments
Post a Comment