መሪያችንን እንደ ዐይናችን ብሌን!
ጉድ ሳይሰማ፤ መስከረም አይጠባም ነው
ነገሩ።
ለአብይ አህመድ የሚደረገው ሰልፍ
በየክልሉ እየደራ ነው። ማን ከማን ክልል ያንሳል? በሁዋላ ለምን ይኼ ክልል ለእኔ ድጋፍ አለወጣም? የሚል ተጠያቂነት ስለሚያመጣ፤
ወደድክም ጠላህም፤ “መሪያችንን እንደ ዐይናችን ብሌን!” እንጠብቃለን እያልክ ግንባርህን በአደባባይ ማሳመታት አለብህ። እንደ ዐይናችን
ብሌን የሚለው የደንቆሮና የሆዳም ካድሬ ቅጥፈት ነው። ሰው እኮ ራሱም
አሻግሮ ማየት ሲችል ነው የሌላውን የዐይን ብሌን ሊጠብቅ የሚችለው።
የፕሮፌሰር መስፍን ምርር ያለች እንጉርጉሮ
ዛሬም የምንገኝበትን ስርዓት እንደ መስታወት ስለምታሳይ፤ ቀንጨብ ላርጋት፤
“ስብሃት ለጨለማ”!
“ስብሃት ለጨለማ”! ለብርሃን ዋዜማ!
ጨለማ! የስርቆሽ ውድማ ! የግብዝ
ከተማ!
ጨለማ! የክፋት፤ የተንኮል፤ የጭቃኔ
አለኝታ!
የወንጀል ነፃነት! የኃጢአት ደስታ!
ይጠየቅ ሰው ሁሉ፤ እውነቱን ይናገር፤
የሚናገር ቢኖር፤
ብርሃን ነው ጨለማ ሰውን የሚያሳፍር?
ጨለማን ይጠላል ሰው ጨዋ ለመባል፤
ብርሃን ሲያሸማቅቅ አያውቀው ይመስል!
ጨልም ! ጨልም ! ድፍን ብለህ ጨልም!
ዓይኖቻችን ይጥፉ አያዩም አይጠቅሙም!”
* መቼ እንደጻፈው አልተገለጠም።
እንጉርጉሮ የሚለው ስራው የታተመው እ.ኢ.አ በ1967 ዓ.ም ነው።
ስርቆት፣ግብዝነት፣ክፍት፣ተንኮል፣ጭቃኔና
የወንጀል ነጻነት የአብይ አህመድ አገዛዝ መገለጫዎች ለመሆናቸው ህልቆ መሳፍርት መረጃዎች አሉ።
ግብዝነት
አብይ አህመድ በወታደራዊ ወኔው፤
ኢትዮጵያ ከሰላሳ አመታት በሁዋላ ከሁለቱ አንድዋ የአለም ኃይላን አገር ትሆናለች ያለ ግብዝ ነው። እንደዚህ አይነት ድፍረት የሚመጣው
የአለምን የኢኮኖሚና የፖለቲካ አደረጃጀት በትንሹ እንኩዋን ካለማወቅ ነው። ብዙ ጥናቶች ወለል አድርገው እንደሚያሳዩት ጉዳዩ ውስብስብ
ነው። እስኪ ግብዝነቱን እንፈትሽ።
ከቀዝቃዛው ጦርነት ማክተም ማግስት
ጀምሮ የአለማችን የሃብት ክፍፍል በአገሮች መካከል ይሁን ሃብታም በሚባሉ አገሮች በሚኖሩ ዜጎች መካከል እጅግ እየተዛባ መጥቱዋል።
ለምሳሌ በየአመቱ የአለምን የሃብት ክፍፍል እያጠና የሚያሳትመው የኦክስፋም ድርጅት እ.አ.አ በ2019 ባወጣው ሪፖርቱ፤ በቀደመው
አመት(2018)፤ 26ቱ(ሃያ ስድስት) የአለማችን እጅግ ሃብታሞ ግለሰቦች ያላቸው የሃብት ዋጋ፤ በአለማችን ከሚኖሩት 3.8 ቢሊዮን
ድሆች(ግማሽ የዓለም ሕዝብ ቁጥር) እኩል መሆኑን አረጋግጡዋል። በተጨማሪም ሪፓርቱ በ2018 ዓ.ም የዓለማችን 2200 ቢሊየነሮች
የሃብት ዋጋ በ12% ሲጨምር የ3.8 ቢሊዮን ድሆች ደግሞ በ12% መቀነሱን ያረጋግጣል። ሌላ አንድ የራሴን ትዝብት ልጨምር። ጄኔራል
ኤሌትሪክስ በሰራሁበት ወቅት በሃብታምነቱ እደመም ነበር። እንደ አንድ አገር ነው። የዛሬው አንጡራ ሃብቱ 88 ቢሊዮን ነው። የኢትዮጵያ
የዓመት አጠቃላይ ጅምላ ምርት 95 ቢሊዮን ነው። የውጭ እዳዋ ደግሞ በ2019 39.43 ቢሊዮን ነበር። ጀኔራል ኤሌትሪክስ በሃብት ረገድ
125ኛ ደረጃን የሚይዝ የአሜሪካ ካምፓኒ ነው። የኢትዮጵያ የምርት አቅም ያውም ጥራቱን ሳይጨምር ከጄኔራል ኤልክትሪክስ አንጡራ
ሃብት ሲመዘን ከግማሽ በታች ነው። ለተጨማሪ ግንዛቤ ያህል፤ ዛሬ የአፕል፣የማይክሮሰፍትና የአማዞን የገበያ ዋጋ የእያንዳንዳቸው
ከአንድ ቲሪሊዮን በላይ ነው።
በጎሳ ፖለቲካ ክልል ታጥራ፤ የሰውንና የካፒታልን ነጻ እንቅስቃሴ የምትገድበው የአብይ አህመድ
ዘረኛ ኢትዮጵያ እንኩዋን በ30-- በ300 አመታትም ከአለም ከሁለቱ አንድዋ ኃያል ልትሆን ይቅርና ከርሱዋንም መሙላት አትችልም።
ታዲያ እንዲህ ያለ ዐይኑ የማያይን
መሪ ትንሽ የማገናዘብ አቅም ካለህ ለምንድነው እንደ ዐይንህ ብሌን የምትጠብቀው? በጄ ደንቆሮና ወራቤሳው/ጅቡ የጎሳ ካድሬ እጁ እስኪነድ ያጨብጭብ። ዳንኪራ ይርገጥ። ሰርተህ መብላት የምታፈቅር
ከሆንክ ግን የውሸት ቀለብ የሚመግብህን እንዴት ትንከባከባለህ? በኢትዮጵያ አውርቶና ሰምቶ ማደር ከደርግ ጀምሮ እየተባባሰ የመጣ
ባህላችን ስለሆነ እንደዚህ ያለውን ውሸት የሚያቀነቅኑ ካድሬዎችንና መሪዎቻቸውን መጥየፍ እንጂ ለእነርሱ ማጨብጨብ ከድህነት ያወጣኻል?
ጭቃኔ፤ የብሄርተኞችና የፈሪዎች አይነተኛ
መገለጫ ነው።
በአርሲ ኔጌሌ ጃዋር መሐመድ በተገኘበት
የሰው ልጅ ተዝቅዝቆ ተሰቅሎ አይተናል። በሻሸመኔ፣በኮፈሌ፣በአጋርፋ፣በአዳባ፣በመተከል፣በወለጋ፣በወልቃይት ወዘተረፈ የተደረጉትን እልቂቶች አይተናል። እነዚህ በግብታዊነት የፈነዱ ሳይሆኑ
ታስቦባቸው የተደረጉ የብሄርተኞች ወንጀሎች ናቸው።
ወልቃይት
በወልቃይት ለአራት አስርታት የተደረገው የዘር ማጥፋት ጭቃኔ የብሄርተኞችን ተንኮልም አጋላጭ ነው። ወያኔ የትግራይ ሕዝብ በአማራ ምንም በደል እንዳልደረሰበት ያውቃል። ትግራይን ሁሌም ያስተዳደሩት ትግሬዎች ናቸው። ይሁን እንጂ አረጋዊ በርሄም ሆነ ሌሎች እንደነገሩን ‘ደርግን ለመጣል’ የመረጡት ስትራቴጄ የትግራይን ሕዝብ በብሄር ጥላቻ መቀስቀስ ነው። ጠላትህ አማራ ዝቅ ሲልም የሸዋ አማራ ብለው መረዙት። ዋናው ግባቸው የአማራን ለም መሬቶች መንጠቅ ነው። እንደአሰቡትም አደረጉት።
ዛሬም የወልቃይትና የሌሎች የጎንደርና የወሎ ግዛቶች ወደ ባለቤቱ መመለስ ለብሄረተኞች የጎን ውጋት ሆኖአል። የእነ ዶ/ር ሙሉ ነጋ ውትወታ የሚጠበቅ ነው። እነዚህ ስለ ሰው ልጅ ነፃነት ህሊና የሌላቸው የጥቅም ባሮች ናቸው።
በእዚህ አጋጣሚ የዘረኛውን ጃዋር መሃመድ አቁዋም በወልቃይት ላይ ማየት ተገቢ ነው። እንደ ጃዋር ከሆነ መሬቱ ወደ አማራ ክልል ከተመለሰ..."የትግሬን ብሄረተኝነት ስለሚያባብስ ጉዳዩ ሁሉንም በማይጎዳ መልኩ መፈታት አለበት" ይላል። ጃዋር መሃመድ ልክ እንደ ትግሬዎቹ የፖለቲካ ሰዎች ለአማራም ሆነ ለሰው ልጅ ሕይወት አይጨነቅም። እርሱ እንደምንም ብሎ በአማራና በትግሬ ስንጥቅ በማስፋት ላይ ነው የተጠመደው። ዶሮ ብታልም ጥሬዋን እንዲሉ፤ የእርሱ ኦሮሞ ለዘላለም እንዲገዛ እንጂ የአማራ ነገድ ቢጠፋ እንደመለስ ዜናዊ ቁቡ አይደለም።
በዚህ የወልቃይት ጉዳይ ግን የአብይ አማካሪ የሆነውን አቶ ሌንጮ ለታን ማመስገን ግድ ነው። ሌንጮ በአንድ አሜሪካ በተደረገ ስብሰባ ላይ ከአረጋዊ በረሄና ከፕሮፌሰር መስፍን ጋር በእንግድነት ተጋብዞ ስለ ኢትዮጵያዊ ይወያይ ነበር። በወቅቱ በወልቃይት ላይ አንድ ፋሽን ተጀምሮ ነበር፤በአብርሃ ደስታ በሚባል የወያኔ ተጋዳላይ፤ የመቀሌ አሰተማሪና ዛሬ ደግሞ በትግራይ የማህበራዊ ጉዳይ ሹመኛ። አብርሃ የወልቃይት ጥያቄን፤ ሆን ብሎ በማሳነስ…"ቀሽም" ነው ብሎ ፈረጀው። አረጋዊም ሆነ ፕሮፈሰር መስፍን ጥያቄውን እንዲሁ ቀሽም ነው ባይ ነበሩ። ሌንጮስ?… " እኔ የወልቃይት ነገር በጣም ያሳስበኛል። እርግጥ ነው ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በአገሩ እየተዘዋወረ የመስራትና የመኖር መብቱ መጠበቅ አለበት። ይሁንና የአገሬውን ሰው እያጠፋህ ከሌላ ቦታ ሰው እያመጣህ ማስፈርን በጣም አድርጌ ነው የምቃወመው" ነበር ያለው። እኔ ተወልጄ ያደኩበት የኦሮሞ ስነ ልቦና ይኼው ነው። ነፃነትን አፍቃሪ ነው። ታዲያ ዛሬ ዘረኛው አብርሃ ደስታ ትናንት ቀሽም ነው ያለውን የወልቃይት ጉዳይ፤ ዛሬ እያንገበገበው የአማራ ልዩ ኃይል ከቦታው ይውጣ! መሬቱ ይመለስልኝ ባይ ወትዋች ሆኖአል።
በቅርቡ በኢትዮጵ 360 እንደተደመጠው፤ ጃዋር መሃመድ ከአብይ ጋር እፍ እፍ
በሚልበት ጊዜ የኢትዮጵያን አየር መንገድ 16 ከፍተኛ በፓይለትነትና፣በቲከንክ፣በአስተማሪነትና በአስተዳደር ልምድ ያካባቱ ኦሮሞ
ያልሆኑ(ትግሬዎችም አሉበት) እንዲባረሩ አድርጉዋል። እንደሚጠበቀው የተባረሩት ሰዎች የተሻለ ደመወዝ በማግኘት ተለምነው በአፍሪካና
በአረብ አገሮች ተቀጥረው ይሰራሉ። እነዚህ ጎሰኞች ግን በምትካቸው የቀጠሩት በዶላር እየከፈሉ ኢትዮጵያዊ ያልሆኑ ዜጎችን ነው።
ይኼን የሚያደርጉት ኢትዮጵያን የሚያስኮራትን ተቁዋም በኦሮምማ ለመተካት ነው። እጅግ የሚያዛዝነው ዛሬ አየር መንገዱ የሚመራው ምንም
ክህሎት በሌለው በአብይ ቀኝ እጂ አባ ብላ ገመዳ ነው።
ጃዋር መሃመድ ካድሬ ነው። በየትኛውም
የመንግስት ሆነ የግል ኩባንያ ተቀጥሮ ምንም ያካባተው የስራ ልምድ የለውም። እርሱና እንደርሱ ያሉ ሰዎች የኦሮሞን ወጣቶች የጥላቻ
ምርኮኛ በአደረጉበት አገር፤ የሰውና የካፒታል እንቅስቃሴ እንደሚገባው በኢትዮጵያ መንቀሳቀስ ስለማይችል ከድህነት ለመላቀቅ የማይታሰብ
ነው።
በተለይ የኢትዮጵያ ወጣት ሊገነዘብ የሚገባው፤ ከድህነት ለመወጣት በዛሬው አለም ማድረግ
ያለበት በትምህርቱ ተገቶ የፈጠራ ክህሎትን ማዳበር ነው። ወጣቱ በትምህርቱ ከጎበዘ የስራ እድሉ በአለም አቀፍ ገበያ ይሰፋል። ወደ 400 ሚሊዮን ሕንዶች ከድህነት የተላቀቁት
በትምህርታቸው ተግተው በአለም ላይ ሙያቸውን መሸጥ በመቻላቸው ነው። ስለዚህ የወጣቱ መሪዎች መሆን ያለባቸው ከጎሳ ከረጢት በላይ
የሚያስቡ ሰዎች ናቸው። አብይ አህመድ፣ጃዋር መሃመድ ሆኑ ሌሎች ጎሰኞች አይናቸውን ያልገለጡ ሁዋላ ቀር ዘመኑን ያልዋጁ፤ ሕዝበኛ
ዋልጌዎች ናቸው። እነዚህ ገና አይናቸው አልበራም። የማያይ አይን ደግሞ እንደ ብሌን አይጠበቅም።
Comments
Post a Comment