" ሃረጉ ይሙት ጋ. እም. ይወዳል"

“ሃረጉ ይሙት! ጋ. እም. ይወዳል!”
ቦጋለ ካሣዬ  ማርች 2014 አምስተርዳም
መግቢያ፤
የፌስቡኩ(Facebook) ኤትኖግራፈር፤የኤርትራው ኢሳያስ አፈወርቂ አንዳንድ አሁን በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ ካሉት ኢትዮጵያውያን የተሻላ ለኢትዮጵያ ያስባል ብሎ በመጻፉ የተነሳ፤ ለተስነዘረበት ምላሽ፤‘ተስደብኩ’ እያለ  በሞራል ጥያቄ ስርቻ ውስጥ ለመወተፍ መውተርተሩን አጤነናል። ከንቱ ልፍት። ነገሩ ጅራፍ ራሱ ገርፎ ራሱ ይጮሃል አይነት ነው።
እንደ ኢማኑኤል ዋለርስታይን ከሆነ፤ በምእራቡ ዩኒቨርስቲዎች ማሕበራዊ ሳይንስ፤  በታሪክ፣በኢኮኖሚክስ፣በሶሶሎጂንና በፖለቲካ ሳይንስ ላይ ብቻ ላይ ነበር ተከፋፍሎ የሚጠናው። ይሁን እንጂ በ19ኛው ክፍለ ዘመን ሃያል አገሮች በተቀረው ዓለም ላይ ቀንበራቸውን ሲጠምዱ፤ እነርሱ ሁዋላቀር አርገው የሚቆጥሩትን ሕዝቦች ለማጥናት ማህበራዊ ሳይንስንም ማስፋት አስፈለጋቸው። በዚህም መሰረት አንትሮፖሎጂን በዩኒቨርስቲዎች ማስተማር ተጀመረ። አንዱ የአንትሮፖሊጂስቶች ስራ በሕዝቡ መሃል እየኖሩ፤ ቁዋንቁውን በመናገርም ይሁን በቱርጁማን ፣ባሕሉንና አኑዋኑዋሩን አጥንተው ለቅኝ ግዛት አስተዳዳሪዎች ስራቸውን ማቅረብ ነበር። በሚገኘው መረጃም ቅኝ ገዚዎች ሕዝቡን እንዴት ማስተዳደር እንደሚገባቸው ይገለገሉበት ነበር። ሕዝቡን የሚያጠኑበት ዘዴ፤ በማየትና በመሳተፍ የሚደረግ ስለነበር፤ ስራቸው “ኢትኖግራፊ መጻፍ” ይባል ነበር። እንግዲህ ኢትኖግራፊ የቅኝ ግዛት ‘ቱሴ’ ወይም መረጃ አቀባይ ነበርም ማለት ነው። ወደ ቡዳ ኢትኖግራፈሮች እንሂድ።
1ኛ/፤ አንደኛው ቡዳ  ለሻእቢያ ያረገደው  አስመሮም  ነው። እርሱ በጻፈው የኦሮሞ የገዳ ስርዓት ስራ ላይ ተመርክዞ ነው፤ የሻእቢያው ስላይ ተስፋዬ ገብረአብ ፤ የስደተኛውን ማስታወሻ የጻፈው። ተስፋዬ ስለ ቡርቃ ትዝታ የተነሳበትን ተቃውሞ ለማብረድ ሲባዝን፤ በጋዜጠኛው ማስታወሻ ስራው ላይ፤ የቡርቃን ትዝታ ከመጻፉ በፊት፤ «የአስመሮም ለገስን ስራ አንብቤ ቢሆን ኖሮ፤ በዚያ መልክ አልጸፈውም” ብሎ ነበር። በሌላ አነጋገር ቡርቃን ከእውቀት ማንስ የተነሳ ነው የጻፍኩት ብሎ  እኛን ለማሞኘትና ተቃውሞአችንን ለማብረድ መሞከሩ ነው። ይሁን እንጂ ውሎም ሳያደር የኢትዮጵያ ደመኛ ጠላትና የሻእቢያ ሰላይ ስለመሆኑ በሰደተኛው ጋዜጠኛ ስራውና፤ በአገር ወዳድ ኢትዮጵያዊው ክትትል ገሀድ ሆነ። ታዲያ ይኼው የእኛ ነጉላ የፊስቡኩ ኢትኖግራፈር በተስፋዬ መተቸትና መጋለጥ ደብኖና ተንገብግቦ ፤«ተስፋዬ ገ/አብን በትክክል አልተረዳችሁትም! አማርኛ ስነጽሁፍ እየደከመ ስለሆነ ተስፋዬን ጠላት ማድረግ አይጠቅምም” የሚሉ አስገራሚ ማደናገሪያና ቅብጥርጥሮችን ሲደረድር ነበር። በአፍቅሮተ ሻእቢያና በአፍቅሮተ ኦነግ ካልተለከፈ በስተቀር፤ለምን የሻእቢያ ሰላይና ኢትዮጵያ እንደ አገር እንዳትቀጥል ቮድካ እየተጋተ የሻእቢያን ፕሮፓጋንዳ የሚያሰራጨውን ደመኛ ጠላታችንን ይከላከላል?
2ኛ/ደሞ ባክሰተር የሚባል ዘረኛ ኢትኖግራፈር አለ። ከኦነግ በላይ ኦሮሚያን የሚናፍቅ። የአማሮች ቀንደኛ ጠላት። ባክስተር እንደሚለው በኦሮሞች ጋብቻ በፍቅርና በመተሳሰብ ላይ የተመረኮዘ ሲሆን፤ በአማሮች ግን በጥቅምና በእግረ ቀጭንነት የተሳሰረ ነው። እኛ አማሮች ለእርሱ የሴተኛ አዳሪ ልጆች ነን ማለት ነው።
3ኛ/ቴሩሊዝ የሚባል ኢታሊያዊ ሌላው ስነፍና ቡዳ ነው። ስንፍናው ብዙ አመት ኢትዮጵያ ኖሮ አንድ የኢትዮጵያ ቁዋንቁዋ እንኩዋን መማር ባለመቻሉ ነው።  ቡዳም ደግን ለመጉዳት አይሰንፍም። እንደ መለስ ዜናዊ ሁሉ እርሱም የኢትዮጵያ ገበሬ በዜግነቱ የመሬት ባለቤት እንዲሆን አይፈልግም።
ለምን? በእርሱ ቤት መሬት የግል ከሆነ በትውልድና በዜግነት የሚነሱ ግጭቶች ኢትዮጵያን የሚያህል አገር አንድ አድርጎ ለማስተዳደር አዳጋች ይሆናላ! በእርግጠኝት ለመናገር ግን ነገሩ  “የኢትኖግራፊሩ ሽፍጥ” ነው።
እነሆ ዛሬ የኢትዮጵያ ሆነ የአፍሪካ መሬት ከአፊንጫቸው አርቀው በማያስቡ የአፍሪካ ገዢዎች እየተቀራመተና በመርዝ እየተቃጠለ ነው። መሬት በግል ይዞታ ቢያዝ ኖሮ ግን፤ ገበሬው ይረጋጋል፣ በመሬቱ ላይ ላቡን ያፈሳል፣ መሬቱን ይንከባከባል። ምርት ያድጋል። ድህነት ይጠፋል። እንዱስትሪ ያብባል። ሰላምም ይሰፈን ነበር።
4ኛ/ ወደ ራሳችን የፌስቡኩ ኢቶኖግራፈር ቅብጥርጥሮች፤ ከመሄዳችን በፌት፤አንዳንድ ነገሮች እንበል። ከማንኛውም የጥናት ዘርፍ እውቀት ይገኛል። አሁን የአባቱዋን ስም የዘነጋሁት  አስቴር የምትባል ኢትዮጵያዊት ስለ ኑዌር ጎሳ ያጠናቺው ስራ በጣም የሚወደድ ነው። የአባ ባህርይም ድንቅ ድርሰቶችም ከዚሁ ግሩም አንትሮፖሎጂ ስራዎች የሚቆጠሩ ናቸው።
5ኛ/ የትም ያልተጻፈ አንድ ‘የኢትኖግራፈር’ ስራ ደግሞ አውቃለሁ። እንዲህ ነው። ደርግና መኢሶን አብረው እፍ! እፍ! በሚሉበት ጊዜ፤ አዳሃሪና ነፍጠኛ እያሉ በደቡብ በተለይ አማራውንና ስላሌውን (ጎበዝ አራሾችና ኦርቶዶክስ በመሆናቸው ተመቅኝተው ነው) ይተናኮሉአቸው ነበር። ብዙ ለፍቶ አዳሪና ጀግኖች፤ እንደነ ጋሼ ከበደ ቱሉ፣ ሽፈራው ዳኜና ጣሰው አበጋዝ በእነ አሊ ሙሳ ተግደልዋል። ስላሌን ከባሌ የነቀሉት፤በሽታ ይንቀላቸውና  የመኢሶን ጠባቦች ናቸው። ታዲያ አባቴም፤ ካሣዬ  አንዱ ሊታረድ የተዘጋጀ ነበር። እርሱ ግን “የማን’ም ሰው ገንዘብ አልነካሁም። ማንም አይነካኝም” ይል ነበር። ሆኖም ይኽ እምነቱ  መትነኑን የተገነዘበው፤ ከደሎ መና ቤቱ ፓሊስ በቁጥጥር ስር ሊያደርገው መጥቶ አጥቶት መመለሱን መረጃ የደረሰው እለት ነው። አባቴ በፈቃዴስ እጄን አልሰጥም! ብሎ ሐረና ደን ውስጥ ከእነ ሐሰን ቱሬ፣ሁሴን ዳዲና በክር ጂሎ ጋር በደርግ ላይ ሸፈተ። ዝርዝሩን ለሌላ ጊዜ እናቆየውና፤ ወደ ተነሳንበት እንመለስ። ቀጥሎ አባቴ በሰላም እጁን እንዲሰጥ የፋሲል አውራጃው አስተዳደር ጥረት ማድረግ ጀመረ። መልእክተኞች ተመረጡ። ከእነርሱም መካከል ጋሼ ላቅዬ ሃርጉ አንዱ ነበር። እኔም የ15 አመት ጎረምሳ ብሆንም፤ አባት መቼም የሚወደውን ልጁን ሲያይ ሆዱ ይራራል በሚል እሳቤ መሰለኝ ከሽማግሎቹ ጋር ተቀላቀል ተባልኩኝ። እናቴ ግን የአባቴ እህት አክስቴ እንድትሄድ ነበር የፈለገቺው። የእኔ ታናሽ በወባ ተነድፋ ስለሞተች እኔም እዚያ ጫካ ውስጥ ወባም ሆነ ሌላ ክፉ ነገር ሊገጥመኝ ይችላል ብላ በጣም ተጨነቀች። እምቢ ብያት ሄድኩኝ። ብስል ቀይ ናት። እስካሁን ከፊቴ አይጠፋም፤ በአባቴ መሽፈትም ሆነ በእኔ ሐረና ለመሄድ መነሳት ምክንያቶች ሳምባ የመስለው ፈትዋ። የአራት ቀን መንገድ በበቅሎ ተጉዘን ጥቅጥቅ ያለው ሐረና ደን ውስጥ ገባን። ሽፍታ አባቴን ሳገኝ  አንገቱ ላይ ተጠመጠምኩ። ጋሽ ላቅዬ ማየትና መጠየቅ ይወዳል። ና! ይለኝና መንደር ለመንደር እንዞራለን። የሚያገኘውንም ሁሉ ሰው ያናግራል። እዚያው ደን ውስጥ ሆነን እሳት አንድደን የድኩላ ስጋ እየጠሰብንና እየበላን ሲወራ፤ ለካስ አጅሬ ስለ አባ አልዩ የከብትና የሚስት ብዛት ታዝቦ ኖሮአል። አባ አልዩ ስምንት ሚስቶች አሉአቸው። በጋሽ ላቅዬ አንገጋገር…እየሳቀ… ኸረ ተወኝ « ካስዬ ስምንት ናቸው እኮ! ሃረጉ ይሙት! ይገርማል! ጋላ እም. ይወዳል”! ጋሽ ላቅዬ ቢማር ኖሮ ጥሩ ኢትኖራፈር አይወጣውም ነበር ትላላችሁ?
6ኛ/ የእኛው የፌስ ቡኩ ኢትኖግራፈር በወርቅ ብእሩ ብዙ ነገር አካፍሎናል። ጠቤ ከእውቀት ጋር አይደለም። ጠቤ የኢትኖግራፈርስ ስራዎች በልዩነት ላይ ስለሚያተኩሩ፤ እነዚህ ልዩነቶች የመጥፎ ፖለቲካ መርፊ ሲወጉ በሚያስከትሉት እብደት ላይ ነው። ልክ ኢስያስ ለኢትዮጵያ ያስባል ማለት፤ የእብደት እንጂ የጤንነት እንዳልሆነ ሁሉ።
7ኛ/ አንዴ ከመሬት ተንስቶ ይኸው ኢቶኖግራፈር፤ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ ፊውዳል ስለሆኑ፤ በቅንጅት ጊዜ ተቃዋሚውን ይሳደቡ  ነበር ሲል ጽፎአል። ለነገሩ በቅርቡም ፕሮፌሰር ብርሃኑ አበጋዝ እንደተናገረው፤ በኢትዮጵያ ፊውዳሊዝም ስለመኖሩ ጠበብቶች አይስማሙም። ለምሳሌ በኢትዮጵያ ፌውዳሊዝም ኖሮ ቢሆን ኖሮ ገና ድሮ ወደ ካፒታሊዝም ተሽጋግረን ነበር። ዘው! እንል ነበር፤ በኮምጪ አምባው አነጋገር። ፍየል ከመድረስዋ ቅጠል መበጠስዋ እንዲሉ፤ ውይ ጉድ ተብሎ፤ ዝም ተባለ እንደዛ ሲዘረጥጥ።
8ኛ/ የዶ/ር መራራ ጉዲናን መጽሃፍ ካነበበ በሁዋላ ደግሞ፤ መራራ በጦቢያ መጽሄት ላይ ኦነግን አስመልክቶ የወለጋ ፕሮቴስታንት ስብስብ እንደነበር በጻፈው ላይ ቅሬታውን ያሰማል። እንደርሱ አባባል መራራ ይኽን በመናገሩ የኦሮሞን ሕዝብ ከፋፍሎአል። የኦሮሞ ሕዝብ ጥያቄም ወይ በኢትዮጵያ መብቱ ተከብሮለት መኖር፤ አለበለዚያም የራሱን መንግስት አቁቁሞ መኖር እንደሆነና እርሱም ይኸንኑ እንደሚደግፍ ጽፎአል። አሁን ደግሞ ቆንጠጥ ሲደረግ፤ ከኦነግ ጋር አለኝ የሚለው ልዩነት ከኢትዮጵያ እገነጠላለሁ በሚለው አቁዋሙ ላይ ነው ይለናል። እንደገና መለሰ ብሎ ደግሞ የመገንጠል አላማ የሚያራምደው የኦነጉ ዳውድ ኢብሳ ቢሞት ቀብር ጥሩኝ ይላል በክብር ሊቀብረው። በሙዋቹ የኦፒዲኦ አለማየሁ አቶምሳ ቀብር ግን እንደማይገኝ ነግሮናል። ከንቱነት ነው። ሞት ለማንም አይቀር። ምንም የፖለቲካ ፍይዳም የለው። አንተ ቀብረቅ አልቀበርክ ደግሞ። ቁቅም ከፈስ ተቆጠረች ይሉ የለ?
9ኛ/ እኔ ስለ ኦነግ ጉዳይ የምስማማው በከፊል ከመራራ ጋር ግን ሙሉ በሙሉ ከፕሮፌሰር ፍቃዱ ደገፌ ጋር ነው። መራራ አሁን ኢትዮጵያ አንድ ሰው አንድ ድምጽ በሚል ሂሳብ ዲሞክራሲ እንዲመጣ መመኘቱን በመጽሃፉ አንጸባርቁዋል። የመራራ ችግር፤ ብሄረተኝነት ሃሳቡና ግቡ የብሄርና የባሕሉ አንድነት በፖለቲካ የሚቁዋጭበት መሆኑን እያወቀ፤ የኦሮሞ ብሄረተኝነት ከኢትዮጵያው ጋር ተፎካካሪ እንዲሆን መፈለጉ ነው። የትግሬው እንዲህ ናጦና ቅጡንአቶ ከኢትዮጵያ በመብለጡ ያስከተለውን ምስቅልቅል እያየ፤ የኦሮሞ ብሄረተኝነት ላይ ሙጭጭ ያለው ምናልባት ኢትዮጵያ ብትንትኑዋ ከወጣ ኦሮሞም ቢያንስ አሁን የተከለለትን አገር ይገዛል በሚል የፖለቲካ ስሌት ነው። መራራ በሕይወቱ የደረሰበት ውጣ ውረድ ቀላል አይደለም። እንደዛም ሆኖ ክፉ የሚላቸውን ሰዎች ከሁሉም የቈዋንቁዋ ተናጋሪዎች  ጠቅሶአል። መራራ የሕዝብ ጥላቻ የለውም። በዚያ ቀውጢ ወቅት ነፍሱ መትርፉም በጣም እድለኛ ነው። መራራ ሊታዘንለትም የሚገባ ሰው ነው። አሁን እንኩዋን በግል ሕይወቱ ደህንነት ስለማይሰማው ከታሰርኩ እንዲጠይቁኝ በሚል ቤቱን ሸጦ፤ ቤተሰቦቹን ትንሽ በኢኮኖሚ ማጠናከሩን ነግሮናል። እንዴት ያለ አገር ውስጥ ነው የሚኖረው? ፕሮፈሰር በፈቃዱ፤ እቅጩን ተናግረዋል። አንዱ በኢትዮጵያ ዴሞክራሲ እንዳይመጣ ትልቅ ችግር የፈጠረው በጥላቻ የታወረውና የመገንጠል አባዜ ያሳበደው የሻእቢያ አሽከር ኦነግ ነው። ይኽ ሁኔታ ግን በአዲሱ ትውልድ እየተቀየረ ነው። ይኼው መከረኛ የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄ የሚባለው ሲነሳ፤ጄኔራል ታደሰ ብሩ ይነሱ የለ? የርሳቸው ልጆች ለመሆኑ ኦነግ ውስጥ ገብተው ይሆን ብላችሁ ጠይቃችሁስ አታውቁም? እኔ ሳላስበው አሜሪካ የሚኖሩትን እህትና ወንድም ተዋውቂያለሁ። ሁለቱም እግዚአብሄርን የሚፈሩ፤ ድንቅ ኢትዮጵያውያን ናቸው።
10ኛ/ ሀረር ጌዬ የሚለውን መጽሃፍ እስካሁን አላገኘሁትም። ይሁንና በዚህ መጻሕፍ ይዘት ይሁን፤ መታተም ላይ ተመስገን ደሳለኝ ጥያቄ ማንሳቱን ከዚሁ ኢትኖግራፈር ስምተናል። እኔ በነገሩ ላይ የተመስገንን አስተያየት አላነበብኩም። ኢትኖግራፈሩ የፈለገውን ማሳተም መብቱ ቢሆንም፤በወያኔ የሚጉላላው ተመስገን አንድ ከንካኝ ነገር ሳይዝ ብእሩን እንደማያነሳ አልጠራጠርም። ተመስገን ደሳለኝ የኢትዮጵያ እንቁ ልጅ ነው። አይልከሰከስም። አስመራ በአሉላ በመሰየምዋ ይወዳት እንደሆነ ነው እንጂ፤ የተዋረደ የፍሽት ብሄርተኝነት ቤት የሚልከሰከስ አሞት ያለው አይመስለኝም።
ለነገሩ አስመራ የመሸጉት የእኛ አገር ሰዎችም፤ ወያኔን በማጥቃቱ ላይ ብቻ አልተወሰኑም ይባላል። የሽሩቤዎች ስበት ድሮም የዋዛ አይደለምና፤ እነ ሰናይት መወለዳቸውን የምስራች እየሰማን ነው። እኔ እንደሚመስለኝ እነስናይት ከግንቦት-7ና ኦነግ በፊት አዲስ አበባንና አስመራን አንድ ሳያደርጉ አይቀርም።
 እናንተም ከልብ፤ ሰሜን አሜሪካና አውሮፓ ሚስት ፍለጋ ወደ ኢትዮጵያ የምትሄዱ ኢትዮጵያውያን፤ ኦነግ ነኝ፤ግንቦት-7 ነኝ እያላችሁ ወደ አሰመራም ሆነ ወደተቀረው ባሕረ- ነጋሽ ጎራ በሉ። ልባችሁ ደንገጥ የሚያደርጉ ሽሩቤዎች ከአገኛችሁ አግቡዋቸው። ጥቃታችንን ለመከላከል ሰፋ ያለ ስልት መንደፍ አለብን። የምሬን ነው!
11ኛ/ እውቀትን ለስው ልጅ ልማት እንጂ ጥፍት ማዋል ወንጀል ነው።  የእኛ ኢትኖግራፈር፤ አንድ ብጣሽ ስለ ምንይልክ ይሁን ስለ አድዋ የጻፈውን ያነበበ አለ? የለም። ለምን? አድዋ የአንድነት ውጤት ነዋ! እርሱማ ያፋቅረናል! ደግሞም የማይገባበትና የማይነካከው ነገር የለም። ሃይማኖትም ውስጥ አለበት። እንዴት ነው ነገሩ? ምርምር ነው ወይስ ሽቀላ ነው?
የሆኖ ሆኖ ቡዳ ኢትኖግራፈር ፖለቲከኛ ኢላማው መገንጠልን፣ብጥብጥንና ሁከትን ማየት ነው። እኛ ይሄን አንፈልግም። እምቢ! የምንሻው ሰላምንና ፍቅርን ነው።








Comments

Popular posts from this blog

የፋኖ አንድነት እንዴት?

እስከ ስባት ትውልድ!

አሞላቃቂ ጥቅመኛ!