Posts

Showing posts from November, 2013

6 አስተያየቶች፤ በዴሞክራሲና ሁለንተናዊ ልማት በኢትዮጵያ...

መጽሐፍ፤ ዴሞክራሲና ሁለንተናዊ ልማት በኢትዮጵያ፤ በብርሃኑ ነጋ 6 አስተያየቶች፤   ከቦጋለ ካሣዬ አምስተርዳም ስለ መጽሐፉ፤ በምረቃው እለትም ሆነ ከዚያም በሁዋላ የተሰነዘሩትን አስተያየቶች አዳመጥኩ። አነበብኩ። አንብቤው ከጨረስኩ በሁዋላ ግን አብዛኞቹ አስተያየቶች ሙገሳ ብቻ ሆነው ነው የታዩኝ። የግል ( ተዛማች ) ትችቴንና አስተያየቴን በስድስት ነጥቦች ላይ አቀርባለሁ። 1. መፈናቀል ደራሲው በመግቢያው ላይ ከልጁ ኖህ ጋር ስለ አደረገው የስራ ‘ ውልና ’ በገዛ ልጁ ችሎታ መኩራቱን በመጻፉ የብዙዎቻችንን ስሜት ነክቶታል። ኖህ እጅግ ደስ የሚል ፍሬ ነው። ቅር የሚለው ነገር ግን የአሜሪካ ሲሳይ መሆኑ ነው። ሌላም የሚስያተክዝ ነገር በአእምሮ ይመጣል። አባባ ነጋ በአገራቸው ውጣ ውረዱን ተቁዋቁመው የተዋጣላቸው ከበርቴ ሆኑ። ራሳቸውንም ሆነ አገራቸውን ጠቀሙ። ልጃቸው ብርሃኑ ግን ገና በ 17 አመቱ የፖለቲካ ጉጉት አደረበት። ከዚያም ‘ በአህያ አስተሳሰብ ’ የሚል ስድብ መዘዝ ከተቃጣ ዱላ ’ ነፍስ አውጭኝ ተርፎ፤ አሲንባ ሸፈተና በሱዳን በኩል አሜሪካ ተሰዶ እዚያው ተማረ። በፖለቲካ ጉጉት ምክንያት ወደ አገሩ ተመለሰ። ከዚያስ ? ከንቲባ፣ ቀጥሎም ጠቅላይ ሚንስትር ሊሆን ይችል ነበር። ወይኔ ! ወንድሜን ! ስልጣን ለትንሽ አመለጠቺውና እንደገና አገሩ መኖር አልተመቸውም። አሁን ወደ አሜሪካ ተመልሶ አሜሪካኖችን ያስተምራል። ዛሬም ለአርባ አመታት የቀጠለው የፖለቲካ ጉጉቱ አለመርካቱ ብቻ ሳይሆን፤ አቅጣጫውም አነጋጋ...