ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ታላቅ መሪ ነበሩ!

የቀ.ኃ.ሥ አስተዳደር እንዲህ በቀላሉ፤ በአንድ መጣጣፍ ውስጥ ሊጠቃለል የሚችል ጉዳይ አይደለም። ክቡር አቶ ዘውዴ ረታ እንኩዋን በአንድ መጽሐፍ ማቅረብ ስላልቻሉ፤ ከ1923-1948 ያለውን አስተዳደራቸውን ብቻ በ809 ገጾች አቅርበውልናል። እርገጠኛ ነኝ ቀሪውንም ክፍል እንደሚያቀርቡልን። ስለ ቀ.ኃ.ሥ ለማወቅ የፈለገ፤ ይህን መጽሃፍም ማንበብ አለበት።
ቀ.ኃ.ሥ የኢትዮጵያን ነጻነት ለማስመለስ እልህ አስጨራሽ ትግል አካሄደዋል። በተለይ ከእንጊሊዞች የሞጊዚት አስተዳደር ለመላቀቅ የተጫወቱት ሚና ቀላል አልነበረም። ለኢትዮጵያ በተቁዋማት ግንባታና በትምህርት ወደረ የለሽ ከፍተኛ ስራ የሰሩ ሰው ነበሩ። የመሬት ስሪት ጉዳይም በቀላሉ ሊስተካከል ይችል ነበር። በተለይ መሬት ኖራቸው የማያርሱ ባለቤትች ላይ ከፍተኛ ግብር ቢጨምሩ ኖሮ ባላቤቶቹ መሬቱን ለመሽጥ ወይም ለማልማት ስለሚገደዱ ብዙ ሰው የመሬት ባለቤት ይሆን ነበር፤ በመሬት ምርትም ይጠቀም ነበር። የሆኖ ሆኖ ችግሩን ስላልፈቱት አንዱ ስህተታቸው የመሬት ይዞታን አለማስተካከል እንደነበር የማይካድ ነው። ያም ሆኖ በቀኃሥ ጊዜ በኢትዮጵያ የነበረው ምርት እጅግ ከፍተኛ ነበር። በወሎ ለነበረው ረሃብም መድረሻም በቂ ምርት ነበር በአገሪቱ። ትልቁ ችግር የትራንስፖርትና ሲሆን የአስተዳደር መባለግም ነበር። ከደርግ 10 አመታት አገዛዝ በሁዋላ ፤ የተራበው ሰው ሕዝብ ቁጥር ወደ ስምንት ሚሊዮን ነበር። በቀኃሥ ጊዜ መለመን ነውር ነበር። ለዚህም ነው አንዱ የወሎ ርሃብ ወደ ውጭ እንዳይወጣ የታፈነው። ደርግ ግን ረሃብን ማጥፋት ሳይሆን፤ መለመንን እንደ ቁምነገር ቆጥሮ፤ እነሆ ሰው በረሃብ እያለቀ ነው! እኔ እንደ ንጉሱ አልደብቅም! እርዱ ብሎ እሪ አለ! ዛሬም ቢያንስ ከ 10 ሚሊዮን በላይ የሚሆን ጦም አዳሪ አለ በኢትዮጵያ። የብሄረሰብ ጥያቄ የሚባለው፤ችግሩን ከጥዋቱ በኦጋዴን የታዘቡት እንደ ፕሮፌሰር መስፍን ያሉ ሰዎች ለንጉሰ ነገስቱ አቅርበዋል። በተቀረ ግን በዚያን ጊዜ የኢትዮጵያን ብሄረተኝነት ለማጠናከር ደፋ ቀና ከማለት ሌላ ጥያቄውም በግራው መነሳትና መራገብ የጀመረው የርሳቸው አገዛዝ ሊወድቅ አካባቢ ስለነበር ለዚህ ጥያቄ የነበረው ግንዛቤም ሆነ ችግሩን እንደ አንገብጋቢ የተማረውም የሚያየው አልነበረም። የቀ.ኃ.ሥ ባለስልጣን የነበሩት አቶ አማኑኤል አብርሃም፤ በየሕይወቴ ትዝታ መጻሃፋቸው ላይ ይኼን የብሄር ጥያቄ አንጸባርቀዋል። ይሁን እንጂ ቀኃሥን ለማስወገድ የተረባረቡት ተማሪዎችም፤ ደርግ መጠናከሩን ሲያዩ፤ “ኃይሌ ማረኝ ማረኝ፤ ደርግስ ምንም አላማረኝ” ማለት ጀምረው ነበር። ጃንሆይ ከመንግስቱና ግርማሜ ንዋይ የመንግስት ግልበጣ ሙከራ (የዛሬው ጠ/ሚ አባትም አንዱ ነበሩ)፤ ፈጣን ያስተዳደር መሻሻል ማድረግ ነበረባቸው የሚል ትችትም ይቀርብባቸዋል። እርጅናቸው፣የስልጣን ወዳድጅነታቸው፣የኤርትራ ወደ ኢትዮጵያ መቀላቀል፣የስራ አጥ ብዛት ማደግና የመሳሰሉት ተጠራቅመው ያው የካቲት ከች አለባቸው።  የሚገርመው ልጅ እያሱን ያስገደሉት(አቶ ዘውዴ እንደጻፉትም) እርሳቸው ናቸው። ጭቡ ደረሰባቸውና እርሳቸውንም መንግስቱ ገደላቸው።

Comments

Popular posts from this blog

የፋኖ አንድነት እንዴት?

እስከ ስባት ትውልድ!

አሞላቃቂ ጥቅመኛ!