ግምገማ? ወይስ?
ግምገማ? ወይስ?
የፋኖ
አንድነት ብስራት እየተጠበቀ ባለበት ወቅት፤ የቀድሞው የባልደራስ የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ አቶ ስንታየሁ ቸኮል በፅናት ሚዲያቸው
ላይ ስለ አርበኛ እስክንድር ነጋና በፋኖ ትግል ላይ ሃሳቦችንና ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ ግምገማዎችን እያስደመጡን
ነው።
1. አቶ ስንታየሁ ትግሉ በአማራ ጠላቶች በተለይ በብአዴን እንዳይጠለፍ፤ የፋኖ
የመሪዎች ምርጫ የአፋሕድና የአፋብሃ ብቻ መሆን አለበት እንጂ ማንም ከድርጅቶቹ ውጭ ሆኖ እከሌ ካልወጣ! እከሌ ካልገባ!
አንድነት አይመጣም የሚለውን የጠላት መሰሪነት በምሬት አውግዘዋል። ይኼን ብአዴናዊ አካሄድ እንፋለመዋለን ሲሉ ተደምጠዋል።
በጣም ነው የምስማማው።
2. ሆኖም አቶ ስንታየሁ በአንድ በኩል የመሪዎችን ምርጫ ለድርጅቶቹ ይተው
ቢሉም እርሳቸውን ግን የሚመለክት ነገር አይመስልም። በአርበኛ እስከንድር ነጋና በእርሳቸው መካከል ያለውን ቅያሜ ሳይደብቁ፤
እስክንድር ወደ ትጥቅ ትግል ቆርጦ ሲገባም ሆነ ቀደም ብሎ ከባልደራስ መልቀቂያ ሲያስገባ ውሳኔዎቹ እርሳቸውን
እንደሚጎዱ ባለማሰቡም ሆነ ቀጥሎም ከሜዳ እርሳቸውን ለማግኘት በቂ ጥረት ባለማድረጉ(በሻለቃ ዳዊት በኩል መልእክት
ቢደርሳቸውም) በእስክንድር ላይ ከማዘን አልፈው በመካድ ስሜት ላይ መሆናቸው ይታያል። በእንደዚህ ያለ ነገር ላይ መልስ
ሊሰጥበት የሚችል እስክንድር ብቻ ነው።አንድ ነገር ግን እዚህ ላይ ድቅን ይላል። እስክንድር እኮ የትጥቅ ትግል የጀመረው
ነፍሱን ለአገሩ ቤዛ ለመድረግም ነው። ለራሱም ነፍስ የማይሳሳና በቤተሰቡ ላይም የቆረጠ ሰው ነው።
3. አቶ ስንታየሁ ቀጥለው ደግሞ እስክንድር ስለመሰረተው የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ
ግንባርና ቀደም ሲል በእነ ዘመኔ ካሴ ስለተመሰረተው የአማራ ፋኖ ህዝባዊ ሃይል(እርሳቸው ንቅናቄ ይሉታል-ከአሁኑ አፋብሃ ጋር
የሚምታታባቸው ይመስላል) ሲናገሩ፤የሁለቱ ድርጅቶች መፈጠር በሁዋላ ችግር እንደሚያመጣ ቀደም ብለው መገምገማቸውን ይናገራሉ።
በመቀጠልም እስክንድር አዲስ ድርጅት ከማቁዋቁዋም ተቆጥቦ የህዝባዊ ኃይሉ ም/ሊቀመንበር ሆኖ ቢቀጥል ኖሮ የዘመነ ካሴን
ከእስራት መፈታት ችግል ላይ ሊጥለው ይችል ካልሆነ በስተቀር፤ መደረግ የሚገባው ይኼ አቅጣጫ መሆን እንደነበረበት አልተገመገመም
ይላሉ። ይኼን ለመጻፍ ያነሳሳኝም በዚህ የስንታየሁ ከሰማይ ላይ ዱብ ያለ ግምገማ ነው። እስክንድር ገና ጎጃም
ከመድረሱ በፊት ጠበቃ አስረስ ማረ በተሳተፈበት የዙም ስብሰባ ላይ ተገኝቼ ነበር። አስረስ በዚያን ጊዜ የነገረን የአማራ ክልል
ማንም እንዳይፈነጭበት የራሱ ጠንካራ ህዝባዊ ሰራዊት ያስፈልገዋል። በዚህ ረገድ አገዛዙ ሌላ ስጋት እንዳይገባው በጥንቃቄ
እየሰራን ነበር ያለን። ጌጥዬ ያለው በኢትዮ-360 ላይ እንደዘገበው፤ እነ እስክንድር ለህዝባዊ ሰራዊቱ የሽምቅ ውጊያ
እንጀምር ብለው ሃሳብ ቢያቀርቡም፤ በተለይ አስረስ “እንዴት በ21ኛው ክፍለ ዘመን የሽምቅ ውጊያ ለማካሄድ ታስባላችሁ?” ብሎ
ሃሳባቸውን እንዳልተቀበለ ተናግሮአል። ስንታየሁ ይኼ መረጃ ያላቸው አይመስልም። ግምገማቸውና ወቀሳቸው መሰረት የለውም። የቁጭት
ነገር ነው።
4. ያም ሆነ ይኽ እስክንድር የመሰረተው የአማራ ሕዝባዊ
ግንባር፤ የፋኖን አደረጃጀት በአራቱም የአማራ ግዛቶች ቅርጽ አስይዞታል። ከብርጌድ ጀምሮ ፋኖ እንዲደራጅ የተደረገውም በዚሁ
ወቅት ነበር። በሻላቃ ዳዊት የተመራው የዲያስጶራው ድጋፍም በጣም ጠቅሞአል። ዳዊት መጨረሻው ተበላሸባቸው እንጂ፤
በእስክንድር የተሾሙት ባላቸው ተመክሮና ችሎታ ነው። ቀጥሎም ዘመነ ተፈታ። ህዝባዊ ሰራዊቱና ግንባሩ እንዲዋሃዱ ጥረት ተደርጎ አልተሳካም። ከዚያም በአፋህድ ምስረታ የሆነውን
አይተናል። ህዝባዊ ሃይሉም የሁዋላ ሁዋላ ወደ ጎጃም ፋኖ ተሰይሞአል። እስክንድር ከትግስት ሌላ ምንም ጥፋት እንዳለበት ለእግዜአብሄር እንተወው።
5. ሌላው ትዝብት ስንታየሁ ራሳቸው በተናገሩት ላይ የተመሰረተ ነው።
እንደተፈቱ በአዲስ አበባ ለትጥቅ ትግል መሰናዶ በማድረግ መጠመዳቸውንና በአጭር ጊዜም በቂ ሰው ማደራጀታቸውን ነገሩን።እንደገና
በመታሰራቸው ወደ ሰሜን ሸዋ ጫካ የትጥቅ ትግል ለማድረግ የነበራቸው እቅድ ቢሰናከልም፤ እርሳቸው ያደራጁዋቸው ሰዎች አሁንም
በፋኖ ትግል ውስጥ እየታገሉ እንዳሉና እስካሁንም በአዲስ አበባ ያደራጁት ድርጅት እንዳለ ነገርውናል። እሺ ይሁን። ታዲያ ይኼ ሁሉ
መደላደል ባለበት ለምን ወደ ስደት ከመሄድ ይልቅ እንደ ብ/ጄ ተፈራ ወይም እንደ እስክንድር ወደ ሸዋ አልሄዱም?
ደግሞስ አገዛዙ ባሳደረቦት ተደጋጋሚ እስር የተከሰቶበት የጤና ችግር ብዙ ፈተና ለሚጠይቀው የትጥቅ ትግል ያመቻልን? የኔ ግምገማ አያመችም ነው። ዋናው ችግሮም በአሳዛኝ ሁኔታ ይኼው ይመስላል። ከአንድ አሜሪካ ካለ ወዳጄ ጋር ስንታየሁ ወደ አሜሪካ ቢመጡ በትግሉ
የተፈተኑ ስለሆነ ቢያንስ የውጩን እርዳታ ለማስተባበር ይችላሉ የሚል በጎ እሳቤ ነበረኝ። ይኼ ግን ተሸርሽሮአል አሁን።
በመጨረሻም...
ግምገማ
መካሄድ ያለበት ከስሜት ውጭ፤ በመረጃና በእውቀት ላይ ተመርኩዞ መሆነ ይገባዋል። ወቅቱም አስፈላጊ ነው። እስክንድር ከፕሮፌሰር
አስራት ቀጥሎ አማራ የለም የሚሉትን በራሱ ጋዜጦች ላይ፤ እንዴት ሆን ብሎው አማራን ለአደጋ እያጋላጡት እንደሆነና የክህደት
ፖለቲካም መሆኑን ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማሪያምን
ሳይቀር እደሞገታቸው ታሪክ ይመሰክራል። ሁለት መጻህፎችም ጽፎልናል።
እስክንድር
የኢትዮጵያን የፖለቲካ ተጨባጭ ሁኔታ ገምግሞ መአሕድ ወደ መኢአሕድ መለወጥ የለበትም ብሎ ኢ/ር ኃይሉ ሻውልን ከተቃወሙት ሰዎች
ቀዳሚው ነበር። ትክክለኛ ግምገማ ነበር ያደረገው።
ወያኔን
አብይ አህመድ ሲተካው እስክንድር ለአብይ የመቶ ቀን እድል ሊሰጠው ይገባል ያለ ሰውና ቀጥሎ አምባገነን ነው ብሎ የገመገመው።
ስንታየሁ ቸኮል ግን አብይ አህመድን “እባክዎት ኢትዮጵያዊ ሁኑ” እያሉ ነበር የሚማፀኑት።
እስክንድር
የአዲስ አበባን የህዝብ ስብጥር ለመለወጥ የሚደረገውን ፕሮጀክት ቀደሞ የተረዳና የተቃወመ ነበር። በተባበሩት መንግስታት ድርጅት
ተገኝቶም የዘር ፍጅት አደጋ በአማራው ላይ እንደተጋረጠ ቀደሞ ያስጠነቀቀ፣ ነገሮችን ቀደም ብሎ ለማየት በመደበኛ
ትምህርት፣በሞራልና በመረጃ የታጠቀ--እንዲሁም ለየት ያለ ተክለሰውነት ያለው ሰው ነው። ታላቁ እምንለው ከሜዳ ተነስተን
አይደለም። ያም ቢሆን ሰው ስለሆነ ፍጽም ነው ማለት አይቻልም። የፋኖን የመሪ ምርጫ ለድርጅቶቹ ብቻ እንተው ካልን በምርጫው ወቅት በአደባባይ አንዱ መሪ
ለመሆነ የሚጠበቀውን ሰው የማሳነስ ስሁት የግምገማ ዘመቻ መክፈት የሚያሳየው፤ አቶ ስንታየሁም የኢትዮጵያ ፖለቲካ ከታመመብት የምቀኝነት ክፉ ደዌ ያልተፈወሱ
መሆናቸውን ነው።
Comments
Post a Comment