ትንሹ እስክንድር ነጋ!
ትንሹ እስክንድር ነጋ፤ጋዜጠኛና አርበኛ ጌጥዬ ያለው
ባለፈው ስለ አንዳንድ አሞላቃቂ ጥቅመኞች የኢሳት ፍርስራሽ ሚዲያዎች የከሰረ የጋዜጠኝነት ስነምግባር ይዘቶች በደምሳሳው አይተናል።
ዛሬ አንድ
ሌላ ማንሳት በሚገባን፤የኢትዮ-360ው፤ አይጠገቤ ጋዜጠኛና አርበኛ ጌጥዬ ያለው እንጀምር። ጌጥዬ
በሞራል ከፍታው ትንሹ እስክንድር ነጋ ሊባል የሚገባው ነው።ከትግል ሜዳ ሆኖ ከየፋኖ ውሎ ፕሮግራሙ በተጨማሪ፤ የሚሰጣቸው ትንታኔዎች
ሰፊና ጥልቅ ንባቡን የሚያንፀባርቁ ናቸው። የማያውቀውንም አላውቅም ነው የሚለው። ትሁትና የሰላ አእምሮ ነው ያለው። ሲወድም ሲተችም
አያዳላም። እውነተኛ ሰው ነው። የጌጥዬ የድምፅ ፍሰትና ቃና አድማጭን ከመቀመጫው እንዳይነቃነቅ የሚያደርጉ ማግኔቶች ናቸው።ሌሎች
ከጊጥዬ መማር አለባቸው።በሚዲያ ላይ ቀርቦ መቆጣትና መደንፋት የአድማጭን የማድመጥ አትኮሮት ይቀንሳሉና።በዚህም መሰረት ኢትዮ-360
ለእውነት በቆሙ የአማራ ይሁን የኢትዮጵያ ልጆች የተካተቱበት ስለሆነ በገንዘብም በሃስብም ሊደገፍ የሚገባው ተቁዋም ነው።
ከኢሳት
ፍርስራሾች ውጭ ብዙ ሚድያዎች አሉ።የጣና ቲቪ እስካሁን ለፋኖ ትግል እየሰጠ ያለው አበርክቶ ግሩም ነው። ከኢትዮ-360 ጋር ስራቸውን
በቅንጅት ሊሰሩ ቢችሉ ጥሩ ይመስለኛል፤ ችግር ከሌለ።አብረው ለፍኖ መሪዎች ጥሪ በማድረግ የአመራር ብቃታቸውን ህዝብ የሚመዝንበትን
መድረክ ማመቻቸት ይችላሉ። ጥሪ አድርገው እምቢ የሚሉትን ለህዝብ ማሳወቅ ይገባቸዋል። ይኼን ማድረግ ጥቅሙ ብዙ ነው። እንደው በጥቂቱ፤
መጀመሪያ የፋኖ ግለሰብ ታጋይ እውነተኛ መሪዎቹን በትክክል እንዲያውቅ ያስችላል፤ህዝቡ የሚያደርገውም እርዳታ ለተገቢው የፋኖ አደረጃጀት
ፈሰስ እንዲሆን ይረዳል፤በድል ማግስትም የተፈተነና የታመነ አመራር ስልጣን ሲይዝ አገር ይረጋጋል።
ከኢትዮጵያ ጎረቤት አገሮች ሆነው መረጃ የሚያሰራጩት ጋዜጠኞች ውገናቸው ግልጽ ነው። አሳዬ ደርቤ፣ሙሉጌታ አንበርብር፣በቃሉ አላምረው፣በላይ ማናየ፣በለጠ ካሳንና ቴዎድሮስ አስፋውን ተከታትያለሁ። ወደ ዝርዝሩ ሳልገባ እነዚህም ለራሳቸው መተዳደሪያ የሚሰሩ፣የተወሰኑ የፋኖ አመራሮችን በማግዘፍ የተጠመዱና እንዲሁም ካላቸው መረጃና አስቸጋሪ የስደት ኑሮ ላይ ሆነው በመረጃ የተደገፈ የሰላ ትንታኔና ትችት የሚያቀርቡ ናቸው። እነዚህ የአቅም ጉዳይም ሊገድባቸው ስለሚችል የፋኖ አመራሮችን በአደባባይ አቅርበው ህዝብ ራዕያቸውን እንዲያውቅ የሚያስችል ሁኔታ ላይ ያሉ አይመስለኝም።
እንደማጠቃለያ

Comments
Post a Comment