አራት ኪሎ ያለው ሰውዬ፤ ለዘላቂ ሰላም ይሰራል?
- Get link
- X
- Other Apps
ዛሬም ጦርነት ውስጥ ገባን። ከዚህ ጦርነት በፊት ከኤርትራ ጋር ተዋግተን ነበር። እኔ የዚያኔ ጦርነቱን የደገፍኩት ሻእቢያ አክርካሪው ይመታል፤ አስብንም በእጃችን እናስገባለን ብዬ ነበር። ይሁን እንጂ አራት ኪሎ የተቀመጠው ሰውዬ አጭበርባሪ ስለነበረ፤ 70 ሺህ ዜጎች ገብረን ጦርነቱን ብናሸንፍም በመጨረሻ ሙልጭ ወጣን። አሁንስ አራት ኪሎ ያለው ሰው የሚታመን ነው ወይ? በተለይ በአማራው ጉዳይ? እስኪ ዞር ብለን እናስብ፡፡
1. አብይ ጠቅላይ ሚኒስትር እንደሆነ ትግራይን ጎብኝቶ ነበር። ታዲይ በአደባባይ ንግግሩ ወልቃይትን አንስቶ፤ የወልቃይት ጉዳይ የልማት እንጂ የማንነት እንዳልሆነ ነገረን። ብዙም አልተደነኩም። ምክንያቱም ገና ያልጠና ወንበሩን በማደላደል ላይ ስለነበር፤ በዚያን ወቅት የወልቃይትን ጥያቄ መግፍቱ ለስልጣኑ አደጋ ሊሆን ይችላል በሚል አመክንዮ ነበር፡፡
2. ከትግራይ መልስ ደግሞ አማቾቼ ለሚለው የጎንደር ሕዝብ ባደረገው ንግግር ላይ...”የቅማንት ጥያቄ” የሚባለውን ክብደት ሰጥቶ ማንሳቱን ላስተዋለ ሰው አብይ ለአማራው አንድነት በጎ ሰው እንዳልሆነ ፍንጭ የሰጠበት አጋጣሚ ነበር፡፡ ይኼን የወያኔ እኩይ ከፋፋይ ሴራ እንደ ቅማንት መብት ቆጥሮ በአደባባይ መሞገቱ፤ አማራውን ለማዳከም የሚደረጉትን ስልቶች የሚጋራ ለመሆኑ አስረጂ ነውና፡፡
3. በአዲስ አበባ በተለይ አማራው በልማት ስም በግፍ ሲፈናቀል፤ 'የእኔ ስራ ከንቲባነት አይደለም፤ አልሰማሁም' ብሎ ያላገጠና የዋሸ እለትም፤ ሌላው አማራ ጠልነቱን ያስረገጠበት ሃቅ ነበር።
4. አብይ ስልጣን ከያዘ ጀምሮ በየቦታው የሚጨፈጨፈውን የአማራ ጥቃት ከግጭት በላይ ለማየት ያለመፈለጉም፤ ሌላው ለሰው ልጅ ሕይወት ይሁን ለአማራ ያለውን ደንታቢስነት የሚያሳይ ነው።
5. የሰኔ 15ቱ ግድያ ይሁን ቀደም ሲል የኢንጂነር ስመኝው ግድያ እስካሁን ያልዘነቡ ጥቁር ደመናዎች ናቸው።
6. እስክንድር ነጋንና ባልደረቦቹን (ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ) እንደ ፖለቲካ ተቃዋሚ ሳይሆን ፤ እንደ ጠላት የማየቱ የአደባባይ ሚስጥርም ከአማራ ጠልነቱና ከስልጣን ስግብግብነቱ ጋር የተቆራኘ ነው። የልደቱም የእስር ድራማም ከዚህ ጋር ተነጥሎ ሊታይ የማይችል ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ በእስር ላይ እያሉም፤ እነ እስክንድርና እነ ጃዋር መሃመድ እኩል መብት የላቸውም፡፡ እነ ጃዋርን ብዙ ሰው ሊጠይቃቸው ሲችል፤ ይኼውም መብት ሆኖ ለእነ እስክንድር አልተፈቀደም፡፡ አብይ ክርስቲያን ነኝ ቢልም ፍትህን አያቃትም፡፡
7. አብይ ይሁን የራሱ መከላከይ ሚኒስትር፤ ከወያኔ ጋር የሚደረገው ውጊያ የአማራውን ታሪካዊ የመሬት ይዞታዎች ማስመለስ እንዳልሆነ ተናግረዋል። ነገሩ ትክክል ነው። ምክንያቱም ጦርነቱ የተጀመረው ወያኔ ስሜን እዝን በማጥቃቱ እንደሆነ ማንም አያጣውምና፡፡ ይሁንና ተነጥቀው የነበሩ የአማራው ታሪካዊ የመሬት ይዞታዎች በዚሁ ጦርነት በአማራው ደም ጭምር ስለተመለሱ፤ ይኼን ፍትሃዊ ጉዳይ እውቂያ ለመስጠት አብይ አህመድ አልፈልገም፡፡ እንደውም “ምእራብ ትግራይ” በማለት ምናልባት ወደፊት ሊወስድ ስላቀደው ደባ የቁጣችንን ልክ አስቀድሞ ይለካዋል፡፡ ለነገሩ አብይ ለአማራው ሃጃ/ግድ ቢኖረው ኖሮ፤ በግድ በኦሮሚያ ክልል ስር ሆኖ ለሚሰቃየው የደራ አማራ በአንድ የስልክ ትእዛዝ መብቱ እንዲከበር ማድረግ አይገደውም ነበር፡፡ የደራ አማሮች ብሶታቸውን የሚገልጡት አብይ እንደጠላቱ ለሚያየው ባልደራስ ቤሮ እየሄዱ ነው፡፡
8. የሆኖ ሆኖ፤ ዛሬ ደግሞ የወጣው የጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሮ መግለጫ ፤ “ምእራብ ጎንደር” በሚል ሃቁን ለማንጸባረቅ የሞከረ ይመስለኛል፤ ባለፈው “ምእራብ ትግራይ” የሚባለውን ዋዘኛ መግለጫ ተቃውሞ ስላስነሳ ይሆን? ወይስ ከልብ ታምኖበት? አብይ አይታመንም፡፡ እንደ መለስ ዜናዊ ውሸታም ነው። የአንድ አገር መሪ ሆኖ ቁጥር ስፍር የሌላቸው ውሽቶች ተናግሮአል። እምነት ሊጣልበት የሚችል ሰው አይደለም፡፡ አብይ የሚመራውን ዳግመኛ ኢህአዴግ ቀጣይ የፖለቲካ ሃይል ለማድረግ ከተፈለገ፤ እውነተኛ ተሃድሶ ያስፈልጋል፡፡ የማይዋሹ፣ የጠለቀ የአካባቢም ሆነ የአለም ተመክሮ ያላቸውና በእርግጠኝነት የጎሳ ፊዴራሊዝምን በመልካ ምድር ፊዴራሊዝም ለመለወጥ ቁርጠኝነትን ያሳዩ “ሙስጠፌዎችን” ወደፊት ማምጣት አለበት፡፡ አለበለዚያ የአብይ ፓርቲ ወያኔን ቢያሸንፍም በዚህ በኦሮሙማ የዘር ፖለቲካ ተመርዞ ስለሚቀጥል በኢትዮጵያ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፍትህን ማስከበር አይቻልም፡፡ ይኼም ለሁከት እንጂ ለሰላም በር አይከፍትም፡፡
9. እስኪ ደግሞ አብይ አጠገቡ ያቀረባቸውን ሰዎች እንመልከት። አንዱ ተከዜን ተሻግሮ መጀመሪያ ወልቃይቴን/አማራን ማረድ የጀመረው፤ በበርሃ ስሙ በሪሁን ወይም ዛሬ ዶ/ር አረጋዊ በርሄን ነው፡፡ ለምን አብይ አረጋዊን እንደዚህ ወደደው? ችሎታ ስላለው? ውስጡን ለቄስ፡፡ በሪሁን የወያኔ ዋና አበጋዝ በነበረበት ወቅት ወልቃይቴን ብቻ አይደለም ያረደው፡፡ በአንድ ወቅት፤ በወያኔ የተማረኩ የኢትዮጵያ መደበኛ ወታደሮችንና ሚሊሻዎችን እንዲለዩ ካደረገ በሁዋላ ፤ “የወያኔ ታጣቂዎች በመደበኛ ወታደሮቹ ላይ ኢላማ እንዲለማመዱባቸው ያደረገ አረመኔ ነው።” ይኼን ጉዳይ ያጫወተኝ ሆላንድ የሚኖር ሐኪም ሲሆን፤ ቀደም ሲልም በኢትዮጵያ ሰራዊት ውስጥ በውትድርና ያገለገለ ሰው ነው፡፡ እሱም መረጃውን ያገኘው ወያኔ አገርህ ግባ ብሎ ካሰናበተው ሚሊሻ ነው፡፡ ይኼን ከሰማሁ በሁዋላ ከአረጋዊ ጋር ልቅሶ ቤት ተገናኘን፡፡ እኔም ሃዘንተኛዎቹንና ልቅሶ ደራሾችን ሁሉ ሰላምታ ስጥቼ፤ እርሱን ግን ሆን ብዬ ፊት ነሳሁት፡፡ ያን በደም የተጨማለቀ እጁን መንካት ተጠየፈኩ! ይኼ የአረጋዊ የግፍ ፈለግ ነው ዛሬ አድጎ ወያኔ በሰሜን እዝ ላይ ያደረገው አይነት አስቃቂ ግፍ የተከሰተው፡፡ አረጋዊ በርሄ የአማራ ቀንደኛው ጠላት የአብይ አህመድ የልብ ወዳጅና ተሹዋሚም ነው፡፡ ታዲያ እንዴት ነው አራት ኪሎ የጠቀመጠውን ሰውዬ አማራ ጠል ብለን ልንፈርጅ የማንችለው? ወዲያ በል! ሚስቱ አማራስ ብትሆን? የቀደምት አራጆች፤ መንግስቱም ይሁን የመለስ ሚስቶችም እኮ አማሮች ናቸው፡፡ የአህያ ባል ከጅብ አይድንም እንዲሉ፡፡
11. እንዲጠናከር የማይፈለገው፤ የሚፈራው የአማራ ልዩ ኃይል፤ ፋኖና መከላከያ ባደረጉት ታሪካዊ ፍልሚያ አሮጌው ወያኔ የፍሽት አስተዳደር ዛሬ ከጎንደርና ከወሎ አማራ እርስቶች ተጠራርጎ ወጥቱዋል፡፡ ይኽ እውነትም ዶ/ር ዳናቸው ተሸመ እንዳለው የወልቃይትን እምባ ያበሰ ጉዳይ ነው፡፡
12. ከእንግዲህ የወልቃይት ይሁን የሌሎቹ ወደ ትግራይ ተጠቅለው የነበሩ ግዛቶች ችሎታ ባላቸው፣ ሲገፉ፣ ሲሰቃዩ ፣ሲሳደዱ በነበሩና ዛሬ ወደ አገራቸው በመመለስ ላይ ባሉ ሰዎች መተዳደር አለባቸው፡፡ የአብይ የትግራይ ክልል ተሹዋሚ ዶ/ር ሙሉ በዚህ ጉዳይ ምንም ስልጣን እንደሌለው ሆዱ እንደሚያውቀው ሁሉ ድርጊቱም መስካሪ መሆን መቻል አለበት፡፡ የአማራ ክልል አስተዳደርም ከአብይ አሽከርነት እስካልወጣ ድረስ እምነት ሊጣልበት አይችልም፡፡ ጦሩም ይኼ ጉዳይ ዳግም ከተንሻፈፈ፤ ባንሻፋፊው ላይ እርምጃ መውስዱ የሞራል ግዴታው መሆኑን ማወቅ አለበት፡፡ እነ ኢዜማም በዚህ ጉዳይ ላይ ዛሬውኑ አቁዋማቸውን ግልጥ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡
13. የዛሬ 50 አመት ገደማ አረጋዊ በርሄ ተከዜን ተሻግሮ የለኮሰው የአማራ የዘር ፍጅት ስለባዎቹን ለመዘከር፣ ለትምህርታዊነቱና ለተጠያቂነት ይረዳ ዘንድ፤ በባለሙያዎችና በገለልተኛ ተቁዋማት የሚመራ የማጣራት ስራ መደረግ አለበት፡፡ ለሰለባዎቹም መታሰቢይ ሊቆምላቸው ይገባል፡፡ በወልቃይት የሰላም ምርምር ተቁዋም መመሰረት አለበት፡፡ በመጨረሻም፤ ዋናው ጉዳይ፤ ይኽ ጦርነት ከጎሳ ፖለቲካ አገሪቱን ካላወጣ የወያኔ መደምሰስ እልል የሚባልበት ቢሆንም፤ ሁሉም ነገር የወያኔ የጎሳ ፖለቲካ ሃሳብ/ኢዶሎጂ ተሸካሚ ለሆነው አብይ አህመድ ከተተወ፤ ዛሬ ወያኔ ቢሸነፍም፤ መርዘኛና ሁውላ ቀር ሃሳቡ ስለሚቀጥል፤ የወደፊቱ ሰላማችን ዘላቂ እንዳልሆነ ድፍን ጦቢያ ሁሉ ሊያጤነው ይገባል፡፡
Like
Comment
Share
ቦጋለ ካሣዬ/ኦትዋ/11/14/2020
- Get link
- X
- Other Apps
Comments
Post a Comment