መልሰ ብዬ ሳየው...4
... አሳዬ ከሐሰን ቱሬና ከከዲር ዋቆ ጋር ተገኛኝተው መንግስት ደኑን በጄት ለመደብደብ አስቧልና ይህ ጉዳት ከመደረሱ በፊት በሰላም እጃቸውን ለመሰጠትና የሚይቀርቡትም ቅደመ ሁኔታ ካላ ቀጥታ ከእንደራሴው ጃጋማ ኬሎ ጋር ለሁለቱም አመቺ ቦታ ፈልገው ለማገናኘት እንደሚሞክሩ ባቀረቡት ሃሳብ መሰረት ... ሐስንም ሆነ ከዲር እንዲሁም ሁሴን ዳዲ፤ በከር ጂሎና ሐጂ ተመካክረው ተስማሙ። መጀምሪያ ግን ከከዲር ዋቆ ወደ ሰላም እንዲገባ እንፈልጋለን። እኛም ሁኔታውን እያየን ተራ በተራ ወደ ሰላማዊ ኑሮአቸው ለመመለስ ማለትም እጅ ለመስጠት ፍላጎት አለን። ካሳሁን ስምምነቱን ይዘው ከሃሰን ቱሬ ሰላይ ኡመር ሃስን ጋር ወደ ጎባ በማቅናት ከእርሳቸውም ሆነ ከሐሰን ቱሬ ወዳጅ ከሆኑት አቶ ንጉሴ ገረመድሕን ቤት በሁለተኛው ቅዳሜ እቴቱ ላይ ደርሰው አዳር ያደርጋሉ። እቴቱ ከጎባ 10 ኪሎ ሜትር የምትርቅ የገጠር ቀበሌ ናት። በማግስቱም ኡመርን ንጉሴ ቤት ትተው እነ ከተማ ከእንቅልፋቸው ገና ሳይነሱ፤ ልጆች! ከተማ! አቡ! በሩን ክፍተሉኝ ሲሉ ተጣሩ። አሳዬ ጃጋማን በአስቸኳይ ለማነጋገር ቀርቶ ስልጣናቸውም በቀጠሮ እንኳን ቢሆን ለማነጋገር ስለማያስችሏቸው ዘዴ መፈለግ ነበረባቸው። ጊንር ሰራተኛ በነበሩበት ጊዜ በጣም ወዳጃቸው ና ጃጋማን በቀላሉ ለማግኘት የሚችል በቀለ ቱሉን ማነጋገር ነበረባቸው። እንዳሰቡትም በቀለ በሌላ ሁነኛ ሰው በኩል መልእክቱን ለጃጋማ እንዲድደርስ አንደረጉ። ጃጋማም በመገረም አቶ ከበደን ሰኞ ጥዋት በ 2.00 ቢሮአቸው እንዲመጡ አስጠሩዋቸው። ማ ታውኑ ከበደ የሆነውን ለካሳሁን ሲነግራቸው በጣም ተደስተው ጃጋማ ከተመቻቸው ንፍስ ለመቀበል ብለው በመኪና እቴቱ ድረስ ላይን ያዝ ሲል ቢመጡ ኡመርን...