አዲስ ነፍሰ ገዳይ... አሮጌ ነፍሰ ገዳይ!
ወያኔ ስልጣን እንደያዘ በተቃውሞ ጎራ የተሰለፍነውን ኢትዮጵያውያን ብዙ ፈተና ገጥሞን ነበር። አንዱ ማን ምን አድርጎ ከኢትዮጵያ እንደወጣ አለመታወቁ ነው። ከ 1991 በፊት ለስደት የተዳረጉት ከቀይ ሸብር ነጭ ሽብር ያመለጡ ናቸው። እንደኔ ያሉት ደግም ለትምህርት ወጥተው ቀልጠው የቀሩ ናቸው። ታዲያ ገና ወያኔ ስልጣን እንደያዘ እዚህ ሆላንድ ...የኢትዮጵያ ሕልውና በጎሳ ፖለቲካ ወዴት ሊያመራ እንደሚችልና ስለ ኤርትራ ጉዳይም ብዙ ኮንፍረንሶች ይካሄዱ ነበር።
በእነዚህ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ሰው የገደሉም ሆነ ያስገደሉ ሰዎች ሊሳተፉ ቢችሉም መረጃ ሳይገኝ ማንም ላይ ጣት መቀሰር አልተቻለም። ዛሬ ወያኔ ሳይቀር የተፋቸው አጭብጫቢዎች ግን ተቃውሞው የሚሰነዘረው ስልጣን ከተነጠቁ የደርግ ቡችሎች ነው እያሉ ይጽፍ ነበር።
አንዴ አዲስ ዘመን ጋዜጣ ባህርዳርን ከኢሕአፓ ለማጽዳት በሚል ዘመቻ የተገደሉ ከ50( 57?) በላይ የሰዎች ስም
ዝርዝር የያዘ ሰነድ ኢፋ አደረገ። 'አብዮታዊ እርምጃ'' እንዲወሰድባቸው የተደረጉት ሰዎች በጥይት አልተገደሉም።
አንገታቸው በገመድ እየታነቀ ነው... ማነቁ ያስፈለገው የባህርዳር ነዋሪዎች የጥይት ድምጽ እንዳይሰሙ ተሰግቶ ነው።
ከተገዳዮቹ የ18 አመት ልጅም አለችበት። ጥፋትዋም ከቤተሰቦችዋ ቤት መወረሱ ነው። የሚገርመው ግድያው ደግሞ
የተካሄደው ከቀይና ነጭ ሽብር በሁዋላ ነው። የግድያውን ማዘዣ የፈረመው የደርጉ መቶ አለቃ እሸቱ አለሙ ነው።
ይኼው እሸቱ አለሙ ነው ደግሞ በየስብሰባው እየተገኘ ስለ ኢትዮጵያ አንድነት የሚያስተምረው። አንዴ ስለ
ስንደቅ አላማችን ያለውን ክብርና ፍቅር የገለጸበትን የጋለ ስሜት የታዘቡት ፕሮፌሰር ጌታቸው ሃይሌ...” ይኼን
ስስማ... ስልጣንን ለደርግ መልስለት! መልስለት !አሰኘኝ” ብለው አሾፉበት።
ታዲያ አዲስ ዘመን ያተመውን ሰነድ በእንጊሊዘኛ ተርጉመን አግባብ ላላቸው የዚህ አገር ባለስልጣን አካላት ላክን። በመጽሄት ላይም ወጣ። ይሁን እንጂ እሸቱ አለሙ የዳችም ዜግነት ተሰጥቶት ፔንጤም ሆነና በሰላም መኖር ጀመረ። ሰላም ያጣነው እኛ ነበርን... ከነፍሰ ገዳይ ጋር በአምስተርዳም መዲና እየተገፋፋን የምናልፍ። ዴሴምበር 22/2014 እሸቱን አምስተርዳም ደ-ዳም የሚባል አደባባይ ፊለፊት ያለ የልብስ መደብር ውስጥ ሳየው ሰውነቴ ሁሉ ተለዋወጠ። ሁኔታዬን ያየቺው የመደብሩ ሰራተኛ ደህና መሆኔን ጠየቀችኝ... ነገርኩዋት ይኼ ስንት ሰው የጨረሰ ሰው ነው ይኼው ግን እንደ ነጻ ሰው በነጻ አገር ይጋፋናል አልኩዋት። ዘመዶችህን ገድሎብህ ነው አለቺኝ? ምንም ዘመዴን ባይገልብኝም …ነፍሱዋ እንዲራራ ብዬ መስለኝ …አዎ! የ18 አመት እህቴን ወንድሞቼን ገሎብኛል አልኩዋት። ፊትዋ ደም መሰለ። የሆላንድ ባላስልጣኖች እንደሚያውቁ ስነግራት ገረማትና "ወይ ፖለቲካ" ብላ ተገረመች።
ዛሬ ከስራ መልስ.. መኪና ውስጥ ነው ሬዲዮ ዜናውን ያበሰረኝ! እሸቱ በቁጥጥር ስር መዋሉን! ቤቴ ገብቼ የጽሁፍ ማስረጃ መፈለግ ጀመርኩ። እነሆ ፓሮል የሚባል የዳች ጋዜጣም የደርጉ ፍሽት መታሰሩን ዘግቡዋል። ፓሮል ወሬው ቀደም ሲልም ተስምቶ እንደነበር ገልጦ አሁን ግን ወያኔ ፋይሉን ስለላከውና እዚህ ያሉ ኢትዮጵያውያንም በጎጃም ስለተገዱሉት ሰዎች ምስክር ስለሰጡ ነው የታሰረው ይላል። እሽቱ መታሰሩ እሺ በጄ... ለመሆኑ ታስሮ እዚሁ ነው የሚዳኘው ወይስ ለወያኔ ይሰጣል? ይኼ ሁሉ አያሳስበኝም። የሚያሳዝነኝ ነገር ግን አዲስ ነፍስ ገዳይ አሮጌ ነፍስ ገዳይን ማሳደዱ ነው። መቼ ይሆን ህዝብ የመረጣቸው ጀግኖች ስልጣን ይዘው ነፍሰ ገዳዮች ሁሉ የሚዳኙት? ዳጆች ስብአዊነት ቢሰማቸው ኖሮ እሽቱ ለፍርድ መቅረብ የሚገባው የዛሬ ፪፬ አመት ነበር። ለመሆኑ እነዚህ በእሸቱ ላይ የመሰከሩት እነማን ይሆኑ? የወያኔ ወኪሎች ወይስ የተጎጂዎቹ ዘመዶች?
http://www.parool.nl/…/Ethiopische-oorlogsmisdadiger-aangeh…

Comments
Post a Comment