ፕሮፌሰር መስፍን ፤ በጻፉት ላይ የግል አስተያየቴ፡ የእርሳቸውን ጽሁፍ ለማንበብ ጠቅ ማድረጊያው ሊንክ፤
https://www.facebook.com/pages/Prof-Mesfin-Woldemariam/120300297984572
የእኛ ተራ ነው!
በአንድ
የአፍሪካ ቀንድን ሰላም፤በሚመለከት የተዘጋጀ ሴሚናር ላይ ከአንድ የጁቡቲ ተወላጅ ጋር ተዋወቁኝ። እንዲህ አለቺኝ፤…«አሁን ጅቡቲን
ማስተዳደር የእኛ ጎሳ ተራ ነው፤ ምክንያቱም ባለፈው ሲያስተዳድሩ የነበሩት የእከሌ ጎሳ ነበርና”። ልክ እንደ ወያኔ ትግሬዎች ምንም
ሃፍረት ሆነ መሳቀቅ ከፊትዋ አይታይም። ጎሰኝነት አንዱ ዋናው ጠባዩ አግላይነት(ዘረኝነት) ቢሆንም፤ ለርሱዋም ሆነ ለወያኔ ትግሬዎች ግን ጎሰኝነት
ተቀባይነት ያለው ነገር ነው። የጅቡቲ ነዋሪዎች ከ60% በላይ ሶማሌዎች
ሲሆኑ አፋሮች ደግሞ ወደ 35% ናቸው። ትግሬዎች በኢትዮጵያ ከ6% አይበልጡም።
በዚሁ
ኮንፈርንስ ላይ የወያኔን ስልጣን መጨበጥ አስመልክቶ እንዲህ ተብሎ
ነበር። “ትግሮቹ ድሃ ስለሆኑ፤ የነበራቸው አማራጭ የብሄርን ጥያቄ
አንስቶ ህዝባቸውን ቀስቅሰው ስልጣን ላይ በመውጣት የአገሪቱን ሃብት መቆጣጠር ነው። አሁን ስልጣን ይዘዋል። ወደፊት ግን ሁለት
ነገሮች ሊፈጠሩ ይችላሉ። አንደኛው፤ በልተው ወፍራም ሲሆኑ፤ ስልጣን ሊያካፍሉ ይችላሉ። ይኼ ከሆነ ለዴሞክራሲ ተስፋ አለ። አሊያ
ግን መብላታቸውን ብቻ ከቀጠሉ፤ የሚገጥማቸው ተቃውሞ አደገኛ ይሆናል። አገሪቱንም ወደ ከፋ ደረጃ ያደርሳታል።” እየሆነ ያለው የመጨረሻው
ነው። እንኩዋንስ ፉት ቢሉዋት ጭልጥ በምታክል የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ይቅርና፤ ቻይና እንኩዋን እንዲህ እያደገች ገና ከ300 ሚሊዮን
ሕዝብ በላይ ከድህነት ማውጣት አለባት። የቻይና ሕዝብ ሁሉ በቻይና እድገት አልተጠቀመም ማለት ነው።
እርግጥ
ነው፤ በፖለቲካ ተጨባጭኑም ማየትና በጥልቅ ማሰብ ከመደናበር ያድናል። ስለ ኢትዮጵያ ደግሞ ሲናገሩ መደመጥ የሚገባቸው እዚያው ከህዝቡ
ሳይለዩ አብረው የሚታገሉት የህዝብ ልጆች እደሆኑ ማንም ይስማማል። ይሁን እንጂ እኛ ስደተኞቹ እዚህ ሆነን የምናየው ሃቅ አለ።
እስኪ ለመሆኑ ለውጭ አገር ትምህርት በአብዛኛው እድል፤ ለምሳሌ በሆላንድና በቤልጄየም የሚሰጠው ለማን ነው? ለትግሬዎች አይደለም
እንዴ? በበቂ መረጃስ የተረጋገጠው፤ አየር ኃይሉን፣አየር መንገድን፣ደህነትን ሌላውን ጦር የሚቆጣጠረው ማነው? ትግሬዎች አይደሉም
እንዴ? ባንኩን፣ግንባታን፣እንዱስትሪን፣መሬትን የተቆጣጠሩት ማናቸው? ትግሬዎች አይደሉም እንዴ? ሌላው ይቅርና ትግሬ ያለሆኑ ሰዎች
ቤት ሰርተው፤ ግብር ከፍለው ቤታቸውን ለመረከብ የሚቀላቸው ዘዴ የትግሬ ዘመድ መፍለግ አይደለም እንዴ? አንድ ቤት የሰራ ሰው ሚስቱ
ትግሬ ከሆነች ቤቱን ካላችግር ይረከባል። ታዲያ ወያኔ በዚህች ትንሽ ኢኮኖሚ ስንት ሰው ጠቀመ? 250 000 ሺህ? ከኢኮኖሚው ትልቅነት
አንጻር ስናየው ይኽም ቀላል ቁጥር የሚባል እኮ አይደለም። እንደውም
አውሮፓ ስደት ለመጠየቅ የሚመጡት ትግሬዎች፤ ለምን ትሰደዳላችሁ? ሲባሉ…” ለሁላችን የሚሆን የለም። አገሩ ግን ሰለም ነው እኮ
ነው። ደርግ ወድቁዋል። የሚሉን”። "ኤርትራውያን" ነን ብለው ነው የፖለቲካ ጥገኝነት የሚጠይቁት። ወያኔን በልባቸው ይደግፋሉ። ተቃውሞ ስልፍ አይወጡም።
ስለዚህ
ጉዳዩ ወያኔ ትግሬን ጠቀመ አልጠቀመም የሚለው አይደለም። ጠቅሙዋል። በአይን በብረታችን የምንየው ጉዳይ ነው። ችግሩ የጎሳ ፖለቲካ
ጠባይ ነው። ምንይልክ ቤተመንግስት ውስጥ ሌሎች ጎሰኞች ስልጣን ቢይዙ ኖሮ የሚያደርጉት ይኸንኑ ነበር። ስልጣን ከያዘ ጋር ፍርፋሬ
የሚጋራ የሌላም ጎሳ ተጠቃሚ እንደሚኖር የማይካድ ነው።
የፕሮፌሰር
መስፍን ጽሁፍ የተጻፈው በእኔ አስተያየት፤ ወያኔ ትግሬን ጠቀመ እያልን ስንናገር፤በተዘዋዋሪ በትግራይ ህዝብ ላይ ሌላው እንዲነሳበት
መቀስቀስ ስለሚሆን፤ ይኸም በቀላሉ ወደ ከፍተኛ ግጭት ከሄደ የሚከተለውን አደጋ አርቆ በማየት ነው። ዋናው ጥያቄ ግን አርቆ በማየት
መጻፍና መናገር ይቻላል። አርቆ የሚያዩትን የማይሰማ የወሮበላ ቡድን በተጨባጭ በሚፈጽመው ግፍ የተንተከተከው ጎሞራ ፈንድቶ ከወጣ
አደጋውን ማስቆም ይቻላልን? ማንም ጤነኛ ሰው ግን የማይስተው አንድ ነገር አለ። የኢትዮጵያ ሕዝብ(የትግራይን ጨምሮ) ካለምንም
ተጽእኖ የወከለው አስተዳደር እስካሁን አልመጣም። ስለዚህም ሁሉም ትግሬ ወያኔ ለሚፈፅመው ግፍ ተጠያቂ አይደለም። ይሁን እንጂ አንድ
ሕዝብ ጥቅም ሲያገኝ በማንኛውም ስርአት ቢሆን እምቢ አይልም። ከሙሶሎኒ ጋር ኢታሊያውያን፤ ከሂተለር ጋር ጀርመኖች ጨፍረው ነበር።
ሁለቱም ሲወድቁ ግን የተቀጡት ቁንጮዎቹ ናቸው እንጂ ሕዝቡ አይደለም።
የኢትዮጵያ
ነገር እልህ አስጨራሽ ነው። የሚሻለው ጎሰኝነትን አክ! እንትፍ! አድርጎ የመረረ ትግል ማካሄድ እንጂ፤ አደጋን በመፍራት ተጠቀመ
አልተጠቀመ እያሉ መጨነቅ አይመስለኝም። በመጨረሻም፤ በጎስኝነት ስርዓት የተጎዱ ትግሬዎች የአጫወቱኝን ላካፍላችሁ፤ “አገራች ከረን
ነበር። ወደ ጅጅጋ ሄደን የእህል ወፍጮ ተከልን። ወልደን ከበድን። ሱቅም ነበረን። ኑሮአችን ጥሩ ነበር። አሁን ግን አገሩ ተበላሸ።
አማሮች እያሉ አስወጡን። ወፍጮውን በርካሽ 330 ሺህ ብር ሸጠነው አዲስ አባ ገባን።” እኝህ እናት ዛሬ በሕይወት የሉም። የሚገርመው ግን የእርሳቸው ልጅ ሰለባም
ሆና፤ መለስ ዜናዊን “አቤት ጭንቅላቱ” በማለት ከሚያደንቁት ሰዎች ናት። ጎሰኝነት ምንድን ነው? የዚህቺን ልጅ ሁናቴ ስናይ፤ ወደ
ከብተነት መለውጥ ሊሆን ይችላል። የእኛ ተራ ነው በሚል፤ከብት እዳንሆን እንጠንቀቅ!
Comments
Post a Comment