በበርበሬ! ከቦጋለ ካሣዬ(አምስተርዳም)
ከቦጋለ ካሣዬ(አምስተርዳም)
የመጀመሪያው የባሌ ጎባ አዝማች ደግለሃን ትምህርት ቤት
ግድግዳውና ወለሉ
በእንጨት ነው
የተሰራው። ታዲያ
የጎባ የእድገት በሕብረት አዝማች ሆኖ
የተላከውን መኮንን፤ መሬት ይቅለላቸውና እነ
ታምራት ያለው
እጁን የፍጥኝ፤ እግሩንም አስረው በርበሬ አጠገቡ በመነስነስ፤
«ለወታደር መንግስት፤ ሕዝብ ላልወከለ!
አልገዛም አለ፤ ሕዝቡ እየታገለ!
አንገዛም! አንገዛም! አንገዛም!!»
እያሉ
በመዘመር የጣውላውን ወለል ሲረግጡት በርበሬው እየቦነነ ሰውየው አይኑ
ውስጥ ይገባል። የሰውየው አይን ተጎልግሎ ሊወጣ ያለ እንደነበር እስከዛሬ ይታየኛል። እኔና
አብሮ አደጌ
አብርሃም ያኔ
ዘጠነኛ ክፍል
ተማሪዎች ስለነበርን አልዘመትንም። ታዲያ ዘማቾች ቅጥር ግብያችን ውስጥ
ለስብሰባ መጥተው ነው፤ ወታደር አዝማቻቸውን በበርበሬ ሲለበልቡት የምንታዘበው። መዝሙሩን ግን ወደነዋል። አሁን ዝም ብዬ
ሳስበው አድራጎታቸው ሰላማዊ ባይሆንም፤ የወታደራዊውን አገዛዝ እንዴት ይጠየፉ እንደነበርና ለራሳቸው ደሕንነት ምንም የማይፈሩ ወኔ
ያላቸው ትኩስ
ወተት የጠገቡ አንበሶች ሆነው ይታዩኛል።
ታምራት ያለው ሲዘምት የ11ኛ ክፍል
ተማሪ ነበር። ጋሼ ወልደሰማያት የሚባል የሂሳብ አስተማሪ ነበረን። ሰነፍ ስለነበር ብዙውን ግዜ ቀላል ቀላሉን ነገር ነው የሚስተምረን። አንዳንዴ ታምራት መጥቶ
እንዲያስተምረንም ያደርግ ነበር። ታምራት ከጋሽ
ወልደሰማያት አስር
እጥፍ ይበልጣል! ታዲያ
ያልገባንና ጋሼ
ወልደሰማያት የሚያልፈውን ነገር ሁሉ ወደ
ታምራት ይዘን
መሮጥ ጀመርንና ወልደሰማያትን ናቅነው። አንዴ
ደግሞ እኛ
ቤት ተጋብዞ ምሳ በልቶአል። በሁዋላ ለወላጆቻችን ወልደሰማያት ጥሩ
አስተማሪ እንዳልሆነ ተሳበቅን። ለዳርክተሩ ለመናገር ስለፈራን ነው። ወዲያው መሃመድ የሚባል ራሰ
ሉጫ ጥይት
የድሬዳዋ ልጅ
መጣና ሂሳብ
በደንብ ልንማር ቻልን።
ታምራት የኢሕአፓን ሰራዊት ተቀላቅሎ ሲዋጋ ነው በደርግ የተገደለው። ዛሬ እርሱ
ያስተማራቸውም ሆነ
የርሱ እኩዮች የደረሱበትን ሳይ የታምራት በዚያ እድሜው መቀጨት እንደ እሳት ይለበልበኛል። በተለይ አባቱን ጋሽ
ያለውን ሳስብ ልቤ
ይደማል። እኛን
ሲያይ ምን
ይሰማዋል? ግን
በሥላሴ የጠና
እምነት ያለው
በመሆኑ ነው
መሰለኝ የዛሬ
ሁለት አመት
ሳገኘው ደህና
ነው። ጉዳቱ
ደግሞ በታምራት ብቻ አይደለም። የመጨረሻውን ልጁን ደርግ ኤርትራ አዝምቶት እስካሁን ይኑር
ይሙት አያውቅም። ስንት ስቃይ አለ
በየቤቱ? መቼ
ነው ጦቢያ
ከጦርነት የምትላቀቀው? እነሆ
አርባ አመታት ጦርነት!! ዛሬም የጦርነት ጉም! ጉም! ጉምግምታ!!
Comments
Post a Comment