ግንባር? ውህደት? እየተስተዋለ!
ግንባር? ውህደት? እየተስተዋለ! ‘ነጻነቴን ከኢሳያስ መንጋጋ አገኘዋለሁ ማለትህን ተወኝ!’ ቦጋለ ካሣዬ (አምስተርዳም ኦገስት) በኢሳያስ አፈወርቂ ‘እየተደገፉ’፤ ወያኔን ከስልጣን ለማስወገድ የትጥቅ ትግል እናካሄዳለን የሚሉ ሶስት ድርጅቶች አንድ ግንባር ለመፍጠርና ወደፊትም ለመዋሃድ መስማማታቸውን በቅርቡ የግንቦት-7ቱ ኢሳት በሰበር ዜናው ነግሮናል። የዲያስጶራውም ሰሞነኛ መነጋገሪያ ነጥብ ሁኖአል። ከዜናው ትንሽ ቀደም ብሎ የኢሳቱ ዋና ሰው ፋሲል የኔአለም፤ የወያኔ መውደቂያው ዶርሶአል ሲል ተቁነጥንጦ በፊስቡኩ ላይ የለጠፈው የመልካም ምኞት ብስራት፤ ፍጥምጥሙ ያለቀ ጉዳይ መሆኑን ያመላክታል። ዜናው ወያኔ በማንኛቸውም መንገድ ተወግዶ ለማየት ለሚሹ ገራገር ኢትዮጵያውያን ክፋት ያለው አይደለም። ሌላም ሰው ቢሆን ጭቆና ባለበት የትጥቅ ትግልን ማስቆም እንደማይቻል ስለሚገነዘብ፤ ተዋጊዎቹ ግንባር መፍጠራቸውን ክፉ ነገር ነው! ብሎ ቢያንባርቅ የፖለቲካ ሀሁ ያልገባው ቂላቂል ተብሎ ሊቆጠር እንደሚችል አይስተውም። ለነገሩ ጠላት አይናቅምና፤ ግንባሩን እንደ ክፉ ነገር ሊያይ የሚገባው ወያኔ ይሆን እንዴ? ‘ናይ ፖለቲካ ናጽነት አይኮነን ሆድ ናጽነት !’ በቅርቡ ወያኔ መጪውን ምርጫ ተከትሎ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን ...