ትንሹ እስክንድር ነጋ!
ትንሹ እስክንድር ነጋ፤ ጋዜጠኛና አርበኛ ጌጥዬ ያለው ባለፈው ስለ አንዳንድ አሞላቃቂ ጥቅመኞች የኢሳት ፍርስራሽ ሚዲያዎች የከሰረ የጋዜጠኝነት ስነምግባር ይዘቶች በደምሳሳው አይተናል። ዛሬ አንድ ሌላ ማንሳት በሚገባን፤የኢትዮ-360ው፤ አይጠገቤ ጋዜጠኛና አርበኛ ጌጥዬ ያለው እንጀምር። ጌጥዬ በሞራል ከፍታው ትንሹ እስክንድር ነጋ ሊባል የሚገባው ነው።ከትግል ሜዳ ሆኖ ከየፋኖ ውሎ ፕሮግራሙ በተጨማሪ፤ የሚሰጣቸው ትንታኔዎች ሰፊና ጥልቅ ንባቡን የሚያንፀባርቁ ናቸው። የማያውቀውንም አላውቅም ነው የሚለው። ትሁትና የሰላ አእምሮ ነው ያለው። ሲወድም ሲተችም አያዳላም። እውነተኛ ሰው ነው። የጌጥዬ የድምፅ ፍሰትና ቃና አድማጭን ከመቀመጫው እንዳይነቃነቅ የሚያደርጉ ማግኔቶች ናቸው።ሌሎች ከጊጥዬ መማር አለባቸው።በሚዲያ ላይ ቀርቦ መቆጣትና መደንፋት የአድማጭን የማድመጥ አትኮሮት ይቀንሳሉና።በዚህም መሰረት ኢትዮ-360 ለእውነት በቆሙ የአማራ ይሁን የኢትዮጵያ ልጆች የተካተቱበት ስለሆነ በገንዘብም በሃስብም ሊደገፍ የሚገባው ተቁዋም ነው። ከኢሳት ፍርስራሾች ውጭ ብዙ ሚድያዎች አሉ።የጣና ቲቪ እስካሁን ለፋኖ ትግል እየሰጠ ያለው አበርክቶ ግሩም ነው። ከኢትዮ-360 ጋር ስራቸውን በቅንጅት ሊሰሩ ቢችሉ ጥሩ ይመስለኛል፤ ችግር ከሌለ።አብረው ለፍኖ መሪዎች ጥሪ በማድረግ የአመራር ብቃታቸውን ህዝብ የሚመዝንበትን መድረክ ማመቻቸት ይችላሉ። ጥሪ አድርገው እምቢ የሚሉትን ለህዝብ ማሳወቅ ይገባቸዋል። ይኼን ማድረግ ጥቅሙ ብዙ ነው። እንደው በጥቂቱ፤ መጀመሪያ የፋኖ ግለሰብ ታጋይ እውነተኛ መሪዎቹን በትክክል እንዲያውቅ ያ...