እስክንድር ነጋና አማራ
እስክንድር ነጋና አማራ አንድ ለመንገድ /3/ … ባለፈው አንድ ለመንገድ/2ኛ/ ዳሰሳ፤ \እስክንድረ ነጋና አማራ/ ከእስክንድር ስራ የተወሰደ መሆኑን ገልጫለሁ። አሁን ወደ መጨረሻው ሶስተኛው ክፍል ደርሰናል። ዳሰሳውን ዘርዘር አድርጌ ያቀረብኩትም እስክንድር እንዴት ስለአማራ ህዝብ እንደሚጨነቅ የጻፈውን ስራ ለማስተዋወቅ ነው። ያነሳሳኝ ጉዳይም ባለፈው ወር በህብር ሬዴዮ አንድ የፋኖ ‘ቃለ አቀባይ ነኝ’ ባይ መስሪ ወይም ደንቆሮ ስለ እስክንድር የተናገረውን ፍሬፈርስኪ ካዳመጥኩ በሁዋላ ይኼ የእስክንድርና የፕሮፌሰር መስፍን ሙግት ‘ለቃለ አቀባዩም’ ለተቀረው አንባቢ ግንዛቤ ይሰጣል በማለት ነው። አንድ ለመንገድ /3/ እስክንድር ነጋና አማራ እስክንድር በኮሚኒስቶች መስፍርትም ቢኬድ አማራ ጎሳ/ብሄር/ማህበረሰብ ለመባል፤ከአምስቱ መስፍርቶች፤ የጋራ ቁዋንቁዋ፣ስነልቦና ታሪክና መሬትን ያሙዋላል ይላል። የማያሙዋለው የጋራ ኢኮኖሚ ነው። በኢንዱስትሪ የዳበረ ኢኮኖሚ እንኩዋን አማራ ኢትዮጵያም ስለሌላት፤ ነገድ ለመባል የኢኮኖሚውን መስፍርት ማሙዋላት አይጠበቅበትም።ኮሚንስቶችም ሁሉም መስፍርቶች መሙዋላት አለባቸው አይሉም። ይሁን እንጂ ከመስፍርቶቹ መቅረት የሌለበት የጋራ ስነልቦና ነውና በዚህ ረገድም የአማራ ነገዳዊ ማንነት አሌ የሚባል አይደለም። እስክንድር ገሪማ ታፈረ( የታዋቂዊው ፊልም ሰሪ ኃይሌ ገሪማ አባት) ስለ አማራ 25 ዓመታት ሙሉ ያጠኑትን አለቃ ታዬ የሚባሉትን ሊቅ በመጥቀስ እ.ኢ.አ 1973 የጻፉትንም ያጋራናል። ገሪማ አለቃ ታዬ አማራ የሚባለው ህዝብ ትውልዱ ከሴም ልጅ ከኤቦር ነገደ ዮቅጣን መሆኑን አረጋግጠዋል ይላሉ።ጥናታቸውም የተመረኮዘው፤ በአለም ታሪክ ተመራማሪዎች ስራ(ኢዘንበር፣መልዚ፣ፓስቴንና ቫንሲን)፣ከመልኩ(...