Posts

Showing posts from February, 2021

መሪያችንን እንደ ዐይናችን ብሌን!

  ጉድ ሳይሰማ፤ መስከረም አይጠባም ነው ነገሩ። ለአብይ አህመድ የሚደረገው ሰልፍ በየክልሉ እየደራ ነው። ማን ከማን ክልል ያንሳል? በሁዋላ ለምን ይኼ ክልል ለእኔ ድጋፍ አለወጣም? የሚል ተጠያቂነት ስለሚያመጣ፤ ወደድክም ጠላህም፤ “መሪያችንን እንደ ዐይናችን ብሌን!” እንጠብቃለን እያልክ ግንባርህን በአደባባይ ማሳመታት አለብህ። እንደ ዐይናችን ብሌን የሚለው የደንቆሮና የሆዳም ካድሬ ቅጥፈት ነው።   ሰው እኮ ራሱም አሻግሮ ማየት ሲችል ነው የሌላውን የዐይን ብሌን ሊጠብቅ የሚችለው። የፕሮፌሰር መስፍን ምርር ያለች እንጉርጉሮ ዛሬም የምንገኝበትን ስርዓት እንደ መስታወት ስለምታሳይ፤ ቀንጨብ ላርጋት፤ “ስብሃት ለጨለማ”! “ስብሃት ለጨለማ”! ለብርሃን ዋዜማ! ጨለማ! የስርቆሽ ውድማ ! የግብዝ ከተማ! ጨለማ! የክፋት፤ የተንኮል፤ የጭቃኔ አለኝታ! የወንጀል ነፃነት! የኃጢአት ደስታ! ይጠየቅ ሰው ሁሉ፤ እውነቱን ይናገር፤ የሚናገር ቢኖር፤ ብርሃን ነው ጨለማ ሰውን የሚያሳፍር? ጨለማን ይጠላል ሰው ጨዋ ለመባል፤ ብርሃን ሲያሸማቅቅ አያውቀው ይመስል! ጨልም ! ጨልም ! ድፍን ብለህ ጨልም! ዓይኖቻችን ይጥፉ አያዩም አይጠቅሙም!” * መቼ እንደጻፈው አልተገለጠም። እንጉርጉሮ የሚለው ስራው የታተመው እ.ኢ.አ በ1967 ዓ.ም ነው።   ስርቆት፣ግብዝነት፣ክፍት፣ተንኮል፣ጭቃኔና የወንጀል ነጻነት የአብይ አህመድ አገዛዝ መገለጫዎች ለመሆናቸው ህልቆ መሳፍርት መረጃዎች አሉ። ግብዝነት አብይ አህመድ በወታደራዊ ወኔው፤ ኢትዮጵያ ከሰላሳ አመታት በሁዋላ ከሁለቱ አንድዋ የአለም ኃይላን አገር ትሆናለች ያለ ግብዝ ነው። እንደዚህ አይነት ድፍረት የሚመጣው የአለምን የኢኮኖሚና የፖለቲካ አደረጃጀት በትንሹ እንኩ...

የምርጫው ነገር፤ ደግሞ መጣ!

  የምርጫው ነገር ... ደግሞ መጣ ! === “ እኔ የምለው … ወያኔ በምርጫ ቢሸነፍ ስልጣን በሰላም ያስረክባል እንዴ ” ? ባያስረክብስ ምን መደረግ እንዳለበት ዝግጅት አለ እንዴ ? እኚህ ጠያቂ ዛሬ ስማቸው ብዙም አይጠራም። የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ፕሬዝዳንት የነበሩት ዶ / ታዬ ወልደሰማያት ናቸው። === ከምርጫው በፊት ለጥያቄዎቻቸው መልስ የሰጣቸው ሰው አልነበረም። በመጨረሻም የጠበቁት ሆነ። ወያኔ በቅንጅት ተሸነፈ። ግን ሽንፈቱን አልተቀበለም። የለመደውንም ደም አፈሰሰ። የተቃዋሚዎቹም አንድ ወጥ ያልሆነ አመራር ተደምሮ ዴሞክራሲ ጨነገፈ። ጭቡ ውሎ ይደር እንጂ ይደርሳል ትል ነበር አክስቴ። አይ ! አይ ! ናይ ! ወያኔ ! ዛሬ የራስሽ ደም ጢሻ ለጢሻ፤ ገደል ለገደል እየጎረፈ ነው። እብሪአትና ዘረኝነት መጨረሻቸው ውድቀት ነው። የአብይ አህመድ አሊ ምርጫ === ታዲያ … የአብይ አህመድ ብልፅግና ምርጫውን በግድም በውድም ካላሸነፈ ስልጣን ይለቃል ወይ ? ካለሸነፈና እንደ ወያኔ አሻፈረኝ የሚል ከሆነ ምንድን ነው የሚደረገው ? ቀድሞ ዝግጅት ለማድረግ ታስቦአል ወይ በተቃዋሚዎቹ ? ብልፅግና በኦሮምያ፤ 1. ብልጽግና የድሮ ኢሕአዴግ ሲቀነስ እየተደመሰሰ ያለው ወያኔ ነው። ልብ በል የወያኔ አባል የነበሩና ቀደም ሲል ወያኔን ለቀው ወደ ብልጽግና የተቀላቀሉ አሉ። አሁንም በትግራይ ብልጽግና ውስጥ ተደራጅተዋል። ለምሳሌ የትግራይ ተሹዋሚ ዶ / ር ሙሉ ወያኔ የነበረ ነው። እነዚህ አሁንም የጎንደርና የወ...