ወርቅ-ቅብ፣መርዘኛ ብእር። እኛም አውቀናል፤ ጉድጉዋድ ምሰናል!
ወርቅ-ቅብ፣መርዘኛ ብእር። እኛም አውቀናል፤ ጉድጉዋድ ምሰናል! ከቦጋለ ካሳዬ፤ ማርች 2014 አምስተርዳም የአፈንዲ ሙተኪ ጮሌነት ፀሃይ ሞቆታል። በዚህም ምክንያት ተጨንቆ በትክክል ማሰብ እንደተሳነው ከመጣጥፎቹ መረዳት አዳጋች አይደለም። አፈንዲ የከሸፈውን የተስፋዬ ገ/አብን ተልእኮ፤ ከውስጣችን ተቀላቅሎ ረቀቅ ባለ መንገድ እያካሄደ የሚገኝ ለምድ የለበሰ የቀበሮ ባሕታዊ ነው። ብዙ ክሶችን ደረደርኩ አይደል? ምክንያቶቹን እንያቸዋ አብረን። 1.በኦነግነት ተከሰስኩ ብሎ በሰጠው ምላሽ ላይ፤ ኦነግን ይደግፍ እንደነበርና፤ አሁን ግን በኦነግ የመገንጠል አቁዋም ላይ ስለማይስማማ እንደማይደግፈው ነግሮናል። ሃቀኝነት ያለው ምላሽ አይደለም። 1.1 በዚሁ ምላሹ፤ በቂ ዋቢ ሳይጠቅስ ‘ኦነግ አደረጋቸው’ ተብሎ ሲጻፍና ሲነገር የነበረውን ወንጅሎች፤ በአንድ ቦታ ከተፈጸመው ወንጀል በስተቀር ውድቅ አድርጎለታል። እውነት ሊሆን ይችላል። ይሁን እንጂ ከእርሱ ገና ድሮ ቀድሞ ኦነግ ከሽግግሩ መንግስት ከመውጣቱ በፊት እርሱ በሚያስተዳድርበት አካባቢ ስለተፈጸመው ወንጀል ሃላፊነቱን እንደሚወስድ ራሱ ስለነገረን፤ የአፈንዲ ማብራሪያ መረጃ ላልነበራቸው ሰዎች ይጠቅም ካልሆነ በስተቀር፤ ለብዙዎቻችን ተደጋጋሚ ነገር በመሆኑ ምንም ተጨማሪ ፋይዳ አላየንበትም። በነገራችን ላይ እኛ እራሳችንን “እኛ” የምንለው፤ እኔ የሚለው ተውላጠስም ስለ ራስ የገነነ እድምታ እንዳይፈጥር በመስጋት ነው። እኛ የምንጽፋውም ሃሳብ ቀደም ሲል ሌሎች ያጤኑት ወደፊትም ሊሎች ሊያጤኑት እንደማይቀሩ ከግንዛቤ በማስገባትም ነው። ቀዳማዊ ኃይሥላሴ ግን “እኛ”ይሉ የነበረው፤ የዘውዱ፣የሃይማኖትና የሕዝቡ ተቀቢ፣ተወካይና ገዢ መሆናቸውን ለማንጸባርቅ እንጂ፤ አፈንዲ እንዳለው የሐረር ሰው ስ...