Posts

Showing posts from December, 2025

ግምገማ? ወይስ?

   ግምገማ? ወይስ? የፋኖ አንድነት ብስራት እየተጠበቀ ባለበት ወቅት፤ የቀድሞው የባልደራስ የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ አቶ ስንታየሁ ቸኮል በፅናት ሚዲያቸው ላይ ስለ አርበኛ እስክንድር ነጋና በፋኖ ትግል ላይ ሃሳቦችንና ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ ግምገማዎችን  እያስደመጡን ነው። 1. አቶ ስንታየሁ ትግሉ በአማራ ጠላቶች በተለይ በብአዴን እንዳይጠለፍ፤ የፋኖ የመሪዎች ምርጫ የአፋሕድና የአፋብሃ ብቻ መሆን አለበት እንጂ ማንም ከድርጅቶቹ ውጭ ሆኖ እከሌ ካልወጣ! እከሌ ካልገባ! አንድነት አይመጣም የሚለውን የጠላት መሰሪነት በምሬት አውግዘዋል። ይኼን ብአዴናዊ አካሄድ እንፋለመዋለን ሲሉ ተደምጠዋል። በጣም ነው የምስማማው። 2. ሆኖም አቶ ስንታየሁ በአንድ በኩል የመሪዎችን ምርጫ ለድርጅቶቹ ይተው ቢሉም እርሳቸውን ግን የሚመለክት ነገር አይመስልም። በአርበኛ እስከንድር ነጋና በእርሳቸው መካከል ያለውን ቅያሜ ሳይደብቁ፤ እስክንድር ወደ ትጥቅ ትግል ቆርጦ ሲገባም ሆነ ቀደም ብሎ ከባልደራስ መልቀቂያ ሲያስገባ  ውሳኔዎቹ እርሳቸውን እንደሚጎዱ ባለማሰቡም ሆነ ቀጥሎም ከሜዳ እርሳቸውን ለማግኘት በቂ ጥረት ባለማድረጉ(በሻለቃ ዳዊት በኩል መልእክት ቢደርሳቸውም) በእስክንድር ላይ ከማዘን አልፈው በመካድ ስሜት ላይ መሆናቸው ይታያል። በእንደዚህ ያለ ነገር ላይ መልስ ሊሰጥበት የሚችል እስክንድር ብቻ ነው።አንድ ነገር ግን እዚህ ላይ ድቅን ይላል። እስክንድር እኮ የትጥቅ ትግል የጀመረው ነፍሱን ለአገሩ ቤዛ ለመድረግም ነው። ለራሱም ነፍስ የማይሳሳና በቤተሰቡ ላይም የቆረጠ ሰው ነው። 3. አቶ ስንታየሁ ቀጥለው ደግሞ እስክንድር ስለመሰረተው የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ግንባርና ቀደም ሲል በእነ ዘመኔ ካሴ ስለተመሰረተው...