Posts

Showing posts from January, 2025

የፋኖ አንድነት እንዴት?

ቦጋለ ካሣዬ/2025 የዚህ መጣጥፍ ዋና አላማ የፋኖ አንድነት ሕዝባዊነቱን ጠብቆ እንዲረጋገጥ ቅንና ግልጽ ውይይት መቆስቆስ ነው።በጎደለ መረጃ ሊዳብር ይገባል። መነሻችን/መድረሻችን እንደሚታወቀው የአማራ ፋኖ፤ለምሳሌ በትግሉ መነሻና መዳረሻ ጉንጭ አልፋ ሰበቦች ወደ አንድ የፋኖ አደረጃጀት ሊመጣ አልቻለም። መነሻችንም አማራ መዳረሻችንም አማራ የሚሉት፤ አብይን ከስልጣን አውርደን ብቻችንን ወይም ሊፎካከሩን ከሚችሉ ነገዶች ጋር ስልጣን ተጋርተን፤ የወያኔን ህገ መንግስት ትንሽ አሻሽለንም ይሁን እንዳለ ተቀብለን ኢትዮጵያን እናስተዳድራለን ማለት ነው። መነሻችን አማራ መዳረሻችን ኢትዮጵያ ደግሞ ወያኔ የተከተለውን የጎሳ ስርአት ነቅለን በኢትዮጵያዊ ዜግነት ላይ የተመሰረተ አዲስ ስርአት ተክለን ኢትዮጵያን እንታደጋለን ነው። እንደ የሸዋ ፋኖ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ዶ/ር አብደላ እድሪስ ከሆነ ግን፤በዘመነ ካሴ የሚመራው የጎጃም አማራ ፋኖ ፣በሻለቃ ምሬ ወዳጆ የሚመራው የወሎ ፋኖና በሻለቃ ባዬና በሻለቃ ሃብቴ የሚመራው የጎንደር አንድነት የወያኔው መለስ ዜናዊ ፈለግ ተከትለው፤ መነሻችንም አማራ/መዳረሻችን አማራ ነው መንገዳቸው።ጄኔራል ተፈራ ፋኖን ከተቀላቀለ በሁዋላ ከሜዳ የሰጠው አስተያየት የአስራትን ፈለግ የተከተለ ቢሆንም እርሱ የተቀላቀለው የሸዋ ፋኖ አቁዋም ግን የወያኔን ህገመንግስት አጥብቆ የሚደግፍ ነው። ጀኔራሉ ከልብ የአስራትን ፈለግ ተከታይ ከሆነ ለምን ወደ መከታው አልሄደም? በፋኖ እስክንድር ነጋ የሚመራው የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት(አፋሕድ) ስር የተደራጁት እዞች ደግሞ፤ መነሻችን አማራ መዳረሻችን ኢትዮጵያን ነው የሚያራምዱት።የልዩነታቸውን ሰበብ እስኪ በወፍበረር ከአደረጃጀታቸው ተነስተን እንቃኝ። የፋኖ አደረጃጀት የወያኔን...