ተፈሪው ፋኖ እስክንድር ነጋ!
ተፈሪው ፋኖ እስክንድር ነጋ! ቀ ዳማዊ ማንነታችን አማራ ነው፡፡ የአካባቢ ማንነቶች(ጎጥ) ከቅርብ ታሪካችን የተከሰቱ ናቸው፡፡ ጥንታዊ የአማራነቱን ማንነት ሳያውቅ በአካባቢ ማንነት መኩራራት አጉል መኮፈስና ታሪክን አለማወቅ ነው ሲል እስክንድር ድል ለዲሞክራሲ በሚለው መድብሉ ገና ዱሮ የትጥቅ ትግል ከመጀመሩ በፊት በዝርዝር ጽፎኣል። እስክንድር-ጠሎች ግን እርሱ ድል ለዲሞክራሲ ነው እንጂ ድል ለአማራ አይልም ሲሉ ይከሱታል። በእርግጠኝነት ለመናገር ወይ መጽሃፉን ተንተርሰውታል፣ አላገኙትም ወይም ሃቁን ቢያውቁትም ወደ ስም ማጥፋት ላለመሄድ ህሊናቸው አልቆረቆራቸውም። እ ስክንድር አማራው መንግስት፟፟ - መር የዘር ፍጅት እየተካሄደበት ለከፍተኛ የህልውና አደጋ በመጋለጡና አደጋውም በሰላማዊ ትግል ማስቆም ስላልተቻለ የፋኖን የትጥቅ ትግል ከጎዋዶቹ ጋር ማስተባበር ጀመረ። ወጣት የነብር ጣቶቹ በተለይ እኔ የማውቃቸው ጌጥዮና ወንድይራድ በአሳፋሪ ሁኔታ ዘመኔ ካሴ(የአማራው አብይ አህመድ) አግቶታል። እንዲሁም ሌሎቹ ስማቸውም የማላቀው ብዙዎች አይኔ ላይ ይመጣሉ። በወጣጥነት እድሜያቸው የሚያደርጉት አስተዋጽኦ ትውልድ የሚኮራበት ነው። እስክንድር ገና ወደ ትጥቅ ትግሉ ከመግባቱ በፊት የባልደራስ መሪ እያለ ከታዋቂ የፋኖ መሪዎች ጋር ተገናኝቱዋል። መክሮአል። አንዴ እንደውም በአዲስ አበባ ዘላለም ከሚባል የአገዛዙ ደጋፊ ጋዜጠኛ ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ፤ የወለጋን ጭፍጨፋ የአካባቢው ልዪ ሃይል ማስቆም ስላ...