ውድ ዋጋ!
ውድ ዋጋ! ፋኖ የአማራን ህልውና ለማስከበር ነፍጥ አንስቶ መዋጋት ከጀመረ አንድ አመት ሊሞላው ነው። ጥሪቱን በመሸጥና ከብልጽግና ወታደሮች በማረከው ትጥቅ ወታደራዊ መዋቅሩን አደራጅቶ፣ በአማራ ህዝብ ስንቅ ተደግፎ በአጭር ጊዜ እዞችን በመመስረት ለኢትዮጵያም ሆነ ለአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋት እውን መሆን ፤ተአማኒና ተስፋ ሰጪ ኃይል ሊሆን ችሎአል። ወታደራዊ ኃይል በአሁን ወቅት ፋኖ በሸዋ ሁለት፣በጎጃም በጎንደርና በወሎ አንዳንድ እዞች አሉት። ትናንት ደግሞ በመቶ አለቃ ማስረሻ የሚመራ የአማራ ፋኖ ህዝባዊ የጎጃም እዝ ተመስርቶአል፡፡ ሌሎችም ሊፈጠሩ ይችላሉ፡፡ እነዚህን በአንድ ኮማንድ ለማምጣት ስራ እየተሰራ እንደሆነ ከፍኖዎቹ በተደጋጋሚ ሰምተናል። አንዳንድ የወታደራዊ ሙያ ያላቸው ሰዎች ደግሞ ይኼ ሂደት ቶሎ የማይቁዋጭ ከሆነ አንድ ላይ ለመስራት የሚችሉ እዞች በአንድ ኮማንድ ይሰባሰቡና፤ ለጊዜውም ቢሆን ደግሞ ካልቻሉት ጋር በመናበብ አብሮ እየሰሩ ወታደራዊ ድሉን ወደ መቁዋጨቱ ቢኬድ ይሻላል ሲሉ፤ ሌሎች ደግሞ አስቀድሞ ሰራዊቱ በእዝ ደረጃ በመዋቀሩ በቂ አቅም መፍጠሩን ስለሚያሳይ በአንድ አማራ ኮማንድ ስርም ባይኮን፤ እየተናበቡ መዋጋት እንደሚቻል ያሳስባሉ። እዞቹ የተዋጊ ሳይሆን የተለያዩ የሎጂስቲክ ችግሮች እንዳሉባቸው እሙን በመሆኑ እስከ ድል ድረሰ ያልተቁዋረጠ ድጋፍ በተቀናጀ መልክ ያ...