Posts

Showing posts from 2023

WHAT A LIFE!

  What a life! [1] ሻለቃ ዳዊት ወልደ ጊዮርጊስ የጻፉት ዳጎስ ያለ የህይወት ታሪካቸው ነው፡፡ በብዙ ዋቢዎች የታጨቀ ስራ ነው፡፡ በአማርኛ ይተረጎማል የሚል ተስፋ አለኝ፡፡ እንግሊዘኛ የምትችሉ ገዝታችሁ ብታነቡት ትጠቀማላችሁ እንጂ አትከስሩም፡፡ አንዳንድ ጉዳዮችን በወፍ በረር እነሆ፤ 1/አባታቸው ወልደ ጊዮርጊስ ዮሃንስ የቤተክህነት ትምህርትን በትጋትና በጥልቀት ስለተማሩ ለትርጉም ስራ ያግዛሉ ተብሎ ተመረጡና ከቤተመንግስት ጋር ትሥራቸው ቀና ሆነ። የመጀመሪያው የአዲስ ዘመን ጋዜጣ አዘጋጅ ለመሆንም በቁ። መጻህፍትም ጽፈዋል። አንዱ ልጃቸውም የኢትዮጵያ ሄራልድ አዘጋጅ ለመሆን በቅቱዋል። የዳዊት እናት ዋካ የቤት እመቤት ናቸው። እውቁ ዲፕሎማት ብርሃኑ ድንቄ አጎታቸው ናቸው። ዳዊት ለጣሊያን ያደሩት የባንዳ ወልደ ጊዮርጊስ ዮሃንስ ልጅ ነው የሚለው ሃሰት መሆኑንና፤ ጉዳዩ በሰመ ሞክሼ የመጣ እንደሆነ አብራርተዋል። በበአሉ ግርማ፤ ኦሮማይ ድርሰትም እርሳቸውን የሚገልጠው ገፀባህሪ የተለየ እንደሆነና ፍያሜታም ከእርሳቸው ሁለት  ፀሃፊዎች አንዱዋ እንደነበረች፤ በአሉም የራሱን የአዲስ አበባዋን ፀሃፊ ከሚያመጣ ይልቅ ፍያሜታን ራሳቸው እንደመደቡለት ያስረዳሉ። በዘፈቀደ ወደ እርሳቸው የተላከከው የፍቅር ተረክ ካለማወቅ እንደሆነ አብራርተዋል። ዳዊት አብርሃም ያየህና ገ/መድህን አርአያ ለደርግ እጃቸውን በሰጡበት ወቅት፤ በስፋት የተሰራጨው “ታላቁ ሴራ ” የእርሳቸው ጽሁፍ መሆኑን ኢፋ አድርገዋል፡፡ 2/ለምለም ምህንድስና ነበር ለማጥናት ያሰቡት። ካለፍላጎታቸው ወደ ሐረር ጦር አካዳሚ ለስልጠና ከገቡ በሁዋላ ነው ወላጆቻቸው ያወጡላቸውን ስም፤ ራሳቸው ወደ ዳዊት የለወጡት። ምክንያታቸውም፤ እንግዲህ ወታደር ከሆኑኩ አይቀር ፤ ዳዊት...