አራት ኪሎ ያለው ሰውዬ፤ ለዘላቂ ሰላም ይሰራል?
ዛሬም ጦርነት ውስጥ ገባን። ከዚህ ጦርነት በፊት ከኤርትራ ጋር ተዋግተን ነበር። እኔ የዚያኔ ጦርነቱን የደገፍኩት ሻእቢያ አክርካሪው ይመታል፤ አስብንም በእጃችን እናስገባለን ብዬ ነበር። ይሁን እንጂ አራት ኪሎ የተቀመጠው ሰውዬ አጭበርባሪ ስለነበረ፤ 70 ሺህ ዜጎች ገብረን ጦርነቱን ብናሸንፍም በመጨረሻ ሙልጭ ወጣን። አሁንስ አራት ኪሎ ያለው ሰው የሚታመን ነው ወይ? በተለይ በአማራው ጉዳይ? እስኪ ዞር ብለን እናስብ፡፡ 1. አብይ ጠቅላይ ሚኒስትር እንደሆነ ትግራይን ጎብኝቶ ነበር። ታዲይ በአደባባይ ንግግሩ ወልቃይትን አንስቶ፤ የወልቃይት ጉዳይ የልማት እንጂ የማንነት እንዳልሆነ ነገረን። ብዙም አልተደነኩም። ምክንያቱም ገና ያልጠና ወንበሩን በማደላደል ላይ ስለነበር፤ በዚያን ወቅት የወልቃይትን ጥያቄ መግፍቱ ለስልጣኑ አደጋ ሊሆን ይችላል በሚል አመክንዮ ነበር፡፡ 2. ከትግራይ መልስ ደግሞ አማቾቼ ለሚለው የጎንደር ሕዝብ ባደረገው ንግግር ላይ...”የቅማንት ጥያቄ” የሚባለውን ክብደት ሰጥቶ ማንሳቱን ላስተዋለ ሰው አብይ ለአማራው አንድነት በጎ ሰው እንዳልሆነ ፍንጭ የሰጠበት አጋጣሚ ነበር፡፡ ይኼን የወያኔ እኩይ ከፋፋይ ሴራ እንደ ቅማንት መብት ቆጥሮ በአደባባይ መሞገቱ፤ አማራውን ለማዳከም የሚደረጉትን ስልቶች የሚጋራ ለመሆኑ አስረጂ ነውና፡፡ 3. በአዲስ አበባ በተለይ አማራው በልማት ስም በግፍ ሲፈናቀል፤ 'የእኔ ስራ ከንቲባነት አይደለም፤ አልሰማሁም' ብሎ ያላገጠና የዋሸ እለትም፤ ሌላው አማራ ጠልነቱን ያስረገጠበት ሃቅ ነበር። 4. አብይ ስልጣን ከያዘ ጀምሮ በየቦታው የሚጨፈጨፈውን የአማራ ጥቃት ከግጭት በላይ ለማየት ያለመፈለጉም፤ ሌላው ለሰው ልጅ ሕይወት ይሁን ለአማራ ያለውን ደንታቢስነት የሚያሳይ ነው። 5. የሰኔ 15ቱ ግድያ ይሁን ቀደም ...