Posts

Showing posts from December, 2018

አገር ቤት ደርሶ መልስ....

ባህርዳር...  እንደ ደረስን ወደ ሆቴላችን በባጃጅ ለመሄድ ሃሳቡ ነበረን።  ሻንጣችንን ከመኪናው ላይ ያወረደው ልጅ ግን፤ ..."ጋሼ እኛ ባጃጅ የሌለን ምን ስርተን እንብላ? ሆቴላችሁ እዚህ ቅርብ ነው። ኑ ተከተሉኝ"!.... እንዳለውም አምስት ደቂቃም ሳንራመድ ደረስን። እውነቱን ነው።  አሳዘነኝ። አንድ ወዳጄ እንዳጋጣሚ ለስራ ጉዳይ እዚያው ባህርዳህ መጥቶ ሆቴል ይዞ ስለነበር... ጣና ባህሩ ዳር ወስዶ ጥሩ ራት ጋበዘን። ይሁን እንጂ ልጄ አይነቱ በዛበት መሰለኝ... አሞት አደረና በሚቀጥለው ቀን ያቀድነው ፕሮግራም ሊካሄድ አልቻለም።  እኔም መጽሃፍ እያነበብኩ ከሆቴሉ ሳልወጣ ዋልኩ። አንድ ዘመድም ስለነበረኝ ረፋዱ ላይ የርሱን ልጆች ላይ ሄድኩኝ። በማግስቱም ጥዋት የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ የባህርዳር ጽ/ቤት ካረፍኩበት ሆቴል ቅርብ ስለነበር ሰተት ብዬ ሄጄ ተዋወኩዋቸው። የፖለቲካ ፕሮግራማቸው ገና አልቆ ስላልተበተነ ላገኘው ባልችልም፤ በመሬት የግል ይዞታና በኢትዮጵያ የወደብ ጥያቄ ላይ ጥሩ የሃሳብ መለዋወጥ አድረግን። ስለ አብንና አዴፓ ግንኙነት በሚመለከት ከነርሱ የተሰጠኝ መልስ ግን ስጋት ውስጥ ጣለኝ። አዴፓ አብንን ለማጥፋት እንደሚሰራና አብን በህዝቡ ድጋፍ ብቻ ህልውናው ሊጠበቅ እንደቻለ አስረዱኝ። አዴፓ ያሰረባቸውን አባሎቻቸውንም ህዝቡ እንዳሰፈታቸው ነገሩኝ። ይኼንኑ ስጋቴን  አዲስ አበባ ተመልሼ እኔ አባል ለሆንኩበት የአማራ ህልውና የኢትዮጵይ አንድነት ድርጅት ሰዎች ነገርኩዋቸው።   የአማራ ህልውና ለኢትዮጵይ አንድነት አመራሮች ከሁለቱንም ከፍተኛ የፖለቲካ ድርጅቶች አመራሮች ጋር ተነጋግረዋል። ድርጅቶች እየተቀራረቡ ሲመጡ ሊፈታ የማይችል ምንም አይነት ጉዳይ እንደማይኖር ነው የሚያስቡትና እን...

አገር ቤት ደርሶ መልስ...

አገር ቤት ደርሶ መልስ... ከስምንት አመታት በሁዋላ ኢትዮጵያ ደርሼ ተመለስኩ ። ብቻዬን አልሄድኩም። ጎረምሳውም ዘንደሮስ ተለይቼህ አልቀርም ስላለ ሁለት ራሴን ሆኜ ነው የሄድኩት። በቶሮንቶ አለም አቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ የኢትዮጵያን አየር መንገድ ዴሪም ላይነር ለመሳፈር... በተሽከርካሪ ወንበር ላይ የተቀመጡ ስድስት አሮጊቶች ተገፍተው ቀደም ብለው ገቡ። አንድም በሚገፋ ተሽከርካሪ ወንበር ላይ የተቀመጡ ሽማግሌ ባለማየቴ ይመስለኛል ...አንድ ትዝብት ትዝ ብሎኝ ብቻዬን ፈገግ አልኩ። እንዲህ ነው ነገሩ። ..."አባቶቻችንና እናቶቻችን ይጨቃጨቃሉ። በተለይ ውሃ ቀጠነ ብለው ነገር የሚያነሱት ብዙውን ጊዜ አባቶቻችን ናቸው። ታዲያ እግዚአብሄርም ይኼን አየና... እነሱን ቀድሞ በመውሰድ እናቶቻችን ቀሪውን እድሜያቸውን እፎይ ብለው እንዲያሳልፉ ያደርጋል ይባላል።" እነሆ በድሪም ላይነር የሰሜን አሜሪካ ክረምት ሲገባ ወደ ኢትዮጵያ...ሲወጣ ደግሞ ወደ አሜሪካ እየበረሩ እፎይ ማለት ነዋ! እናቶች ይመቻችሁ! አባቶችም አደብ ግዙ! በአሊታሊያ፣ በአሜሪካ፣በካናዳ፣በኬኤሌም፣ በሉፍንታዛና በብሬትሺ ኤር ወይስ በተደጋጋሚ በርሬያለሁ። በእነዚህ አየር መንገዶች ውስጥ አንድ የጎላ ፊት ይታያል። አብዛኛው ተሳፋሪ ፈረንጅ ነው። አልጠላውም። ግን ብቸኝነት ይሰማኛል። በኢትዮጵይ አየር መንገድ ስበር ሁለተኛዬ ነው። የተሳፋሪው ፊት.... አፍሪካውያን፣እስያውያና ፈረንጆችንም ስለሚያካትት  አለም አቀፋዊ ነው። በዚህም መሰረት በበረራ ወቅት የባይተዋርነት ስሜት በጭራሽ አይኖርም። በመቀጠልም የደስ ደስና ትህትና ያላቸው እህቶቻችን ለአዋቂ ይሁን ለልጆች ተሳፋሪዎች የሚያሳዩት እንክብካቤ የሚደነቅ ነው። ምንም የመሰልቸት ፊት አያሳዩም። በተጠሩ ቁጥር ከነፈገግታቸው ከች ነ...