Posts

Showing posts from June, 2018

አብይ አህመድ፤ ትን! ብሎት ግጥም ቢልስ?

ሳር ቅጠሉ፤ አብይ! አብይ! ሆኖአል፡፡ አማን! አማን አንዶም! ፤ መንጌ መንጌ! የተባሉበትም ጊዚያት ነበሩ፡፡ መለስ ዜናዊ መሌ ተብሎ አያቅም፡፡ ራሱም ባንዳና አያቱም ባንዳ ስለነበሩ እኛም እንደጠላነው እርሱም እንደጠላን አምላክ ጠራልን፡፡ አዎ...ድፍን ትግሬ ይወደው ነበር። ከዚያም ዱቤ መጣ፡፡ ዱቤ ማለቴ እርሱም ሆነ ሌላ ማንም ሳያስበው ጠቅላይ ሚኒስተር የመሆኑን ድንገተኛነት ለመጠቆም ነው፡፡ ሃይለማርያም በትምህርቱም ሆነ በተመክሮው ከማንም ባያንስም ጥርስ የሌለው አለቃ ሆኖ ወንጀልም ፈጥሞ ተሰናበተ፡፡ አማንን መንግስቱ በላው፡፡ መንግስቱም 17 የስልጣን አመቱን ሰው ሲገድልና በመፈክር ኢምፔሪያሊዝምን ሲደመሥስ፤ ስልጣን ህዝባዊ ይሆን ዘንድ ምንም ስራ ሳይሰራበት አለቀና ለስደት ተዳረገ፡፡ ለነገሩ  ነው እንጂ ከመንግስቱ መቼም ዴሞክራሲ ይጠበቃል ብዮ አይደለም፡፡፡ ወያኔ ስልጣን በያዘ ማግስት የመንግስቱን ሰለባዎች እየሰበሰበ ማስለቀስ ጀምሮ ነበር፡፡ አንድ በጣም በሳል እመቤት ይኽንኑ ታዝባ፤ ለሃይሌ ገሪማ የሰጠቺው አስተያየት እስከዛሬ አይረሳኝም፡፡ ብዙም ሰው ግን የረሳው ይመስላል፡፡ እመቤቲቱ ምን አለች? ቃል በቃል ባይሆንም መልእክቱዋ....የእኛ ነጻ መሆን እኮ የሚለካው ደርግ በመውደቁ አይደለም። የሚለካው ሕዝቡ እውነተኛ የስልጣን ምንጭ ሲሆን ብቻ ነው ነበር ያለቺው። አረገቴ? አብይ! አብይ! አብዬዎች? የፖለቲካ ባህላቸው ያልበሰለ ሰዎች ስሜት ይገዛቸዋል፡፡ ደግ ነው ብለው የሚይስቡት መሪ ላይ እምነታቸውን ይጥላሉ፡፡ አንድ ግለሰብ መሪ ግን እንደ ሸክላ ተሰባሪ መሆኑን ላንዳፍታም ያጤኑት አይስመስልም። እስኪ ዛሬ አብይ ትን ብሎት ቢያልፍ ነገ አገሪቱ ምን ትሆናለች? ሌላ አብይ እንደሆነ አይመጣም፡፡ ኢትዮጵያ እስካሁን ወደሁዋላ የቀረ...