ሕጻናት አምባ
ሕጻናት አምባ.... ኤርሚያስ ተኩማ...ስለ ሕጻናት አምባ የጻፈውን ካነበብኩ በሁዋላ አንዳንድ የማውቃቸውን ነገሮች ለማንሳት ፈለኩ። በርግጥም አምባው የተመሰረተው በሶማሌም ሆነ በኤርትራ ጦርነቶች ሳቢያ አባቶቻቸውን ያጡ ሕጻናትን ለማሳደግ ተብሎ ነበር። ከዚህ ቀደም ብሎም ኮሎኔል መንግስቱ ሃይለማሪያም በጦርነት ለአካለ-ጎዶሎነት የተዳረጉትን ወታደሮች በደብረ-ዘይት... ወደ ሆራ መሄጃ ላይ የጀግኖች አምባ መስርቶ በሚገባ እንክብካቤ እንዲደረግላቸው ያደርግ ነበር። ሁለት እግሮቹና አንድ እጁ የተቆረጠ ጀግና በአይኔ አይቻለሁ። ከዚህ በመለስ የተለያዩ ጉዳተኞች ነበሩ። እንደዚህ አይነት ጉዳተኞቹን ለመንከባከብ ሙሉ ግልጋሎት የሚሰጥ ተቁዋም ያስፈልጋል። ምክንያቱም ቤተሰባቸው በመንግስት ገንዘብ ቢደጎም እንኩዋን ተገቢውን እንክብካቤ ለማድረግ እውቀቱና አቅሙ አይፈቅዱለትምና። የጀግኖች አምባ ዛሬ ባይኖር አይገርመኝም። በወያኔ አይን የጠላት ማገገሚያ ነበርና። የሕጻናት አምባን ጉዳይ ግን ዘለግ አድርጎ ማየት ሳይጠቅም አይቀርም። በአቡነ ጎርጎርዮስ ምክር ቤተክርስቲያንና መስጊድ ተሰርተው መንፈሳዊ ግልጋሎት መስጠት መጀመራቸውን ከኤርሚያስ ጽሁፍ ነው ላውቅ የቻልኩት። እኔ አምባው ውስጥ ሰራተኛ በነበርኩበት ወቅት ይኽ ግልጋሎት አልነበረም። በመጀመሪያ ደረጃ ልጆቹ ሁሉ አባት የላቸውም ማለት አስቸጋሪ ቢሆንም .... አብዛኞቹ እናት ነበሩዋቸው። አባታቸው የሞቱባቸው ልጆች የተሰበሰቡትም በኮታ ነው። ለምሳሌ አንድ አባት 5 ልጆች ጥሎ ከሞተ አምባ ይገባ የነበረው አንድ ነው። ስለዚህ ሁሉም አባቶቻቸው በጦርነት የሞቱባቸው ልጆች ሕጻናት አምባ ውስጥ አልገቡም። የአባታችንን ምክር ያነሳሁት ካለነገር አይደለም። በአምባው ውስጥ የነበሩ የስነልቦ...