Posts

Showing posts from 2015
አዲስ ነፍሰ ገዳይ... አሮጌ ነፍሰ ገዳይ! ወያኔ ስልጣን እንደያዘ በተቃውሞ ጎራ የተሰለፍነውን ኢትዮጵያውያን ብዙ ፈተና ገጥሞን ነበር። አንዱ ማን ምን አድርጎ ከኢትዮጵያ እንደወጣ አለመታወቁ ነው። ከ 1991 በፊት ለስደት የተዳረጉት ከቀይ ሸብር ነጭ ሽብር ያመለጡ ናቸው። እንደኔ ያሉት ደግም ለትምህርት ወጥተው ቀልጠው የቀሩ ናቸው። ታዲያ ገና ወያኔ ስልጣን እንደያዘ እዚህ ሆላንድ ...የኢትዮጵያ ሕልውና በጎሳ ፖለቲካ ወዴት ሊያመራ እንደሚችልና ስለ ኤርትራ ጉዳይም ብዙ ኮንፍረንሶች ይካሄዱ ነበር። በእነዚህ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ሰው የገደሉም ሆነ ያስገደሉ ሰዎች ሊሳተፉ ቢችሉም መረጃ ሳይገኝ ማንም ላይ ጣት መቀሰር አልተቻለም። ዛሬ ወያኔ ሳይቀር የተፋቸው አጭብጫቢዎች ግን ተቃውሞው የሚሰነዘረው ስልጣን ከተነጠቁ የደርግ ቡችሎች ነው እያሉ ይጽፍ ነበር። አንዴ አዲስ ዘመን ጋዜጣ ባህርዳርን ከኢሕአፓ ለማጽዳት በሚል ዘመቻ የተገደሉ ከ50( 57?) በላይ የሰዎች ስም ዝርዝር የያዘ ሰነድ ኢፋ አደረገ። 'አብዮታዊ እርምጃ'' እንዲወሰድባቸው የተደረጉት ሰዎች በጥይት አልተገደሉም። አንገታቸው በገመድ እየታነቀ ነው... ማነቁ ያስፈለገው የባህርዳር ነዋሪዎች የጥይት ድምጽ እንዳይሰሙ ተሰግቶ ነው። ከተገዳዮቹ የ18 አመት ልጅም አለችበት። ጥፋትዋም ከቤተሰቦችዋ ቤት መወረሱ ነው። የሚገርመው ግድያው ደግሞ የተካሄደው ከቀይና ነጭ ሽብር በሁዋላ ነው። የግድያውን ማዘዣ የፈረመው የደርጉ መቶ አለቃ እሸቱ አለሙ ነው። ይኼው እሸቱ አለሙ ነው ደግሞ በየስብሰባው እየተገኘ ስለ ኢትዮጵያ አንድነት የሚያስተምረው።  አንዴ ስለ ስንደቅ አላማችን ያለውን ክብርና ፍቅር የገለጸበትን የጋለ ስሜት የታዘቡት ፕሮፌሰር ጌታቸው...

አንደንቁዋሪው ዲስኩር ... "ቁዋሚ ጥቅም እንጂ ቁዋሚ ወዳጅ የለም "!

                    አንደንቁዋሪው ዲስኩር ...  " ቁዋሚ ጥቅም እንጂ ቁዋሚ ወዳጅ የለም "!                                                                                               ቦጋለ ካሳዬ፣ አምስተርዳም ብርሃኑ ነጋ በርሃ ገባ ! ' አሜሪካ ተቀምጠህ የጦርነት ፉከራኽን ተወን '! እያልን ስናብጠለጥለው እነሆ በተግባር አፋችንን ዘጋው አይደለም እንዴ? ተቀብለናል አቤ ቶኪቻው .... ስላቅህ እውነትነት አለው። ሰውየው መጀመሪያ የኢህአፓ አባል ሆኖ ነበር በ 17 አመቱ የሽፈተው ። ዛሬ ደግሞ ከ 40 አመታት በሁዋላ የአርበኝነት ትግል ለማካሄድ አስመራ ገብቱዋል። ምንም እንኩዋን...