Posts

Showing posts from May, 2014
  ፕሮፌሰር መስፍን ፤ በጻፉት ላይ የግል አስተያየቴ፡ የእርሳቸውን ጽሁፍ ለማንበብ ጠቅ ማድረጊያው ሊንክ፤ https://www.facebook.com/pages/Prof-Mesfin-Woldemariam/120300297984572 የእኛ ተራ ነው! በአንድ የአፍሪካ ቀንድን ሰላም፤በሚመለከት የተዘጋጀ ሴሚናር ላይ ከአንድ የጁቡቲ ተወላጅ ጋር ተዋወቁኝ። እንዲህ አለቺኝ፤…«አሁን ጅቡቲን ማስተዳደር የእኛ ጎሳ ተራ ነው፤ ምክንያቱም ባለፈው ሲያስተዳድሩ የነበሩት የእከሌ ጎሳ ነበርና”። ልክ እንደ ወያኔ ትግሬዎች ምንም ሃፍረት ሆነ መሳቀቅ ከፊትዋ አይታይም። ጎሰኝነት አንዱ ዋናው ጠባዩ  አግላይነት(ዘረኝነት) ቢሆንም፤ ለርሱዋም ሆነ ለወያኔ ትግሬዎች ግን ጎሰኝነት ተቀባይነት ያለው ነገር ነው።  የጅቡቲ ነዋሪዎች ከ60% በላይ ሶማሌዎች ሲሆኑ አፋሮች ደግሞ ወደ 35% ናቸው። ትግሬዎች በኢትዮጵያ ከ6% አይበልጡም። በዚሁ ኮንፈርንስ ላይ  የወያኔን ስልጣን መጨበጥ አስመልክቶ እንዲህ ተብሎ ነበር።  “ትግሮቹ ድሃ ስለሆኑ፤ የነበራቸው አማራጭ የብሄርን ጥያቄ አንስቶ ህዝባቸውን ቀስቅሰው ስልጣን ላይ በመውጣት የአገሪቱን ሃብት መቆጣጠር ነው። አሁን ስልጣን ይዘዋል። ወደፊት ግን ሁለት ነገሮች ሊፈጠሩ ይችላሉ። አንደኛው፤ በልተው ወፍራም ሲሆኑ፤ ስልጣን ሊያካፍሉ ይችላሉ። ይኼ ከሆነ ለዴሞክራሲ ተስፋ አለ። አሊያ ግን መብላታቸውን ብቻ ከቀጠሉ፤ የሚገጥማቸው ተቃውሞ አደገኛ ይሆናል። አገሪቱንም ወደ ከፋ ደረጃ ያደርሳታል።” እየሆነ ያለው የመጨረሻው ነው። እንኩዋንስ ፉት ቢሉዋት ጭልጥ በምታክል የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ይቅርና፤ ቻይና እንኩዋን እንዲህ እያደገች ገና ከ300 ሚሊዮን ሕዝብ በላይ ከድህነት ማውጣት አለባት። የቻይና ሕዝብ ሁ...