ከውግዘት ባሻገር ተጠያቂነት!
ከውግዘት ባሻገር ተጠያቂነት! በአብይ አህመድ ኢትዮጵያ የሚካሄደውን የዐማራ ይሁን የሌሎች የዘር ማጥፋት ዘመቻ በተመለከተ፤ ከውግዘት ባሻገር ተጠያቂነት ሊመጣ ነው። ዛሬ ዓይነኬ የሚመስሉት የክልል ናዚዎችና አለቆቻቸው ነገ እጃቸው ውስጥ ስንሰለት የማይገባበት ምንም ምክንያት የለም። ዓለም ትንሽ ናት። የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈፅሞ በአገር ሉአላዊነት በሚል ጭንብል ስር መሸፈን ጭራሽ አይቻልም። ዱሮ ቀረ። በአብይ አህመድ ናዚያዊ አገዛዝ ውስጥ በከፍተኛ ስልጣን ላይ የሚገኙ ሹመኞች በሙሉ፣ በቀጥታ ተሳትፎ፣ በመተባበር ይሁን ዝም በማለት ከዚህ ወንጀልና ተጠያቂነት ማምለጥ አይችሉም። ይሰማል? የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የዘር-ጥፋት መከላከያ ድርጅት (ኢተክዘድ)/Orthodox Tewahdo Against Genocide in Ethiopia(OTAGE)፤ በጣም ታሪካዊ ስራ እየሰራ ነው። በአጭሩ ሰነዱን ስንቆ በአራጆች ላይ ክስ ሊመሰርት እየተዘጋጀ ነው! በሚቀጥለው ማክሰኞ ከፍተኛ የመነቃቃት ስራ በአለም ዙሪያ እንደሚጀምር አዘጋጆቹ በኢትዮ360 አስታውቀዋል። https://www.ethio360media.info/ ለዚህ ሕጋዊ እርምጃ ገንዘብ ወሻኝ ነው። በዚህም መሰረት የሚከተለውን ማስፈንጠሪያ በመንካት ይኼን መቆሚያ የለሽ እርድ ለማስቆምና አራጆቹን ለህግ ለማቅረብ በሚደረገው ጥረት ታሪካዊ ሃላፊነታችንን እንወጣ! ችግሩን ከመነሻው እንቅበረው! እግዚአብሄር ሰላሙን ያውርድልን። https://www.gofundme.com/f/orthodox-tewahdo-against-genocide-in-ethiopia?utm_source=customer&utm_medium=copy_link&utm_campaign=p_cf%20share-flow-&fbclid=IwAR24sUTW...